Get Mystery Box with random crypto!

......ረመዳን..... የወር ሁሉ ንጉስ የኢስላም ስጦታ መጣልን ረመዳን የሙስሊሞች | ኢስላማዊ አለም እና ግጥም☪️

......ረመዳን.....



የወር ሁሉ ንጉስ የኢስላም ስጦታ
መጣልን ረመዳን የሙስሊሞችደስታ
ፁመን ልናሳልፍ በአላህ ችሮታ
እጅጉን ተቃርበን ወደ አለማት ጌታ
አላህ ከጅሎልን ዘንድሮን ወፈቀን
ድጋሚ ውዱን ወር ለማየትም በቃን
እስኪ እናሳልፈው በፆም በኢባዳ
በዘካ በሰላት በሀምድ በሰደቃ
ከአላህ ጋር እንሁን በእያንዳንዷ ቅፅበት
ለከርሞ እንዲያደርሰን ከልብ በመመኘት
ታላቁ ወር መጧል ብስራት ዜና ይዞ
መንገድን ሊያመቻች ለጀነቱ ጉዞ
ሸይጣንን አባሮ ከምድር አፈር ላይ
ወደአላህ ሊያቃርብ በዲናችን ጉዳይ
ከአላህ አስተሳስሮ እጅግም አቃርቦ
ቶሎ ያልቅብናል ሳንጨብጠው ቀርቦ
ህልም ይመስለናል የረመዳን ማብቃት
ወር ሲፈጥን ስናይ ልክ እንደ ሳምንታት
ታዲያ አንዘናጋ እያየነው እስኪያልቅ
እንጠባበቀው ቆመን በተጠንቀቅ
ተጠቃሚ እንሁን በታላቁ ወር ውስጥ
ካለፉት ጊዜያት በደረጃ እንድንበልጥ
ከልብ ተመልሰን ወደ አለማት ጌታ
ረመዳንን እንፁም በጤና በደስታ
የተቸገሩትን ሳንዘነጋ ላፍታ
ተግባራችን ሆኖ ዘካናእርዳታ
ለሌለው አካፍለን ያለንን በደስታ
ከአላህ ምንዳን ሽተን እናግኝ እርካታ
ረመዳን ተባለ በአራት ፊደላት
መቼ ይገልፁታል ሺ የሆኑ ቃላት!!

°°°°°°°°° ረ
°°°°°°°°°°°°° መ
°°°°°°°°° ዳ
°°°°°°°°°°°°° ን

@Islamic_Poem_Ss
°°~°°~°~°°~°~°~
@Islamic_Poem_Ss