Get Mystery Box with random crypto!

Info Health Center (አይ ኤች ሲ የጤና ማዕከል, IHC Health and Wellness Consultation Center )

የቴሌግራም ቻናል አርማ jossiale2022 — Info Health Center (አይ ኤች ሲ የጤና ማዕከል, IHC Health and Wellness Consultation Center ) I
የቴሌግራም ቻናል አርማ jossiale2022 — Info Health Center (አይ ኤች ሲ የጤና ማዕከል, IHC Health and Wellness Consultation Center )
የሰርጥ አድራሻ: @jossiale2022
ምድቦች: ጤና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.22K
የሰርጥ መግለጫ

አገልግሎታችን በአካል ቀርበው ለማግኘት፤ ለማማከር፥ ቀጠሮ_ለማስያዝ በ 251921785903 እና 251711114443 ላይ ይደውሉ።
#ጎተራ_ንፋስ_ስልክ_ማሞ_ራሚ_ህንፃ_4ኛ_ፎቅ_ ላይ ያገኙናል።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-12 17:40:36 የደም ማነስ/ Anemia

የደም ማነስ በደምዎ ውስጥ በቂ የሆነ ጤናማ ቀይ የደም ሴሎች ወይም ሄምግሎቢን ሲያንስ የሚከሰት በሽታ ነው፡፡ ሄሞግሎቢን ዋናው የደም ሴሎቻችን ክፍል ሲሆን ከኦክስጅን ጋር ይጣመራል በጣም ጥቂት ወይም ጤናማ ያልሆኑ ቀይ የደም ሴሎችን ካሉን ወይም ጤናማ ያልሆነ ጥቂት ሄሞግሎቢን ካለን በሰውነታችን ውስጥ ያሉት ሴሎች በቂ ኦክስጅን አይደርሳቸውም፡፡

የደም ማነስ ምልክቶች ከሆኑት አንድ የሆነው የድካም ስሜት የሚከሰተው የሰውነት አካሎቻችን በትክክል ለመስራት የሚፈልጉትን ያክል ኦክስጅን ስለማያገኙ ነው፡፡ ሴቶች ህፃናት እና ከባድ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ለደም ማነስ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው፡፡

★ ልናስታውሳቸው የሚገቡ ጠቃሚ ነገሮች እነሆ፦

አንዳንድ የደም ማነስ አይነቶች በዘር የሚተላለፉና በወሊድ ጊዜ ህፃናትን የሚያጠቁ ናቸው፡፡
ለአቅመ ሂዋን የደረሱ ሴቶች በብረት እጥረት ለሚከሰተው የደም ማነስ በተለየ ሁኔታ የተጋለጡ ናቸው ምክንያቱም በወር አበባ ጊዜ የደም መፍሰስ እና በእርግዝና ወቅት የደም ፍላጎት ስለሚጨምር ነው፡፡
በእድሜ የገፉ ሰዎች በደም ማነስ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ነው ምክንያቱም በምግብ እጥረት እና የተለያዩ የህክምና ችግሮች ስለሚኖሩባቸው ነው፡፡ የተለያዩ የደም ማነስ አይነቶች አሉ ሁሉም የተላያዩ መነሻ እና የተለያየ ህክምና አላቸው፡፡ በብረት እጥረት የሚከሰተው የደም ማነስ በጣም የተለመደ በሽታ ነው አመጋገባችንን በመቀየር እና የብረት ንጥረ ነገር በመዉሰድ በቀላሉ መታከም እንችላለን፡፡ አንዳንድ የደም ማነስ አይነቶች ለምሳሌ በእርግዝና ወቅት የሚከሰተው ጤናማ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ እስከ እድሜ ልክ የሚዘልቁ ናቸው፡፡

★ የደም ማነስ መነሻ ምክንያቶች!

ከ400 የሚበልጡ የደም ማነስ አይነቶች አሉ እነሱም በሶስት መደቦች ይከፈላሉ፦
1. በደም መፈሰስ የሚከሰት!
2. ቀይ የደም ሴሎች ምርት መቀነስ ወይም የማምረት ችግር!
3. በቀይ የደም ሴሎች ውድመት/ጥፋት የሚከሰት የደም ማነስ አይነቶች ናቸው፡፡

1. በደም መፍሰስ የሚከሰት የደም ማነስ!

