Get Mystery Box with random crypto!

#አትፍረድ ፀሀፊ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi) Part ➋❶ ግን እኮ መሽቷል። ስትል ባመጣሁ | ካሊድ ታረቀኝ(ye umi) official

#አትፍረድ

ፀሀፊ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi)

Part ➋❶

ግን እኮ መሽቷል። ስትል ባመጣሁት ሀሳብ ለመስማማት ዳርዳር አለች።
አሁን ልቤ አንድ ነገር እየነገረኝ ነው ፡ፋሪስን መበቀያው ጊዜው አሁን መሆኑን።
እና ቢሆንስ የኔ ቤት ከመሸ እንግዳ አይገባም አሉሽ እንዴ?። ደግሞ አሁን የእንግድነት ስሜት ቢሰማሽም ወደፊት የቤቱ ባለቤት መሆንሽ አይቀርም። ስል አስፈነደቅኳት። ይሄ ድንቅ ፈገግታ በዚህ ምሽት ላይ ላየው ሰው፡ እንዴ ጨረቃ በሰው ፊት ላይ ልክ እንደመስታወት ትታይ ጀመር እንዴ? ብሎ ወደሰማይ የሚያንጋጥጥ ይመስለኛል።

ምንም ማድረግ አልችልም፡ ሀኒም እኔ እስከዛሬ ካጋጠሙኝ ሴቶች ሁሉ አንቺ ለእኔ ትለያለሽ፣ በጣም ልዩ ነሽ፣ አላህ ብሎ አግብቼሽ ብኖር በጣም ደስተኛ ነኝ፡ እመኚኝ ሀኒም እንዳንቺ አይነት አዝግ፣ቆንጆ፣ከሰው ጋር ቶሎ የመግባባት አቅም ያለው፣ እረ እኔንጃ! ከአንቺ ውጭ የሚገኝ አይመስለኝም። በቃ ምን ልበልሽ በአጭሩ አንቺ ለኔ ከልዩም ልዩ ነሽ፣ የተፈጠርሽውም ለእኔ ሽልማት ሆነሽ ይመስለኛል። ግን ግን ወንድምሽ በድሎሻል፡፡ አልኩ በሆዴ የሀኒምን አይኖች በሀሳብ ተሳፍሮ እየተመለከትኳቸው።

አብዲ፣ አንተ የት ሄድክ። የምትላዋ ቃል ወደ ራሴ መለሰኝ ልቤ በጣም ፈርቷል
እ ምን አልሽን የሆነ ሀሳብ ውስጥ ገብቼ እኮ ነው።
እንሂድ።
ወዴት?
ወደቤትህ ነዋ።
እ.. እ.. እሽ እሽ።
ያቀድኩት ነገር እግር በእግር እየተሳካ ያለ ይመስለኛል።

ፈገግ ብዬ ፍቃደኛ ስለሆንሽ አመሰግናለሁ። ስል ተያይዘን ወደእኔ ቤት ሄድን።
ሀኒም ከውኅላ እንዳለች እኔ ከፊት ቆሜ የተዘጋውን በር በያስኩት ቁልፍ እከፍት ጀመር። ሀኒም እመኚኝ እግርሽ ይህን ቤት የረገጠበትን ቀን ትረግሚያለሽ።አልኩኝ አሁንም በሆዴ። ከመንቀጥቀጥ እና ከመርበተበት በማይተናነስ ሁኔታ ላይ ሀኜ ቁልፉን ወደ ግራ ማዞሬን ቀጠልኩ።

ወደ ውስጥ እንደገባን፡
ያው የወንደላጤ ቤት እንደዚህ ነው።
ፈገግ እያለች፡
ባለፈው እኮ ተናድጄም ተጣድፌም ቢሆን እዚህ የመግባት እድሉን አጊንቼ ነበር።

