2022-05-25 22:41:20
ማንም ሰዉ በፍፁም መፍራትህን እንዳያዉቅ! ተኩላዎች መፍራትህን ከሰዉነትህ እንቅስቃሴ ያዉቃሉ ምንም ያህል ብትፈራም፣ ማንም ሰዉ ፊት እንደፈራህ ሆነህ አትቁም! ቆፍጠን ብለህ ጠንከር ብለህ ድምፅህን ረጋ አድርገህ አይንህን ቀስ አድርገህ አንቀሳቅስ
• ሰዎችን ትንሽ አርቃቸዉ ማንንም አትመን ወደራስህ ህይወት በጣም ካስጠጋሃቸዉ ማንነትህን በደንብ አብጠርጥረዉ ስለሚያዉቁ መናቅ ይጀምራሉ
ስለዚህ መስመር አስምር ሰዎች ስላንተ ትንሽ ብቻ ካወቁ አክብረዉህ ይኖራሉ ስላንተ ያላቸዉ መረጃ አነስተኛ ሲሆን የቀረዉን ነገር በራሳቸዉ ሃሳብ ዉስጥ በሚፈጥሯቸዉ ነገሮች ሲፈልጉ ይሙሉት
• ወሳኝ ከምትለዉ ሰዉ በስተቀር ያገኘኸዉን ሁሉ ዝም ብለህ ወደቤትህ አትዉሰድ ሰዎች በተፈጥሮ ቤትህን ሲያዉቁ አንተነትህን በቀላሉ መግለፅ አይከብዳቸዉም ምን አልባትም ሲያወሩ ትደርስባቸዉ ይሆናል
• ስለዚህ ሰዎችን በዉጪ አግኝ ቢዝነስም ይሁን ሌላ ማንኛዉም ነገር በዉጪ ጨርስ ከምንም በላይ ለራስህ ዋጋ ስጥ ለማንም ለምንም በቀላሉ የምትገመት ሰዉ አትሁን ይኸዉ ነዉ
• ሰዎች በብዙ ነገር ማንነትህን ይፈታተኑታል፡፡ ስለዚህ 'ለምን ተፈተንኩ?'ብለህ አትቆጣ አትናደድ ሃይልህን አትጨርስ ብቻ ለሚመጣዉ ነገር እራስህን አዘጋጅ
አንዳንድ ነገሮች ፈፅመህ ካልጠበከዉ መንገድ እየጎረፈ ሲመጣ ታያለህ የዛኔ እንደምንም ብለህ እራስህን አረጋጋ ከአምስትና አስር አመት በኋላ ያለህበት ነገር ምን ያህል ተፅእኖ ያሳድርብሃል? ብዙ ነገሮች ለጊዜዉ ብቻ የሚያስቆጡ ስለሆኑ በእርጋታ አሳልፋቸዉ
• ሁል ጊዜ ለሰዎች ክብር ይኑርህ ቢያጠቁህም እነሱን ለማጥቃት መልሰህ ጦርነት አትክፈት ባህሪያቸዉን ወይም ከላይ ያለዉን ማንነታቸዉን አታጥቃዉ ነገር ግን የዉስጥ ሃሳባቸዉን አትቀበል
ዋናዉን የልብ ፍላጎታቸዉን ብቻ ቀይ ስጠዉ! ይህን የምታደርገዉ ግን በተረጋጋ ማንነት ዉስጥ መሆን ቢችል ጥሩ ነዉ ነገሮችን ከግራም ከቀኝም የማየት አቅም ስለሚኖርህ የበሰለ ዉሳኔ መወሰን አያቅትህም
• ከማን ጋር እንደምትዋጋ እወቅ ልታሸንፍ የምትችለዉን ጦርነት ብትመርጥ ይሻልሃል ያለበለዚያ ብዙ ነገር ይበለሻሻል
ምሳሌ ልስጥህ አንድ ጓደኛዬ ከሴት ጓደኛዉ ጋር ተጣላና መደባደብ ጀመረ ከሁለተኛ ፎቅ ላይ እቃዉን ሁሉ እያወጣች መወርወር ጀመረች ፊቱን ሞነጫጭራ ሞነጫጭራ አዲሱን የቀለበት መንገድ ዲዛይን ፊቱ ላይ ሳለችዉ እሱም አልተዉም ብሎ ደበደባት
ቴሌግራም ቻናላችንን
@kebranaw
217 views , 19:41