Get Mystery Box with random crypto!

በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያን ዜጎች እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ ገለፁ። ጄይሉ ቲቪ ነሀሴ 1 | ጄይሉ ቲቪ // Jeilu Tv

በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጲያዊያን ዜጎች እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ ገለፁ።

ጄይሉ ቲቪ ነሀሴ 16/2014 አዲስ አበባ

ዜጎች የተሻለ ህይወትን ፍላጋ በሚል ቀያቸውን፤ ሀገራቸውን ለቀው ይሰደዳሉ፡፡

ስደት እንደ ጦርነት ዜጎችን ተስፋ አስቆርጦ ሞት ወይንም በአንፃሩ የተሻለ ህይወትን በሚሉ ሁለት ምርጫዎች አጣብቆ የሚወሰን ነው፡፡

በዚህም ስደት በአብዛኛው እንደ አፍሪካ ባሉ አህጉራት ህጋዊና ደህንነቱ የተጠበቀ ጉዞ በአያሌ ምክንቶች አይደረግም፡፡

በዚህ ሠንሰለቱ በረዘመና በስጋት በተሞላ ጉዞ በተለይም ወጣቶችና ሴቶች አስከፊ ጊዜአትን ያሳልፍሉ።

ብዙዎች ቀባሪ አጥተው በድናቸውን በርሃ በልቶታል፤ ሰብዓዊነታቸው ተገፏል፤ ተደፍረዋል፤ ጥቃት ደርሶባቸዋል፤ የውቅያኖስ እራትም ሆነዋል፡፡

ኢትዮጵያዊያንም የዚህ አንገብጋቢ የማህበራዊ ቀውስ ሰለባ ከመሆን የታደጋቸው ያለ አይመስልም፡፡

በቅርቡ እንኳን ምክንያት በሌለው ሁኔታ በሱዳን ሀገር የሚኖሩ ኢትዬጲያዊያን ዜጎች እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ እየተናገሩ ይገኛል።

ነዋሪዎቹ በተለይ ለጄይሉ ቲቪ እንደተናገሩት በሳፋ፣ ሸሪቅ፣ ባህሪ፣ እንዱርማን እና መሰል ቦታዎች ያለ በቂ ምክንያት በታጣቂዎች ታፈነው ከተያዙ በኃላ ገንዘብ ካልከፈሉ እንደማይለቋቸው ገልፀዋል።

ይህ እንግልት እና ስቃይ የተጀመረው በቅርብ ቀን መሆኑን የነገሩን ግለሰብ አቶ አይደል በሱዳን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ እስካሁን ድረስ ያደረገልን ነገር የለም ያሉን ሲሆን ከዚህ በበለጠ ግን የሱዳን ህዝብ እየተባበራቸው እንደሆነ ይናገራሉ።

ኢትዬጲያዊያኖቹ በተለይ በሳፋ፣ በሸሪቅ፣ በባህሪ፣ በእንዱርማን እና መሰል ቦታዎች ያለ በቂ ምክንያት በደል እየተፈፀመባቸው መሆኑን ጄይሉ ቲቪ ጣራው መረጃ መሰረት ለማወቅ ችሏል።

በ ሙሀመድንጉስ አብዱ