2021-10-27 09:19:07
ኢየሱስ አማላጅ ነው!!!" የ ኢየሱስ ምልጃ በ መፅሐፍ ቅዱስ " "ክፍል አንድ"
ምልጃ ማለት በሁለት አካላት መካከል ባለ ጠላትነት ወይም በተፈጠረ አለመስማማት በሌላ ሶስተኛ ወገን የሚቀርብ ፀሎት ፣ልመና እና የማስታረቅ ክንውን ነው።
ምልጃ በ በዳይ እና በ ተበዳይ አካላት የተፈጠረን ግጭት ለመፍታት ሌላ ሶስተኛው ወገን በ በዳዩ ስም ተበዳዩን የሚለምነው ልመና ነው።
አማላጅ ማለት ደግሞ በሁለት የተጣሉ፣ የተራራቁ፣ የተቀያየሙ አካላት መካከል ገብቶ እርቅን ለማምጣት ወይም ለማስታረቅ ምልጃን የሚያቀርብ ነው።
ኢየሱስ አማላጅ ነው ወይም ያማልዳል ሲባል በ ሰው እና በ እግዚአብሔር መካከል የነበረውን ጠላትነት ለመሻር ፣የሰውን ልጅ ከ እግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ ፀሎትን ፣ ልመናን እና ምልጃን የራሱን ደም በማፍሰስ አቅርቦለናል ማለት ነው ።
የ ኢየሱስ ክርስቶስ ምልጃ በ መፅሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ከ ብሉይ ኪዳን ጀምረን እስከ አዲስ ኪዳን ያሉትን ከዚህ በታች እንመልከት:-
1). “ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።”
— ኢሳይያስ 53፥12
ነብዩ ኢሳያስ ከ ኢየሱስ ልደት ሰባት መቶ ዓመት አስቀድሞ ስለ ኢየሱስ ምልጃ ተናግሯል።
ኢሳያስ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ ማለቱ ሃጥያተኞች ሳለን አመፃችንን እንዳይቆጥርብን ወደ እግዚአብሔር ለመነልን ።( ሉቃ 23:34)
" ማለደ " የሚለው ቃል የ ዕብራይስጥ አቻው (יַפְגִּֽיעַ׃) ወይም (yap̄-gî-a‘) የሚል ነው ትርጉሙም አማለደ ማለት ነው።
የ እንግሊዘኛ አቻውም ( made intercession ) የሚል ነው ትርጉሙ ምልጃን አደረገ ማለት ነው።
2).
ኢሳይያስ 59
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ እውነትም ታጥቶአል፥ ከክፋትም የራቀ ሰው ለብዝበዛ ሆኖአል። እግዚአብሔርም አየ ፍርድም ስለሌለ ተከፋ።
¹⁶ ሰውም እንደሌለ አየ፥ ወደ እርሱ የሚማልድ እንደሌለ ተረዳ ተደነቀም፤ ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድኃኒት አመጣለት፥ ጽድቁም አገዘው።
.እግዚአብሔር አምላክ ወደርሱ ምልጃን ሊያቀርብ የሚችል ማንም ሰው እንደሌለ በተረዳ ጊዜ የገዛ ክንዱ (ኢየሱስ ) መድሃኒት አመጣለት አማላጅም ራሱ ልጁ ሆነለት።
3 ).“በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።”
— ዮሐንስ 1፥29
ዮሐንስ ኢየሱስን የ እግዚአብሔር በግ ያለበት ምክንያት በ ሙሴ ሕግ ለ ሀጥያት ስርየት የሚሆነው ከ መንጋው በጎች በደል የሌለበት በግ ስለሆነ ነው
ዘሌዋውያን 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁷ ማናቸውም ሰው ኃጢአት ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፍ፥ ባያውቅም፥ ያ ሰው በደለኛ ነው፥ ኃጢአቱንም ይሸከማል።
¹⁸ ነውር የሌለበትን አውራ በግ ከመንጋው ለበደል መሥዋዕት እንደ ግምጋሜህ መጠን ወደ ካህኑ ያመጣዋል ካህኑም ሳያውቅ ስለ ሳተው ስሕተት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።
¹⁹ እርሱም የበደል መሥዋዕት ነው፤ በእውነት በእግዚአብሔር ፊት በደለኛ ነው።
ስለዚህ ኢየሱስ ለ ምልጃ የሚቀርብ የ አዲስ ኪዳን በግ ነው ስለታረደም አማለደን።
4).ሉቃስ 22
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³¹ ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤
³² እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ።
.ጌታ ራሱ ስለ አንተ አማለድኩ ብሎ እንዳማለደ በራሱ አፍ ተናግሯል።
."አማለድሁ" የሚለው የ ግሪክ ተመሳሳይ ፍቹ "ἐδεήθην" ወይም " edeēthēn"(ኤዴቴን ) የሚል ሲሆን ቀጥተኛ ፍቺው "መለመን "የሚል ነው።
5).ሮሜ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³³ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው?
