Get Mystery Box with random crypto!

#አትፍረድ ፀሀፊ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi) Part ❶❽ እሽ ችግር የለውም ነገ ስራ ት | ካሊድ ታረቀኝ(ye umi) official

#አትፍረድ

ፀሀፊ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi)

Part ❶❽

እሽ ችግር የለውም ነገ ስራ ትጀምራለህ እንዴ?
አይ ነገ እንኳን አልገባም እኔ ምልሽ ግን የወንድምሽን ስሙን እኮ አላውቀውም።
ስል ወደ ዋናው ነጥብ ተጠጋሁ።
ሲጀመር በደንብ መቼ ተዋወቃችሁ እና ነው ለማንኛውም ፋሪስ ይባላል ደግሞ እርሳውና ዋ!

ከተጋደምኩበት አልጋ በፍጥነት ከወገቤ ቀና ስል ተቀመጥኩ
እየሆነ ያለው ነገር ህልም መስሎ እየታየኝ ነው እይሆንም አይሆንም ፋሪስ የሀኒም ወንድም በፍጹም አይሆንም ስል ከእራሴ ጋር መሟገት ጀመርኩ

እ የት ሄደክ
ተኛህ እንዴ
እንቅልፋም በል ደህና እደር።
በድንጋጤ ዝምታን በገባሁ ሰአት ከ ሀኒም የተላኩ ቴክስቶች ናቸው።

በጠዋት ተነስቼ ለድርጅቱ የሚሆኑትን አዳዲስ እቃዎች የሚያስረክበንና የሚጠግንልን አካል ሙሉ ስራውን ስለጨረሰ በውላችን መሰረት ነገ ቀሪውን ክፍያ መፈፀም እንዳለብን በስልክ አወራሁኝ።

ዛሬም ግን ስራ የመግባት ጉጉቴ ማታ በተፈጠረው ነገር ገደል ገብቷል። አሁን ምን ተሻለ ሀኒምን አፍቅሬያታለሁ ወንድሞ እህቴን እንዳጣ ትልቁ ምክንያት እሱና እሱ ብቻ እንደሆነ አረጋግጫለሁ።

ስልኬ መጥራት ጀመረች ሰአዳ ናት።

ሄለው አብዲዬ ሰላም አለይኩም እንዴት አደርክ ተኝታ እያወራችኝ እንደሆነ በደንብ ያስታውቅባታል።
ወአለይኩምሰላም ሰአዲ እንዴት አደርሽ
አልሃምዱሊላህ
ተኝተሽ ነው?
እ ማታ እኮ እንቅልፍ እንዲች ባይኔ ሳይዞር ፈጅር ከሰገድኩ ቡኋላ ትንሽ ተኛው።
ምነው በሰላም
አብዲዬ ይቅርታ አድርግልኝና እኔ ትላንትና ያየውት ነገር እውነተኛ ፋሪስ መሆኑን ውስጤ አምኖ ተቀብሏል።

እንባዬን እያወረድኩ እንደመሳቅ አልኩና ሰአዲዬ ልጅቷን እኮ ጠይቄያት ነበር እና ሌላ ስም ነው የነገረችኝ ስል ዋሸኋት
እየተዋጠላትም ባይሆን እረ እ.. እ.. ምን አልባት ይሆናል ግን እኮ አብዲዬ አላህ አጋልጦት ፋሪስ የተባለውን ክፋ በአይንህ ብታየው ትላንትና ያየነው እራሱ ነው ትል ነበር።
አይ አንዳዴ እንደዚህ አይነት ነገር ያጋጥማል።
ይሆናል። አለች አሁንም ነገሩ እንዳልተዋጠላት በማሳወቅ።
በቃ በይ እረፍት አድርጊ አላህ ያለ ቀን እናገኘዋለን።
እሱማ አይቀርም በል መልካም ቀን። ብላ ተሰናበተችኝ

ከሰአት ቡሃላ ወደ ጀሞ ተመለስኩ መኪናዬን ከነ ሀኒም ሱቅ ፊትለፊት እንደሁሌውም አቁሜ ሀኒም ጋር ጎራ አልኩ ከወንድሟ ጋር እየተጨዋወቱ ከት እያለ ይስቃል ሰላም አለይኩም ስል ተቀላቀልኳቸው ሀኒም በደስታ ተቀበለችኝ ወንድሟ ሰካራም ስለሆንኩ ብዙም ቦታ ሊሰጠኝ አልፈለገም። ወሬያቸውን ቀጥለው ይሳሳቁ ጀመር ሀኒም ጨዋታውን እንድቀላቀል የማትፈነቅለው ድንጋይ የለም ወንድሟ እህቴን ነጥቆኝ እንዲህ ሊስቅ አይገባም ስል ደመደምኩ። ከቆምኩበት እግሬን አንቀሳቀስኩ።
እንዴ አትጫወትም እንዴ አለች ሀኒም። ቆይ ተመልሼ እመጣለሁ እቤትም አልጋባሁም ብዬ ወጣሁ ብፍጥነት ወጣሁ።

እቤት እንደገባሁ ጥቂት ቆይቼ በእጄ መዳፎች ላይ ካስቀመጥኩት ስልክ፡ እስክሪኑ ላይ አይኖቼን በመጣል ምንም ከማይናገረውና ከማይጋገረው የናዲ ፎቶ ጋር አወራ ጀመር።

ናዲ ላንቺ ስል የማፈቅረውን ሰው ልበድል ነው እኔ እንዳለቀስኩት እኔ ሰካራም እንደተባልኩት ፋሪስም ይባላል። እስክሪኑ ላይ ከአይኔ የሚወርድ አንድ ዘለላ እንባ ጠብ አለ፡


Part ❶❾ ይቀጥላል !

any comments
@kaludi_bot


@kalidoyeumi
join telegram