Get Mystery Box with random crypto!

ዝናብ ቢሆንም መውጣት ፈለኩ ግን የት እንደምሄድ አላውቅም ብቻ እንዳይበርደኝ እንደነገሩ ለ | የኔ ማስታወሻ✍🏾በኪያብ🦋

ዝናብ ቢሆንም መውጣት ፈለኩ ግን የት እንደምሄድ አላውቅም ብቻ እንዳይበርደኝ እንደነገሩ ለባብሼ ወጣሁ በመንገዱ ብዙም ሰው የለም ዝናቡን ይሁን ብርዱን ሽሽት በየቤቱ ተሸሽጓል እናም ወደማልጠፋበት ሲደብረኝ ምደበርበት ብቻዬን መሆን ስፈልግ ምሄድበት ካፌ ጎራ አልኩ ማሰብ ጀመርኩ ግን ወደፊቴን አልነበረም ያለፈውን ነበር ከበውኝ የነበሩ ሰዎች የት ሄዱ ለምን ጠፉ ልፈልጋቸው ስወጣ ለምን አጣኋቸው እንጃ መልስ የሌላቸው ጥያቄዎች እንደ ጉድ ይግተለተላሉ
ስልኬን አየሁት ይደወሉ የነበሩ ቁጥሮች ትዝ አሉኝ
የት ነሽ?
ስልክሽ ዝግ ነበር
ለምን ዝግ ሆነ?
ለምን አታንሽም..........................................................................
ጥሪዎች ስለሚበዙ ዘጋው ነበር አሁን ያ የለም ስልኬ ስልክ እስከማይመስለኝ (ሚደውል የለም) ወረተኛ ብቻ ሁሉም ወረተኛ ወሬያቸው የወረት
ፍቅራቸው የወረት
ንግግራቸው ውሸት
ቃላቸው ውሸት ሁሉ ነገራቸው ውሸት
ደግሜ ስልኬን አየውት ለሚያየኝ የምጠብቀው ሰው ያለ ይመስላል ደግሜ ማሰብ ጀመርኩ ምናልባት ደካማ ያረጉኝ መስሏቸው ይሆናል ግን ከምንግዜውም በላይ ደና ሆኛለው በውሸታቸው የወደኩ ቢመስላቸውም አጠንክረውኛል የውሸትም ቢሆን እንድወዳቸው አርገውኛል አላዝንባቸውም ሰአቴን አየሁ እንደመምሸት አያረገው ነው ብቻ መሆን ቢደብርም ነፃነቱ ያስደስታል ነፃነቴን እያሰብኩ እንደመጣሁት ቀስ እያልኩ ወደቤት ተመለስኩ በቃ ዛሬ ከዝናቡ ጋ ብቻዬን እንዲ ነበር የሆንኩት

#እናት