ደም በሚፈሰን ጊዜ ብዙ ቀይ የደም ሴሎችን እናጣለን ይህም የሚከሰተው በትንሹ ለረጂም ሰዓት ደም ስለሚፈሰን ሲሆን ይህን ነገር ብዙ አናስተዉለውም፡፡ እንደዚህ አይነቱ ከባድ የደም መፍሰስ በሚከተሉት መንገዶች ይከሰታል
ከጨጓራና አንጀት ጋር የተያያዘ በሽታዎች (ክንታሮት፣ቁስለት፣የጨጓራ ህመም እና ካንሰር)
የህመም ማስታገሻ መድሃኒቶች(አስፕሪን ወይም አይቡፕሮፊን)
የወር አበባ እና በወሊድ ጊዜ(በተለይ በወር አበባ ጊዜ የደም ፍሰት ከመጠን በላይ ከሆነ እና በተደጋጋሚ እርግዝና ከተከሰተ)

2. ቀይ የደም ሴሎች ምርት መቀነስ ወይም የማምረት ችግር!

ይህ አይነት የደም ማነስ በሽታ በሚከሰትበት ጊዜ ሰዉነታችን በጣም ጥቂት የደም ሴሎች ማምረት ወይም የደም ሴሎቻችን በትክክል ተግባራቸውን መወጣት ሲያቅታቸው ሲሆን በሁለቱም አጋጣሚዎች የደም ማነስ ይከሰታል፡፡ ቀይ የደም ሴሎች ችግር ይኖርባቸዋል ወይም በቁጥር ይቀንሳሉ የዚህ ምክንያት ጤናማ ያልሆኑ የደም ሴሎች ሲኖሩ ወይም ተግባራቸውን በብቃት ለመወጣት የሚያገለግሉ ሜኔራሎችና ቫይታሚኖች እጥረት ሲኖር ነው፡፡

ለዚህ አይነቱ የደም ማነስ መነሻ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦
ሲክል ሴል የደም ማነስ(አኒሚያ)
በብረት እጥረት የሚመጣ የደም ማነስ
በቫይታሚን እጥረት
በመቅኒ እና አባት/መነሻ ሴል ችግር
ሌላ የጤና ችግሮች ናቸው።

በሲክል ሴል የሚከሰት የደም ማነስ በዘር የሚተላለፍ ሲሆን ቀይ የደም ሴሎች የጨረቃ ቅርጽ እንዲኖራቸው ያደርጋል ስለዚህ በቂ ኦክስጂን ወደተለያዩ አካሎች ማድረስ ያቅተዋል፡፡ የጨረቃ ቅርጽ ያላቸው የደም ሴሎች በጥቃቅን የደም ቧንቧዎች ውስጥ ይቀረቀራሉ ይህም ህመም ያስከትላል፡፡ በብረት እጥረት ምክንያት የሚከሰተው የደም ማነስ ብረት በተባለው ሚኒራል እጥረት ሲኖር ነው፡፡ በአጥንታችን ውስጥ ያለው መቅኒ ኦክስጂን ወደተለያዩ የሰውነት ክፍል የሚደርደውን ሄሞግሎቢን ለመስራት ብረት ያስፈልገዋል፡፡ በቂ የሆነ የብረት ሜኔራል ከሌለ በቂ የሆነ ሄሞግሎቢን አይመረትም የዚህ ውጤት በብረት እጥረት የሚከሰት የደም ማነስ ነው፡፡

የዚህ አይነቱ የደም ማነስ መነሻ ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው፦
የብረት እጥረት ያለባቸው ምግቦችን የመመገብ ዘይቤ
እርግዝና እና ማጥባት የእናትን የብረት ክምችት መጠን ይቀንሳል
የወር አበባ
በተደጋጋሚ የደም ልገሳ ማድረግ
ከባድ ስፖርታዊ ልምምዶች
የምግብ መፍጨት ችግሮች
አንዳንድ መድሃኒቶች በቫይታሚን እጥረት የደም ማነስ የሚከሰተው በቫይታሚን ቢ 12 እና ፎሌት እጥረት ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ቫይታሚኖች ቀይ የደም ሴሎችን ለመስራት ያገለግላሉ፡፡

★ ለዚህ ችግር መነሻ ምክንያቶች!

ሜጋሎብላስቲክ አኒሚያ፡ የቫይታሚን ቢ12 እና ፎሌት እጥረት
ፐረንሸስ አኒሚያ፡ የቫይታሚን ቢ12 በጨጓራ የመመጠጥ ችግር ነው
የምግብ እጥረት፡ ትንሽ ስጋ ወይም ሙሉ ለሙሉ ስጋ አለመመገብ
እርግዝና፣ አንዳንድ መድሃኒቶች፣ የአልኮል ሱሶች፣ የአንጀት በሽታዎች አፕላስቲክ አኒሚያ፡ አባት(መነሻ)ቀይ የደም ሴሎች በቁጥር ሲቀንሱ ነው።
ታላሲሚያ የሚከሰተው ቀይ የደም ሴሎች በትክክል መብሰል እና ማደግ ሲያቅታቸው ነው
ሊድ ለተባለው መርዛማ ማዕድን መጋለጥ የአጥንት መቅኒ እንዲጎዳ ያደርገዋል።

በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰት የደም ማነስ መነሻው ለቀይ የደም ሴሎች ምርት የሚጠቅሙ ሆርሞኖች እጥረት ሲሆን በዚህ አይነት ምክንያት የሚከሰቱት የሚከተሉት ናቸው::
ከባድ የኩላሊት በሽታ
የታይሮይድ እጥረት
የተለያዩ በሽታዎች(ስኳር፣ ካንሰር፣ ሪህ፣ ኢንፌክሽን)
የእድሜ መግፋት።

3. በቀይ የደም ሴሎች ውድመት/ጥፋት የሚከሰት ደም ማነስ !

ቀይ የደም ሴሎች በሚሰባበሩበት ጊዜ እና የደም ዝዉዉር ውጥረት መቋቋም ሲያቅታቸው ያለ እድሜያቸው ይፈነዳሉ ከዚያም ሄሞላይቲክ አኒሚያ ይከሰታል፡፡ ይህ ችግር ስንወለድ ወይም ካደግን በኃላ ሊከሰት ይችላል አንዳንድ ጊዜ መነሻ ምክንያቱ አይታወቅም፡፡

መልካም ጤንነት!!!
https://t.me/jossiale2022
1.3K viewsኢንፎ ሄልዝ ሴንተር Info Health Center (IHC), 14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 17:38:46

3.8K viewsኢንፎ ሄልዝ ሴንተር Info Health Center (IHC), 14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 22:09:53 #በሴት_ብልት_ጋዝ_የመውጣት_ችግር_አጋጥሞታል?


• የሴት ብልት ጋዝ ወይም “queefing” ማለት አየር በሴት ብልት ውስጥ ሲገባ ነው ፡፡ ብዙውን ጊዜ በሴት ብልት ውስጥ የተወሰነ አየር አለ ነገር ግን ብዛት ያለው አየር ሲገባ ጋዝ ሊከሰት ይችላል፡፡

• አንዴ አየር ከገባ በኋላ በመጨረሻ ከሴት ብልት ይወጣል ይህ በተለምዶ የተለመደ ክስተት ነው ብዙም ጊዜ ከባድ የጤና እክል ምልክትም ላይሆን ይችላል።

#የሴት #ብልት #ጋዝ #መንስኤዎች
#የሴት ብልት ጋዝ ሊያስከትሉ የሚችሉ የተለያዩ ነገሮች አሉ፡፡ አንዳንዶቹን በሕክምና ባለሙያ ማነጋገር ስለሚያስፈልጋቸው የተለያዩ ምክንያቶችን ማወቅ አስፈላጊ ነው ፡፡ ከእነዚህ ምክንያቶች መካከል፡-
የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎችን (መሳሳብ ወይም መወጣጠር)
በማህፀን ምርመራዎች ወይም ሂደቶች ወቅት
የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ ምርቶች
በጾታዊ ግንኙነት ወቅት
የብልት ወለል ችግር
የሴት ብልት ፊስቱላ ፡- የሴት ብልት ፊስቱላ በሴት ብልት እና በሌላ የውስጥ የሆድ ወይም የሆድ ክፍል መካከል ያልተለመደ ፣ ባዶ ቀዳዳ ክፍተት ሲፈጠር ነው ፡፡ ይህም ከጾታዊ ግንኙነት እንቅስቃሴ ጋር በቀጥታ የማይገናኝ ለሴት ብልት ጋዝ መከሰት መንስኤ ነው፡፡ የተለያዩ አይነት የሴት ብልት ፊስቱላዎች አሉ ፡፡ ፊስቱላ በሕክምና ባለሙያ መፍትሄ አግኝቶ መታከም አለበት ፡፡
#የሴት #ብልት #ጋዝ #ለመከላከል
#የሴት ብልት ጋዝ የውጥረት ውጤት ከሆነ ዘና ለማለት መሞከር እና በጥልቀት መተንፈስ ሊረዳ ይችላል:: የሴት ብልት ጋዝ በሚበዛበት ጊዜ የጾታ ግንኙነት እና የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ያስወግዱ፡፡ ወደ ማህፀን የሚገቡ የሴት ንፅህና መጠበቂያ ምርቶችን አለመጠቀም አደጋን ለመቀነስ ይረዳል። ሆኖም ግን መንስኤውን ሊያስተካክሉ የሚችሉ ህክምናዎች እና የቀዶ ህክምና ሂደቶች አሉ ፡፡
https://t.me/jossiale2022
4.7K viewsኢንፎ ሄልዝ ሴንተር Info Health Center (IHC), 19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 22:03:43 Watch "የሪህ በሽታ ምንነት፣ ምልክት፣ ህክምናና መከላከያዎቹ" on YouTube


