Get Mystery Box with random crypto!

ድሮ ለካ ቅርብ ነው… በቤታችን መሀል አጥር አልነበረም…ድሮ እኛ ቤት ቡና ተፈልቶ ለብቻ | ✍ የሚኪያስ ደብዳቤዎች 📩📩📩

ድሮ ለካ ቅርብ ነው…

በቤታችን መሀል አጥር አልነበረም…ድሮ እኛ ቤት ቡና ተፈልቶ ለብቻ አይጠጣም…አንተ ቤት ምሳ ተሰርቶ ለብቻቹ አትበሉም ነበር ……ድሮ ሰው ሀገር ነበረው ሀገርም ሰው ነበራት…ድሮ ላይ ሰው እንደሰው ያስብ ነበር ድሮ በራችን ይዘጋ የነበረው ሲመሽ ብቻ ነበር……አሁንስ ግን?

አሁንማ ሰው ቡና አያፈላም…ቢያፈላም ለብቻው ነው…ሰው ስራ አይሰራም የተሰራውን ግን ይወቅሳል…ሰው አጥር ሰርቶል ሊያውም በጣም እረጃጃጅም……አሁን ላይ በራችን ጠዋትም ማታም ዝግ ነው…አሁን ላይ ወዳጄ ሰው ሰውነቱን ትቶል…እሚያስማማን ብዙ ነገር እያለ አለመስማማትን መርጠናል።

ድሮ ሰው ብቻውን መኖርን ይፈራ ነበር አሁን ግን ከሰው ጋር መኖርን ይፈራል…ድሮ መልካምነት በቴሌቨዥን አይወራም ነበር በሬዲዬ ዜና አይሆንም ነበር ሰዋች ለሽልማት ብለው መልካም አያደርጉም ነበር…ድሮ ደራስያን እውነት ይፃፉ ነበር አሁን ግን ሰው እሚፈልገውን አልያም ሰው እሚስማማበትን ብቻ ይፃፋሉ።


ፍቅር ያሸንፋል!
ሁሉም መልካም ይሆናል!

እግዛብሔር ይቅደመን

ሚኪያስ የ ሕይወት ልጅ
@itsmikiyashappy
@itsmeMiky