Get Mystery Box with random crypto!

እንኳን አደረሳቸሁ አደረሰን “መሠረቶቹ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፤” | ዘማሪ ክብሮም

እንኳን አደረሳቸሁ አደረሰን
“መሠረቶቹ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፤”
* መዝ 86፥1*
"ኢያቄም ወሐና ወለዱ ሰማየ
ሰማዮሙኒ አሥረቀት ፀሐየ"

➠የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያም
የሁላችንም እናት ልደቷን ስናከብር ቅር ሚላቸው ሰዎች ካሉ ይህን ቃል ያስተውሉ
“ደስታና ተድላም ይሆንልሃል፥ በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል።”
ሉቃስ 1፥14 ልደት ማለት መወለድ ማለት ነው። በመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ መወለድ ብዙዎች ሚደሰቱ ከሆነ ታዲያ እውነተኛው ዳኛ፣አማናዊውን ፀሐይ፣እውነተኛውን መብልና መጠጥ፣ቅን ፈራጁን ኢየሱስ ክርስቶስ የወለደች የእናቱን(የእናታችን) የቅድስት ድንግል ማርያምን ልደትማ እንዴት አናክብር ያው በልዩ ሁኔታ ልደትሽ ልደታችን ነው ብለን እናከብረዋለን።
ዘማሪ ክብሮም ገብረኪዳን
ግንቦት 01/09/2015 ዓ.