Get Mystery Box with random crypto!

ማኅበረ ቅዱሳን በምዕራብ ማእከላት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስተባባሪነት በጅማ ሀገረ ስብከት ከሐምሌ | የጅ/ዩ/ቴ/ኢ/ግ/ግቢ ጉባኤ [Y/M/M/Y/I/T/Jimmaa]

ማኅበረ ቅዱሳን በምዕራብ ማእከላት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስተባባሪነት በጅማ ሀገረ ስብከት ከሐምሌ 16 እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ሲያሠለጥናቸው የቆዩ የግቢ ጉባኤያት ደረጃ - 2 ተተኪ መምህራን ሰልጣኞችን በዛሬው ዕለት ነሐሴ 15 ቀን 2014 ዓ.ም በጅማ መንበረ ጵጵስና ደብረ መዊዕ መድኃኔዓለም ወማኅደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን ካህናት አባቶች፣ የማኅበረ ቅዱሳን ጅማ ማእከል አባላት እና በርካታ ምእመናን በተገኙበት  አስመርቋል።

ማስተባበሪያ ጽ/ቤቱ  በዛሬው ዕለት በምዕራብ ማእከላት ሥር ከሚገኙ 6 ማእከላትና 13 ግቢ ጉባኤያት የተውጣጡ 29 የደረጃ 2 ተተኪ መምህራን ሠልጣኞችን ያስመረቀ ሲሆን በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የጅማ መንበረ ጵጵስና ደብረ መዊዕ መድኃኔዓለም ወማኅደረ ስብሃት ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ እና የማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቭዥን አምባሳደር መልዐከ መዊዕ ቆሞስ አባ አብርሃም ለተመራቂዎቹ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት እና የአደራ ቃል አስተላልፈዋል።