Get Mystery Box with random crypto!

#በቂ_ፋት_እያገኙ_እንዳልሆነ_የሚያሳዩ_ምልክቶች ፋት ያለባቸው ምግቦች ብዙውን ግዜ በመልካም ጎኑ | Info Health Center (አይ ኤች ሲ የጤና ማዕከል, IHC Health and Wellness Consultation Center )

#በቂ_ፋት_እያገኙ_እንዳልሆነ_የሚያሳዩ_ምልክቶች

ፋት ያለባቸው ምግቦች ብዙውን ግዜ በመልካም ጎኑ ስማቸው ሲነሳ አይሰማም። ነገሩ እንዳለ ሆኖ ግን ፋት ያለበት ምግብ መመገብ ብቻውን የሰውነት ክብደታችን ያለመጠን እንዲጨምር አያደርግም። በአግባቡ እስከተመገብን ድረስ።

ሰውነታችን በተፈጥሮው ፋት ይፈልጋል። ሰውነታችን የሚፈልገውን የፋት መጠን በአግባቡ ካልሰጠነው በጤናችን ላይ የራሱ የሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ ያስከትላል። ሰውነታችን በቂ መጠን ያለው ፋት ሳያገኝ ሲቀር የሚከሰቱ ምልክቶች አሉ። ከእነዚህ ምልክቶች መካከል የሚከተሉት አምስቶቹ ዋነኞቹ ናቸው።

1. የቫይታሚን እጥረት (Vitamin deficiencies)

እንደ ቫይታሚን ኤ፣ ዲ፣ ኢ እና ኬ (A, D, E & K)የመሳሰሉ የቫይታሚን አይነቶች በፋት የሚሟሙ (fat soluble vitamins) ይባላሉ። ሰውነታችን እነኚህን ቫይታሚኖች መጦ ለመጠቀም የፋት ይዘት ያላቸው ምግቦችን ማግኘት ይፈልጋል። ይህ በማይሆንበት ግዜ የእነዚህ ቫይታሚኖች እጥረት ሰውነታችን ይገጥመውና ለሚከተሉት የጤና እክሎች ልንጋለጥ እንችላለን:-

በምሽት ለማየት መቸገር (night blindness)
የጸጉር ድርቀት (dry hair)
መሃንነት (infertility)
የጡንቻ ህመም (muscle pain)
ድብርት (depression)

2. የቆዳ መቆጣት (Dermatitis)

የኤን ሲ ቢ አይ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ፋት የቆዳ ጤንማነት ላይ ትልቅ ድርሻ አለው። በቂ የሆነ ፋት ካላገኘን ሰውነታችን ዴርማቲቲስ ለተባለው ለቆዳ መቆጣት በሽታ የመጋለጥ እድላችን ሰፊ ነው።

3. የቁስል በቶሎ ያለመዳን

በፋት እጥረት ምክንያት እንደ ቫይታሚን ኤ እና ዲ የመሳሰሉ ቫይታሚኖች እጥረት ሊከሰት ይችላል። ይህም እነኚህ ቫይታሚኖች በቁስል በቶሎ መዳን ላይ ያላቸውን ሚና ስለሚያሳጣን የቁስል በቶሎ ያለመዳን ችግር ሊከሰት ይችላል።

4. የጸጉር መነቃቀል

ፕሮስታግላንዲንስ (Prostaglandins) የተባሉ የፋት ሞለኪውሎች በጸጉር እድገት እና ጤናማነት ላይ ትልቅ ድርሻን ይጫወታሉ። በቂ ፋት ያለመመገብ ይህን ፋቲ ሞሎኪውል በበቂ መጠን እንዳናገኝ ስለሚያደርግ ለጸጉር ወዝ ማጣት እና የመነቃቀል ችግር ሊያጋልጠን ይችላል።

5. ተደጋጋሚ ህመም

በበቂ መጠን ፋት ያለማግኘት ሰውነታችን ሊኖረው የሚገባውን የበሽታ መከላከል አቅም (Immunity) ይጎዳል። ሰውነታችን በሽታን የመከላከል አቅሙን ለማደበር ከሚፈልጋቸው ነገሮች ውስጥ አንዱ ፋት ነው። ይህም በመሆኑ በቂ ፋት አለመመገብ ደካማ የበሽታ መከላከል ስረዓትን በማዳከም በቀላሉ ለበሽታዎች የምንጋለጥበትን እድል ይፈጥራል።

ጤናማ ፋት ያላቸው ምግቦች የትኞቹ ናቸው?

ፋት መመገብ ሲባል የግድ ጮማ ስጋ መቁረጥ ማለት አይደለም። በቀላሉ የፋት ይዘት ልናገኝባቸው ከምንችልባቸው ምግቦች መካከል የሚከተሉት ይጠቀሳሉ:-

አቮካዶ
እንቁላል
አሳ
ለውዝ
እርጎ
ኦሊቭ ኦይል

መልካም ጤንነት!!
#በአካል_ቀርበው_ቢያገኙን_እፎይታን_ያገኛሉ።
ለቀጠሮ ማስያዣ ስልክ ቁጥር = 0921785903

#ጎተራ_ራሚ_ህንፃ_4ኛ_ፎቅ_ቢሮ_ቁጥር_402

1. የዩቲዩብ አድራሻ = https://youtube.com/channel/UCM2HMbAuepuSrLQGVvhLUHw?sub_confirmation = 1
2. የቴሌግራም አድራሻ = https://t.me/jossiale2022
3. የቲክቶክ አድራሻ = tiktok.com/@infohealthcenter
4. የፌስቡክ አድራሻ = https://www.facebook.com/yosef.alebachew.9
5. የፌስቡክ ፔጅ =https://www.facebook.com/profile.php?id=100064131361093