Get Mystery Box with random crypto!

የ2014 ዓ.ም የአማራ ክልል የወርልድ ቴኳንዶ ሻምፒዮና ውድድር በውቢቷ ባህርዳር በአማራ ክ | Kedir world Taekwondo

የ2014 ዓ.ም የአማራ ክልል የወርልድ ቴኳንዶ ሻምፒዮና ውድድር በውቢቷ ባህርዳር

በአማራ ክልል የወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት በየዓመቱ የሚካሄደው የ2014 ዓ.ም የአማራ ክልል የወርልድ ቴኳንዶ ውድድር የቅድመ ውድድር ስብሰባ ዛሬ ማለትም ሚያዚያ 29/2014 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ ተካሄዷል።

በዚህ በ2014 ዓ.ም የአማራ ክልል የወርልድ ቴኳንዶ ሻምፒዮና የቅድመ ውድድር ስብሰባ ላይ የ11 ዞኖች አሰልጣኞች፣ ቡድን መሪዎችና የተወዳዳሪ ስፖርተኞች ወኪሎች ተሳታፊ ሆነዋል።

እሁድ በ30/08/2014 ዓ.ም የመክፈቻ ጨዋታዎች
1. በወንዶች -54 እና -80 ኪሎ ግራም፣
2. በሴቶች -53 እና -62 ኪሎ ግራም ይፋለማሉ፤
ውድድሩ ከሚያዚያ 30 - ግንቦት 04/2014 ዓ.ም ይቀጥላል።

መልካም ዕድል!!!