Get Mystery Box with random crypto!

ዮሀ 21:13  ' እነርሱም፦ አንቺ ሴት፥ ስለ ምን ታለቅሻለሽ? አሉአት። እርስዋም፦ ጌታዬን ወስደ | #Fire🔥 Embassy Girum Révíväll🇪🇹🔥🔥

ዮሀ 21:13  " እነርሱም፦ አንቺ ሴት፥ ስለ ምን ታለቅሻለሽ? አሉአት። እርስዋም፦ ጌታዬን ወስደውታል ወዴትም እንዳኖሩት አላውቅም አለቻቸው "

ግን ግን ግን..... አንድ ናፍቆት አለኝ። አንድ እጅግ ፈላጊ እና ጠያቂ ትውልድ ቢነሳ!!!!!!!!!

ጌታዬን ወዴት አኖራችሁት ብሎ ሚጠይቅም፤ ሚሞግትም!!!!!!
ከሸበረቀ መድረክ ፣ በተለያዩ የቀለም ብርሃናት ከተንቆጠቆጠ፣ በጭስ በታፈነ፣  እጅግ ብዙ ህዝብ ከታደመበት ፣ ታኣምራዊ ዝላይ ከሚታይበት ፣ ከ ' ሊዊ ቪቶ እስከ ፔሬሊዝ ' የልብስ እና ጫማ ፋሽን ከሚታይበት ፣ ከ ' ዲዮር እስከ ቶም ፎርድ ' የሽቶ ጠረን ካወደበት ፣ ድንቅ ድንቅ የንግግር ችሎታ ከሚታይበት፣ ግጥማዊ ስብከት እና ቃና ከሚሰማበት ፣ ስንት አገር እንደተዞረ እና ስንት ታዋቂ ሰው እንደተዋወቀ ከሚነገርበት ፣ " እውቀት " የተባሉ ከሚፈሱበት ፣ ድንቅ እናሳያችሁ ብለው ' ሾው ታይም' ተብሎ ከሚጀመርበት................ ብቻ ብቻ ብዙ ብዙ ብዙ ትርምስ መካከል................

"ኢየሱሴስ?" ብሎ የሚጠይቅ ፤ "ጌታዬን ወዴት አኖራችሁት?"  የሚል ጀግና ትውልድ ተነስቶ ማየት ረሀቤ ነው።
ያለ እርሱ ናፍቆት የሌለው ፣ እርሱ ማእከል ካልሆነ የማይጥመው፣ ናፍቆቱም ጥማቱም እርሱ የሆነለት፣ መነሻውም መድረሻውም እርሱ የሆነለት። በክርስቶስ ፍቅር የሰከረ፣ በንግግሩም በኖሩውም የጨከነ ትውልድ ማየት ናፍቆቴ ነው። መንፈስ ቅዱስን አሁንም አሁንም የሚጠማ  እና ልዩነቱን የሚረዳ ቢበዛ ደስ አይልም  አሁንም ስላሉን ቅሬታዎች እግዚአብሔር ይባረክ።

ማስታወሻ፡- ከላይ ከዘዘዝርኳቸው መካከል አንዳንዶቹ በራሳቸው ክፉ ናቸው እያልኩ እንዳልሆነ ከግምት ይግባልኝ።
#እናንተ ለበረከት ናቹ

@jesussssssssssssss
@jesussssssssssssss