Get Mystery Box with random crypto!

#በመጀመሪያ_ፍጥረት_እግዚአብሔር_አንዲት_ሴትን_ለአንድ_ወንድ_ሰጥቷልና። ስለዚህ ሁለቱም አንድ ስጋ | JUSTIN APOLOGETICS721]

#በመጀመሪያ_ፍጥረት_እግዚአብሔር_አንዲት_ሴትን_ለአንድ_ወንድ_ሰጥቷልና። ስለዚህ ሁለቱም አንድ ስጋ ይሆናሉ። [መፅሐፈ ዲዲስቅልያ(didaskalia) 13:8-19]
ስለዚህ በክርስትና ከአንድ በላይ ማግባት ፈፅሞ የተከለከለ ነው። አንድ ነገር ብየ ልጨርስ። አንድት ቅድስት ሴት ነበረች ሰሟ አፎምያ ይባላል። እናም ከባሏ ጋር እግዚአብሔር በማመሰገን ይኖሩ ነበር። ከዚያም ባሏ አረፈ። እሷም መበለት ሆና መኖረ ጀመረች።ይህን ያየ ሰይጣን ባል እንዲታገባ ይወተውታት ጀመር። እሷም አልስትለት ስትል መልአክ መስሎ አብርሃም ይስሀቅ ዳዊት አግብተዋ ሰለዚህ አንቺም እንደነሱ አግቢ ይላታል። ከዛም "መልአክ ከሆንክ መስቀልህ ወዴት አለ? የንጉስ ጭፍራ ሁሉ የንጉሱን ማሕተም ሳይዝ አይሔድምና አለችው"... ከዛም ሰይጣን መሆኑ ታወቀበት.....ሚካኤል ታደጋት።[ስንክሳር ዘወርኀ ሰኔ:12]
ይህ ታሪክ እኛ የሚወክል ነው። ከዚህ የምንረዳው ዳዊት አብርሀም ....ብዙ ሚስት አግብተዋልና እናንተ አግቡ የሚለን ከሰይጣን እንደሆነ ግልፅ ነው።

"ከአንድ በላይ ጋብቻ ከተፈጥሮ ህግ ውጭ ነው"
ስብሐት ለእግዚአ ኩሉ አሜን
@JUSTIN_APOLOGETICS721