Get Mystery Box with random crypto!

#Ethiopia | በትግርኛ ዘፈኑ፤አክሱማዊት የተሰኘ ሙሉ አልበም አውጥቷል። ባባ ኢለን፣ ዘዊደሮ | Adey job zone

#Ethiopia | በትግርኛ ዘፈኑ፤አክሱማዊት የተሰኘ ሙሉ አልበም አውጥቷል። ባባ ኢለን፣ ዘዊደሮ፣ ወዛመይ፣ ቸኮላታ፣ ኣጆኺ ትግራይ፣ ደስ ይበለኒ'ሎ፣ ቕዱስ ፀባያ የተሰኙ ሥራዎቹ በሕዝብ ዘንድ የሚታወቁ ነጠላ ዜማዎቹ ናቸው -ይህ ድምፃዊ ዳዊት ነጋ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

አዲስ ህይወት ሆስፒታል ደረስኩ።

የሆስፒታሉ በር፣ ግራ እና ቀኝ ቤተሰቦቹ ፣ ወዳጆቹና አድናቂዎቹ ተሰብሰበው ያለቅሳሉ።

ለቅሷቸው በጣም ይረብሻል፣ ያስለቅሳል።

ግቢው ድንጋጤ ባረበበባቸው ሰዎች ተጨናንቋል።

አርቲስት ዳዊት ነጋ #Dawit Nega ህመም አጋጥሞት ያለፉትን ቀናት በአዲስ ህይወት ሆስፒታል በበጽኑ ሕክምና ላይ ነበር።

አርቲስት ዳዊት ነጋ (ሰላምተኛዬ) የሙዚቃ ሥራዎቹ የትግርኛ ቋንቋ ከሚያደምጡ ሰዎች ባለፈ ቋንቋውን በማያቁትም ዘንድ እጅግ ተወዳጅ የነበሩ ናቸው። ሙዚቃ የዓለም ቋንቋ ነው የሚባለውም ለዚህም ነው።

ከሙዚቃ ሥራዎቹ መካከል ፦ ባባ ኢለን፣ ዘዊደሮ፣ ወዛመይ፣ ቸኮላታ፣ ኣጆኺ ትግራይ፣ ደስ ይበለኒ'ሎ፣ ቕዱስ ፀባያ የሚባሉት ይጠቀሳሉ።

አርቲስት ዳዊት ነጋ ባለትዳር እና የአንድ ልጅ አባት ነበር።

ለወዳጅ ዘመዶቹና የቅርብ ቤተሰቦቹ ልዑል እግዚአብሔር መጽናናትን ይስጥልን። እንወድሃለን


--ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን---



ነፍስህ በሰላም ትረፍልን