የለበስኩትን ሌዘር ጃኬት እስካወልቀው ድረስ ሀኒም በቆመችበት እቤቴን እንደሚከራይ አሊያ እንደሚገዛ ሰው ዙሪያውን ትቃኝ ጀመር።

እኔ ምልሽ አልኩ የሰፈነውን ዝምታ ለማደፍረስ በሚመስል መልኩ፡ የለበስኩትን ሸሚዝ በእጄ ወደላይ በማንሸራተት እየሳብኩ።
እንዴት አየሻት እቤቴን?
ማንሻ አላህ! ቆንጆ ቤት አለህ።
ልክ እንደምወዳት ልጃ? ስል በፈገግታ ታጅባ እንድትሽኮረመም አደረኳት።
በይ በቃ። ስል ፊት ለፊት ወዳለው ፍራሽ እጄን በመዘርጋት። እንድትቀመጥ እየጠየኳት መሆኑን ባሳየኋት ምልክት በደንብ ተረድታለች። ጫማዋን አውልቃ ግማሽ ለግማሽ ታጥፎ በተዘረጋው ምንጣፍ ላይ አልፋ በትራሶች ወደተከበበው ፍራሽ ላይ በመጠጋት አረፍ አለች።
አሁንም ፍራቻው አለቀቀኝም ለምን እንደሆነ አላውቅም፡ በቀልና ፍቅር ተዛብቶብኛል።
ወደ ኪችኑ በመግባት እስቶቩን አብርቼ
ውሃ ጣድኩ። ለወዳጄ ሻይ ለመጋበዝ በማሰብ።

ከኪችኑ ወጥቼ ወደ ሀኒም ጋር በመጠጋት ፊት ለፊቷ ያለውን ቴሌቭዥን ለቤቱ ድምቀትና ለሀኒም ዝምታ ጨዋታ ይፈጥር ዘንድ ከፈትኩ።

እኔም ልህ ምንም ነገር ልታመጣ እንዳታስብ አሁን እሄዳለሁ አልቆይም።
ከኪሴ ውስጥ ስልኬን አውጥቼ ሰአቱን ተመለከትኩትና በኔና በሀኒም መሀከል ባለው የጎን ክፍተት አስቀምጬ።
ማለት?። አልኳት ፊት ፊቷን እያየሁ።
በጣም መንጎዳጎድ አበዛህ፡ ደግሞ ጃኬት አውልቀህ ሸሚዝ ስትሰበስብ የሆነ ከባድ ስራ የምትሰራ ነው የሚመስለው።
አሽሙር ይሁን ምስጋና ነገሩ ባይገባኝም ከሳኩላት በኋላ።
ሻይ እያፈላው ነው። ስል ግብዣው ሻይ በቻ መሆኑን እንድታውቅ አደረኩ።

የተጣደውን ሻይ እንደፈላ በወግ በወጉ አሳምሬው ለማቅረብ በዝርግ ሰሀን ላይ አጫጭር ብርጭቆዎችን ደርድሬ ወደ ሳሎኑ ስመጣ ሀኒም ደንገጥ ብላ ስልኬን ወደቧታው ስትመልስ አይኔ ውስጥ ገባች። እኔም ማንኛውንም ጥያቄ ሳላነሳ ከሀኒም ፊት ለፊት ሻዩን አስቀምጬ ከጎኗ ተቀመጥኩ።

ጥቂት ቆይቶ ሰአዳ መደወል ጀመረች ከሚሰማው ጥሪ እኩል እስክሪኑ እንደበራ አይኔ የገባ መልህክት እንዳለኝ ከእስክሪኑ አናት ላይ ወደሚታየው የልተነበበ መልእክት መጠቆሚያ ላይ አረፈ። ስልኩን ለማንሳትም ሆነ የተላከልኝን መልእክት ለማንበብ አልፈለኩም ሙሉ ለሙሉ ስልኬን ዘጋሁ። ሀኒምም ለምን ትዘጋዋለህ? ከሚል ጥያቄ ተቆጥባለች።

ከቆይታዎች በኋላ መቀላለድ ፣መጎሻሸም ተጀመረ፡ ፈገግታዋና ጮክ ብሎ የሚሰማው ሳቋ እቤቴን ከምሽቱ ጋር አብሮ የሚሄድ ውበት አላብሶታል፡ አስራ አንደኛው ሰአት አለ የስራ ባለደረባዬ አሼ...

Part ➋➋ ይቀጥላል !

any comments
@kaludi_bot


@kalidoyeumi
join telegram