4.4K viewsYoseph Alebachew, 19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 09:16:13 Watch "በዘር የሚተላለፉ የተለያዩ በሽታዎች አሉ። እነርሱን በማወቅ ሊጠነቀቁ ይገባል። ይመልከቱትና ይወቁዋቸው። ሰብስክራይብ ያድርጉ!!!" on YouTube


4.9K viewsኢንፎ ሄልዝ ሴንተር Info Health Center (IHC), 06:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 19:55:00 Watch "የኮሶትል ምንነት፣ ምልክት፣ መተላለፊያ መንገዶች፣ ህክምናውና መከላከያ መንገዶቹ" on YouTube


5.1K viewsYoseph Alebachew, 16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 18:05:13 Watch "መደመጥ ያለበት የኩላሊት በሽታዎችን በተመለከተ የቀረበ" on YouTube


4.9K viewsኢንፎ ሄልዝ ሴንተር Info Health Center (IHC), 15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 20:36:58 #መዋጥ #መቸገር (#Dysphagia)
#ከወደዱት #ያጋሩት

ምግብ አኝከዉ ሲዉጡ ወይም ፈሳሽ ሲጠጡ ጨጓራዎ ጋ መድራስ ያለበት ያለምንም ችግር መሆን አለበት። ነገር ግን የጎረሱት ምግብም ይሁን የተጎነጩትን ፈሳሽ ለመዋጥ የሚቸገሩ ከሆነ አሊያም ምግቡ ጨጓራዎ ጋ ለመድረስ ብዙ ሰዓት ከወሰደ የመዋጥ ችግር አለዎ ማለት ነዉ። ይህ ችግር ካለ ምግብ ሲዉጡ ህመም ሊኖር ይችላል። አንዳንዴም ምግብ ጭራሹኑ አልዋጥም ሊል ይችላል።

አንዳንዴ ምግቡን በችኮላ አሊያም በደንብ ሳያኝኩ ሲዉጡ የመዋጥ ችግር ሊገጥሞዎ ይችላል። ይህ ሁኔታ ሲኖር በጭራሽ ሊያሳስብዎ አይገባም።ምክንያቱም ችግሩ ግዜያዊ ስለሆነ።

የመዋጥ ችግር በየትኛዉም የእድሜ ክልል ሊከሰት የሚችል ቢሆንም በብዛት በእድሜ በገፉ ሰዎች ላይ ይከሰታል።

የህመም ምልክቶች

ከመዋጥ ችግር ጋር ሊገናኙ የሚችሉ የህመም ምልክቶች ዉስጥ፡

ምግብ ሲዎጡ ህመም መኖር
መዋጥ አለመቻል
ምግብ ከዋጡ በኃላ በጉሮሮ፣ በደረት ላይ ወይም ከጡት አጥንት ጀርባ (sternum) የቆመ ወይም ተወትፎ የቀረ ስሜት መኖር

የምራቅ መንጠባጠብ
የድምፅ መጎርነን
የወጡት ምግብ እንደሚያመነዥኩ እንስሳት ወደኃላ መመለስ
በተደጋጋሚ ቃር መከሰት
የሰዉነት ክብደት መቀነስ
ምግብ ሲዉጡ ማሳል ወይም የማስታወክ ስሜት መኖር (gagging)

አጋላጭ ምክያቶች

እርጅና፦ በተፈጥሮ የእድሜ መግፋት ወይም እርጅና ምክንያትና በእድሜና አገልግሎት ብዛት የተነሳ የጉሮሮ ጡንቻዎች መላሸቅ ምክንያት አሊያም ከነርቭና ከፓርኪንሰን ህመም ጋር በተገናኘ በሚፈጠር ችግር በእድሜ የገፉ ሰዎች ለመዋጥ ችግር ይበለጥ ተገለጭ ናቸዉ።

የተወሰኑ የህመም ችግሮች መኖር፦ አንዳንድ የነርቭ ወይም የነርቭ ሥርዓት መዛባት ችግር ያለባቸው ሰዎች ብዙውን ጊዜ ለመዋጥ ይቸገራሉ።

st urael clinic
https://t.me/jossiale2022
5.4K viewsYoseph Alebachew, edited  17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 20:28:52 https://vm.tiktok.com/ZMNyttbd9/
4.3K viewsYoseph Alebachew, 17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