Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ዜና || ከመሕዲ ፕሮዳክሽን አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ መሕዲ መልቲሚዲያ | መሳጭ ኢስላሚክ ታሪኮች

አዲስ ዜና || ከመሕዲ ፕሮዳክሽን

አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱህ
መሕዲ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን እንኳን ለተከበረው የረመዷን ወር በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን በማለት መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

በዚህ በተከበረው የረመዷን ወር ሁላችንም በዒባዳ በርትተን ወደ አሏህ ለመቃረብ እንድንበቃ እንዲሁም በዕድለኝነት ያገኘነውን ወር ኒያችንን ለአሏህ አጥርተን እንድንጠቀምበት አደራ እንላለን።

*

ዜና
ቁ.1
በጥር 29 /2014 ኢሽተቅና በሚል ርዕስ ልዩ የመድረክ ፕሮግራም ማዘጋጀታችን እና አዳራሹ ከመጠን በላይ ሞልቶብን በኋላ የመጡ ሰወችን ከአፉታ ጋር መመለሳችን ይታወሳል። ይህም ከተማችን ላይ ኢስላማዊ የኪነጥበብ መድረኮች ምን ያክል አስፈላጊ መሆናቸውን አስገንዝቦን አልፏል።

በመሆኑም ኢሽተቅና ቁ.2 በሚል ርዕስ የፕሮግራሙን ተከታይ መድረክ ዝግጅት በማጠናቀቅ ላይ እንገኛለን። በአሏህ መልካም ፈቃድ በቅርቡ ወደ እናንተ ይዘነው እንመጣለን ።

**

ዜና
ቁ.2

ከዚህ በፊት በፕሮዳክሽናችን ተዘጋጅተው ከዑለማወችም አስፈላጊውን እውቅና አግኝተው ለህትመት የበቁ ሁለት የሕፃናት ስዕላዊ መፅሐፍት አሉን።

1ኛው (የሕፃናት የሶላት መማሪያ) የሚሰኝ ሲሆን ከውዱእ ጀምሮ ሙሉ አሰጋገዱን በፅሁፍ እና ዕላዊ በሆነ መንገድ አካትቷል። ዋጋው ደግሞ #25_ብር ብቻ ነው።

2ኛው ደግሞ (ዱዐእ እና አዝካር) የተሰኘ መጽሐፍ ነው። ውስጡ ስዕላዊ ሆኖ ዱዓዎቹ በዐረበኛ እና በአማርኛ ተካተውበታል። ይህም የሕፃናት የዕለት ከዕለት እንቅስቃሴ በነብያዊ ዱዓዎች እና ዚክሮች የታጀቡ ይሆኑ ዘንድ በከፍተኛ ሁኔታ የሚያግዝ መፅሀፍ ነው።
የዚህም ዋጋ #25ብር ብቻ ነው።

******

በቤታችን ውስጥ የሚገኙ ህፃናት እህት ወንድሞቻችን ወይም ልጆቻችን ሊሆኑ ይችላሉ በዲናዊ መንገድ ተኮትኩተው እና ሶላታቸውን ተምረው እንዲያድጉ የማድረግ ኃላፊነት አለብን። ይህንን ሂደት ቀላል ለማድረግ እና አንባቢ ትውልድ ለመፍጠር በማሰብ መሕዲ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን እነዚህን መፅሀፍት በከፍተኛ ጥራት እና በማይታመን (ርካሽ) ዋጋ እንካችሁ ብሏል።

መፅሐፍቱን መግዛት የምትፈልጉ
በ 0918 399260 - 0975 542020 በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ።

******

መሕዲ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን
https://t.me/mehdi_multimedia