Get Mystery Box with random crypto!

አትጨነቁ ትናትናችሁን አልፋችሁ  መታችኋል ።መከራ     ችግር           ረሀብ    | Jehovah jireh 🇪🇹

አትጨነቁ

ትናትናችሁን አልፋችሁ  መታችኋል ።መከራ
    ችግር
          ረሀብ
             ህመም
                    ማጣት
እነዚንህም በህይወታችሁ አሣልፋችሁ ይሆናል
      ነገር ግን
ትናትናን መመለስ አትችሉም
ማነው ?
እደገና በማህፀን ገብቶ መወለድ የሚችል ማነው ከ25ዓመት ወደ ወደ ለጋነት 14አመት ሚመለስ ማነው ከ45ዓመት ወደ ወጣትነት 22ዓመት ሚመለስ ማነው ከ80ዓመት ወደ 40ጎልማሣነት ሚመለስ ማንም  የለም
      ሁላችንም ምንኖረው
ከተሠጠን ወደ ኋላ ካለን ወደፊት ነው ። ስለዚህ ትናትን አልፋቹታል በቃ ስለምን ትጨነቃላችሁ
           እንደዚያውም
ነገን ማየት አትችሉም
        በርግጥ
ለ ነገ ተስፋ
         ህልም
    እቅድ
   ይኖረን ይሆናል
እንደውም  ሁላ ለ ነገስ ብለን
         የምበላውን
        የታክሲ  ብራችንን
ልብሶቻችንን እናሠናዳለን
       ምክንያቱም
   ተስፋ ሚባል ነገር አለና
ግን ብዞች ለነገ ብለው አስቀምጠው
      ያስቀመጡት እደተቀመጠ ቀርተዋል ።
       ይህን ስል ደግሞ ለነገ አታስቡ እያልኩ አይደለም፣
      ግን አታውቁትም
በሁለት ነገር ላይ ነው ምንኖረው
     ወይ በዘውድ
     ወይ በጎፈር
ወይ ይነጋል
ወይ ላይነጋ ይመሻል
     የተፈቀደለት ይኖራል
የጨረሠ ይሄዳ ስለዚህ ነገን አታውቁትም እና አትጨነቁ
           ግን አንድ ተስፋ ልስጣችሁ
            ዛሬ የእኛ
ናት እና እንኑራት
                በዚች ቀን
         ምንደሠትበት
          ምንከባበርበት
         ይቅር ምንባባልበት
        ንሠሀ ምንገባበት
       ተካፈለን ምንኖርበት
        የታመመን ምጠይቅበት
       ምናገባበት ምንወልድበት
       ተረኛን ምሸኝበት
ቀን ነው ነገ አይደለም 
          ዛሬ የኛ ነው
እንኑረው አትጨነቁ 
          ነገ አይታወቅም
      መኪና ያለ መሪ አቅጣጫ
      እደማይጠቁም
     እኛም ያለ ፈጣሪ
       ወዴትም  መሄድ አንችል
እኛ የኛ ሣንሆን የአምላክ ነን
         የፈለገው ጊዜ ስለሚወስደን
ደስ ካለው ስለሚያኖረን በተሠጠን
ዛሬ ላይ ያለ ጭንቀት እንኑር ።
                   አትጨነቁ አሜን (Amen)
https://t.me/jjkasen