Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ ምሽት “ቬነስ እና ጁፒተር ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠጋግተው እንደሚታዩ” የህዋ ሳይንቲስቶች አስ | ልዕልት አንድሮሜዳ🌍

ዛሬ ምሽት “ቬነስ እና ጁፒተር ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠጋግተው እንደሚታዩ” የህዋ ሳይንቲስቶች አስታወቁ!

የህዋ ሳይንቲስት እና ሶሳይቲ ፎር ፖፑላር አስትሮኖሚ ውስጥ ዋና የከዋክብት ተመልካች ፕ/ር ሉሲ ግሪን ፣ ክስተቱ ለከዋክብት አጥኚዎች ብቻ ሳይሆን ለተቀረው ማኅበረሰብም አስደናቂ ብለዋል፡፡ሁለቱ ደማቅ ፕላኔቶች ዛሬ ምሽት ለመነካካት ጥቂት እስከሚቀራቸው ድረስ ነው የሚቀራረቡት።ፕላኔቶቹ በየዓመቱ የሚቀራረቡ ቢሆንም፤ ዘንድሮ ግን ከመቼውም በበለጠ የሚጠጋጉበት ነው ተብለዋል፡፡

ይህንን አይነት ክስተት እስከ ፈረንጆቹ 2039 ድረስ በድጋሚ እንደማያጋጥምም ነው የተገለጸው። ክስተቱን ዛሬ ምሽት በዐይን ወይም በአጉሊ መነጽር መመልከት እንዳሚቻልም ነው የህዋ ሳይንቲስቶች መረጃ የሚያመለክተው፡፡