Get Mystery Box with random crypto!

#አትፍረድ ፀሀፊ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi) Part ➋➋ ከቆይታዎች በኋላ መቀላለድ ፣መጎሻ | ካሊድ ታረቀኝ(ye umi) official

#አትፍረድ

ፀሀፊ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi)

Part ➋➋

ከቆይታዎች በኋላ መቀላለድ ፣መጎሻሸም ተጀመረ፡ ፈገግታዋና ጮክ ብሎ የሚሰማው ሳቋ እቤቴን ከምሽቱ ጋር አብሮ የሚሄድ ውበት አላብሶታል፡ አስራ አንደኛው ሰአት አለ የስራ ባለደረባዬ አሼ፡

ግን እኔ ምልሽ ምንያህል ትወጅኛለሽ?። ስል በጫዎታዎች መሀል ጠየኳት። አይኖቿን እያጉረጠረጠች ጉንጯ ወደ ውስጥ እስኪሰረጉድ ድረስ ፈገግ ካለች በኋላ።
ባክህ እንዴት እንደምጠለህ ባወክ? ስትል ቀልድ ቢጤ ነገር ተናገረች። ፈገግ ብዬ ጉንጯን በጣቴ ቁንጥጥ አደረኩኝ፡፡

ልፊያው ቀጥሏል፡

ሀኒምን ልክ ፋሪስ ናዲያ ላይ የፈጠረውን አይነት ነገር ለካሳ ይሆን ዘንድ ሀኒም ላይ እየሞከርኩ ነው። ሀኒም ለመግደርደር እየጣራች ነው ደጋግሜ ጉንጯንና ከንፈሯን ሳምኩ በስተመጨረሻ ሀኒምን ሌላ አለም ለማሳፈር ቻልኩ፡

ስልኳ እየጠራ ነው፡ ግን ሀኒም ለስልኳ ሳይሆን ለእኔ ቦታ ሰጥታለች፡ ሙከራዬ አሁን ላይ ወደ ስኬት ተቀይሯል።

በቃ ልሂድ አብዲዬ ከእቤትም ተደውሏል። አለች ከጎኖ ያለውን ስልክ አብርታ ካየች በኋላ ፡ከጭንቅላቷ ላይ ሊንሸራተት ያለውን ሂጃብ እያስተካከለች።
ቁም ነገር ሰርቼ ያ ሸነፍኩ ያህል ልቤ ላይ ለየት ያለ ስሜት እየተሰማኝ ነው። አሁን ፋሪስ መፍረድ ምን እንደሆነ በደንብ የሚረዳ ይመስለኛል። ግን ልቤ በስራዬ ሳያዝንም አልቀረ።
በቃ ነይ ቶሎ እንሂድ። ብያት ከቤት ወጥተን እስከነሱ መኖሪያ ቤት ድረስ በመኪናዬ አደረስኳት ፡በመሃል ላይ የቤተሰቡ መሪ ከሆኑት ከአባቷ ጋር በስልክ አውርታ ነበር።

በአዲስ መንፈስ ወደ ስራ ከተመለስኩ በጣት የሚቆጠሩ ቀናቶች አልፈዋል።

ሁሉም ነገር ወደ በፊቱ ተመልሷል አብርሽ ከሆስፒታል ተሽሎት ወጥቷል። ቢሆንም ግን ያ አመሉ አሁንም አለቀቀውም። እኔ አሁንም ከመጠጥ እንደራኩኝ ነው። የሀኒም እህት ኒቃብስቷ ሳሚያም ሰርጓን አብልታናለች።

ሰአዳ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ስለ ናዲያ አንስታ አታውቅም ፡በስልክም ሆነ በአካልም አልፎ አልፎ እንገናኛለን ፡ግን ያለምንም ጥርጥር ሰአዳ እንደወደደችኝ እርግጥ ነው።

