Get Mystery Box with random crypto!

ወቅታዊ ማስታወሻ ለሙስሊሞች ውድ ሙስሊም ወንድም ና እህቶች ይህን ወቅታዊ ማስታ | ኢስላማዊ እና ጠቅላላ እውቀት

ወቅታዊ ማስታወሻ ለሙስሊሞች

ውድ ሙስሊም ወንድም ና እህቶች
ይህን ወቅታዊ ማስታወሻዬን ጥቂት ጊዜያችሁን ሰውታቹ እንድታነቡት አደራ አደራ እላለሁ
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ አና በጣም አዛኝ በሆነው
ያለንበት ወቅት በ ዱንያ ካሉት ቀናቶች በጣም በላጭ የሆኑ እና አላህ ዘንድ በእነዚህ ቀናቶች የሚሰሩ ስራዎች ከሌሎች በተለየ ና በበለጠ ተወዳጅ የሚሆንበት 10ቱ ቀናት ላይ ነው ያለው

ማስታወሻዬም የሚያተኩረው በእነዚህ ውስጥ በሚገኘው በጣም ታላቅ ና ትሩፋቱ የበዛ ስለሆነው ስለ ዓረፋ
(የዙልሂጃ 9ኛው ቀን) ነው
የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም የዚህን ቀን ትሩፋቶች በሚገባ አብራርተዋል

ነብያችን እንዲህ ይላሉ : አላህ ሱ.ወ ከዐረፋ ቀን የበለጠ ባሮቹን ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት የሆነ አንድም ቀን የለም
ከዛም በመቀጠል ያሉት :እኔም ከኔም በፊት ከነበሩት ነብያት ካሉት ንግግር በላጩ
لا ﺇﻟﻪَ ﺇﻻَّ ﺍﻟﻠَّﻪ ﻭﺣْﺪﻩُ ﻻَ ﺷَﺮِﻳﻚَ ﻟﻪُ، ﻟَﻪُ ﺍﻟﻤُﻠْﻚُ، ﻭﻟَﻪُ ﺍﻟﺤﻤْﺪُ، ﻭَﻫُﻮ ﻋَﻠَﻰ ﻛُﻞِّ
ﺷَﻲﺀٍ ﻗَﺪِﻳﺮ
ላ ኢላሃ ኢሏሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር የሚለው ነው::
ይህን ዚክር በብዛት በማለት እንበርታ
ሌላው ነብያችን እንዲህ ብለዋል
በላጬ ዱዓ ማለት የዓረፋ ቀን የሚደረግ ዱዓ ነው

በዚህ በላጭ በሆነው የዓረፋ(ዙልሂጃ 9) ቀን አላህ ሱ.ወ
-ከእሳት ነፃ ከሚያደርጋቸው
-ወንጀላቸው ከሚማርላቸው ባሮቹ መሆን የፈለገ ሰው
የዓረፋን ቀን ይፁም
ነብያችን እንዲህ ይላሉ :
{የዐረፋ ቀን በመፆም አላህ ያለፈውንና የሚመጣውን አመት ወንጀል እንደ ሚምር እተሳሰባለሁ}
{የዐረፋ ቀን የፆመ የሆነ ሰው ተከታታይ የሆኑ የሁለት አመት ወንጀሎቹን ይማርለታል}
የተውሂድ ቃል ዚክር ማለትን ያብዛ
ላ ኢላሃ ኢሏሁ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር
አላህ እንዲምረው እና ከእሳት ነፃ ከሚሆነው እንዲያደርገው መለመንን ያብዛ
አሏሁመ አእቲቅ ሪቃበና ሚነን ናር የምትለዋን ዱዓ በማለት አላህን እንለምን
በዚህ ቀን ዱኣ ተቀባይ መሆኑ በጣም የሚከጀልበት ነው
ለዚህም ቀን ኸይር ፈላጊ የሆነ
ሙስሊም ራሱን ባለቤቱን እህት ወንድሞቹንና ልጆቹን ይህንን የተከበረ ቀን እንዲፆሙ ይቀሰቅሳል
አላህ ሱ.ወ የዚህን ቀን ትሩፋቶች ከሚያገኙ እና ወንጀላቸው ከሚማርላቸው ሰዎች እንዲያደርገን እለምነዋለሁ በመልካም ዱዓቹ አትርሱኝ

ይህን አንገብጋቢ ማስታወሻ ለምታውቁትም ለማታውቁትም ሙስሊም ለሆነ አካል እንድታሰራጬ እና የመልካም ስራ ተቋዳሽ እንድትሆኑ እጠይቃለሁ
ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ
طلحة أحمد