Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ የካቲት23 ልደቴ ነው በዚ ታሪካዊ ቀን የአድዋ በአል መወለዴ ደስተኛ ነኝ እኔ ለሀገሬ ታ | #Fire🔥 Embassy Girum Révíväll🇪🇹🔥🔥

ዛሬ የካቲት23 ልደቴ ነው
በዚ ታሪካዊ ቀን የአድዋ በአል መወለዴ ደስተኛ ነኝ እኔ ለሀገሬ ታሪክ አውሪ ብቻ ሳልሆን ወንጌል አብሳሪ ነኝ!! ሀገሬ ተስፋ አላት!!ኢትዮጲያዬን ሳስብ ደስታ እና ኩራት ይሰማኛል። በዚ ቀን መወለድ ማለት ትልቅ እድል ነው! ሰማይ ያሰበው የመለኮት እቅድ ስለ ሆነ እንደገና የሰማይ አርበኛ እንድሆን ነው እሪቫይባሉ እንዳን ቀሳቅስ የተጠራው መሆኔ ሳስብ ደስታ ይለኛል ለምን ብትሉ እግዚአብሔር ያለኝ ትልቅ ነገር አለኝ የመጣሁበት መንገድም ነግሮኝል።

“ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።”
  — መዝሙር 139፥14
ይህ ቃል የእኔ ነው!! ያልኩበት ምክንያት አለኝ
#የስምት ወር ልጅ አያድግም በሳይንስ ቃል ካለብህ ግን ትኖራለህ እኔ ምስክር ነኝ!
#እናቴ እኔን እርጉዝ ሆና ክፍላገር ለአገልግሎት ከአባቴ ጋር ሲሄዱ ወንዝ ሱሻገሩ ወንዝ ይዞን ሄደ ከዛም ተረፍኩ!
#ከዛ ተርፋ እኔን በሆዶይዛ ደግሞ ከባድ አወዳደቅ ወደቀች ፅንሱ ይጎዳል ሲባል ምንም ሳልሆን በ8ወሬ በሰላም ተወለድኩ
#እግዚአብሔር ደግሞ የእኔ አርበኛ ነህ ብሎ በአርበኝች ቀን ነው ወደምድር የምትመጣው አለኝ ጌታ ስሙ ይባረክ

እኔ እግዚአብሔር ከህፃንነቴ ጀምሮ በህይወቴ የሚታይ የማይካድ ነገር ነው በከፍታዬም በዝቅታዬም፣በድካሜ ለአንድ ደቂቃ ያልተውኝ የኔ ጌታ ሁሌም የጌታዬ መንፈስ ያፅናኝል ያበረታኛል እኔ ላይ ከባድ ኪዳን አለ!!

ዛሬ ደስ የሚል ቀን ነው በተለይ ለእኔ
#ምስጋና፦በመጀመርያ አስደናቂ ምህረቱን በእኔ ላይ ለአ በዛልኝ ለእግዚአብሄር እድሜን እና ጤናን በመውጣት በመግባት ከእኔ ጋር ለነበረ ለእግዚአብሄር ምስጋና ሰዋለሁ
ፈጣሪ ሀገራችንን ይባርክ
መልካም ቀን ይሁንልን