ዛሬ በጊዜ ከቢሮ ወጥቼ ፡ሰሞኑን ለየት ያለ ፀባይ ያመጣችውን መኪናዬን ገራጅ አስገብቼ፡ እግረ መንገዴን እናቴን ዘይሬ ወደ ቤት መመለስ ጀመርኩ። ሰፈር እንደደረስኩ ሀኒምን ለማናገር አቅጄ እየተራመድኩ ቢሆንም እኔ ካለሁበት የጋራ መኖሪያ ቤት ህንፃ ላይ ጎረቤቴ ከሆነው ከአንድ ወዳጄ ጋር ከሀኒም ሱቅ ጥቂት እራቅ ብሎ ተገናኘን፡ እንዳየኝ የያዘውን መኪና ቀጥ አደረገና አቆመ ከመኪናው በስተቀኝ በኩል ስለነበርኩ የመኪናውን መስኮት እንደከፈተልኝ፡ ከወገቤ ሰበር ብዬ እጄን ወደውስጥ በረጅሙ ዘርግቼ ከጨበጥኩት በኋላ፡ ሰሞኑን ስላላየሁት የጠፋበትን ምክንያት እጠይቀው ጀመር፡ በስራ ጉዳይ እንደሆነና አዲስ የስራ እንቅስቃሴ እንደጀመረ ነግሮኝ ስለስራው አንዳንድ ነገረ ካለኝ በኋላ የቢዝነስ ካርድ ሊሰጠኝ እጁን ከጎኑ ወደተቀመጠችው ትንሽዬ ጥቁር ቦርሳ ሰደደ። ወገቤን እረዘም ላለ ደቂቃ ማጠፉ ስለከበደኝ ቀና እንዳልኩ፡ ከሀኒም ሱቅ መውጫ ላይ ያለ አንድ ሰው አይኔ ውስጥ ገባ፡

ሰአዳ
እንዴ?። አልኩ ጮክ ብዬ።
ምነው?። አለኝ ከመኪናው ውስጥ ያለው ወዳጄ።
አይ ምንም፡ የሆነ የማውቀውን ሰው አይቼ ነው።
ሰአዳ ወደ እኔ ቤት መሄጃ በመዞር እያየች፡ በመጣደፍ እየተራመደች አልፋኝ ሄደች።
ምን ልትሰራ መጣች ያውም ሀኒም ሱቅ።
ቢዝነስ ካርዱን ተቀብዬው ወዳጄን ተሰናብቼ፡ ወደ ሀኒም ጋር የመግባቱን ሀሳብ ወደጎን ትቼ ወደቤት ገባሁ።

በመስኮቱ ወደ ታች እየተመለከትኩ ሰአዳ እንዴት ልትመጣ ቻለች? እያልኩ እራሴን እጠይቅ ጀመር። ልደውልላት አሰብኩና መልሼ ተውኩት።
እራሴን በጥያቄዎች እያስጨነኩ ስለሆነ ማምሻውን ለሰአዳ መደወል ጀመርኩ ስልኳ አይሰራም ፡ቴክስት ባደርግም ምንም ምላሽ የለም። ምን እንደተፈጠረ አላውቅም እቤት ውስጥ ባለው ገመድ አልባ ስልክ ላይ የሰአዳን ቁጥር መትቼ እደውል ጀመር ጥቂት ቆይቶ ስልኩ ጠራ፡እንዴ በእኔ ስደውል ለምን አይሰራም? የሚል ጥያቄ ጭንቅላቴ ላይ እንደተፈጠረ ስልኩ ተነሳ
ሄለው።
ሄለው ሰአዳ።
ስልኩ በጆሮዬ ላይ ተዘጋ ደግሜ ሞከርኩ እስከነጭርሱ አይሰራም። ሰአዳ ምን አስባ ይሆን።

ከሀኒም ጋር ከተኛን አስራ አምስት ቀን ሆኖናል ፡እንዳገባት መጨቅጨቅ ጀምራለች እኔ ደግሞ ከጭቅጭቋ የምገላገልበትን ሌላ መንገድ ቀድሜ ነድፌያለሁ።

ሰሞኑን አብርሃም ተሽሎት የነበረ ቢሆንም በድጋሚ ሆስፒታል መግባቱን ሰምቻለሁ። ግን ሄጄ የምጠይቅበትን ቀን ነገ ዛሬ ከማለት ውጭ ቁርጡን ለመወሰን አልቻልኩም ፡ ቀናቶች እንደሁሌውም መሄዳቸውን አላቆሙም።

ወደስራ ለመሄድ እየተሰናዳው ባለሁበት ሰአት ከነጋ የመጀመሪያው ጥሪ ስልኬ ላይ ማቃጨል ጀመረ።
ቢሮዬ ያለበት ቦታ ላይ ያሉት ጓደኞቼ ውስጥ አንደኛው ነው፡ ስልኩን ከተቀመጠበት አንስቼ ድሜፁን ላውድ ካደረኩት በኋላ በእጄ ላይ እንዳለ
ሄለው፡
ሄለው አብዲ እንዴት አደርክ
ደህና አልሃምዱሊላህ፡ አንተስ?
ደህና ነኝ አብዲዬ እኔ ምልህ እ.. አብርሽ...

Part ➋➌ ይቀጥላል !

any comments
@kaludi_bot


@kalidoyeumi
join telegram