³⁴ የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።
. እዚህ ላይ ጳውሎስ ራሱ" ስለኛ የሚማልደው "ብሎ ኢየሱስ እንደሚያማልድ እና በ ምልጃዉም ጳውሎስ ራሱ ተጠቃሚ እንደሆነ ነግሮናል ።
."የሚማልደው" የሚለው ቃል አገላለፁ አንድ ጊዜ ብቻ ተደርጎ ስለምያበቃ ምልጃ ሳይሆን ቀጣይነት ስለሚኖረው ምልጃ መሆኑን ያሳያል ።
. "የሚማልደው " የሚለው ቃል የ ግሪኩ ተመሳሳይ ቃሉ " ἐντυγχάνει" (ኢንቱግካኖ)
የሚል ነው ትርጉሙም የሚያማለድ ወይም አማላጅ ማለት ነው ።
. እንግሊዘኛውም " interceding" ይላል አማላጅ ማለት ነው ።
የ ግዕዙ ቃል ደግሞ "ወይትዋቀስ በ እንቲአነ " ይላል ትርጉሙም ስለኛ ይከራከራል የሚል ነው ይህም ምልጃውን የሚያሳይ ነው።
6).
ዕብራውያን 7
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²³ እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤
²⁴ እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤
²⁵ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።
. ጳውሎስ በሚገርም ሁኔታ የ ኢየሱስን ምልጃ ሲያስረዳ ምልጃው ያለፈ እና ከዚህ በኃላ የማይሰራ አድርገን እንዳናስበው ሲል "ሊያማልድ" ብሎ ነው ቀጣይነቱን የገለፀው።
. እዚህ ላይም "ሊያማልድ " ለሚለው ቃል በ ግሪኩ " ἐντυγχάνειν " ( ኢንቱግካኖ ) የሚል ነው ( to intercede ) ይህም ምልጃውን ሚናገር ቃል ነው ።
. እዚሁ ቃል ላይ ማወቅ ያለብን ነገር የ ኢየሱስ ምልጃ ከ ብሉይ ኪዳን ካህናት የተለየ መሆኑን ነው የሚለየውም የነሱ ምልጃ የሚለወጥ እና በ ሞት የሚቋረጥ ሲሆን የ ኢየሱስ ግን ማይለወጥ እና ዘላለማዊ ነው ( ዕብ 7: 23-24)
. እዚህ ላይ " ሊያማልድ " ለሚለው ቃል ግዕዙ " ተንበለ " ይለዋል ይህም ምልጃውን ሚናገር ነው።
7).
1ኛ ጢሞቴዎስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤
⁶ ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤
. መካከለኛው ማለቱ ኢየሱስ ሰውን እና እግዚአብሔርን ለማስታረቅ በመካከል የገባ ስለሆነ ነው ።
. ኢየሱስ የ አዲስ ኪዳን መካከለኛ ያስባለው ምክኒያት ለሰው ልጆች በደል እና ሀጥያት ሲል ያፈሰሰው ደም የሚናገር፣ የሚጮህ እና የሚለምን ስለሆነ ነው ። “የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።”
— ዕብራውያን 12፥24
ይቀጥላል......
በ ወንድም ዴቭ
@jesusGtruth
Please share and follow
ጥያቄ ካለዎት https://t.me/Jesuskingofkingslordoflords
338 viewsAddis A. Robele, 06:19