Get Mystery Box with random crypto!

ስለ አምላካችን አላህ ያስተማሩት ከፊል ነቢያት። 'ኑሕ' 11:25-26 ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ | ኢስላማዊ እና ጠቅላላ እውቀት

ስለ አምላካችን አላህ ያስተማሩት ከፊል ነቢያት።

"ኑሕ"
11:25-26 ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክን፤ አላቸውም ፦ እኔ ለናንተ ግልጽ አስፈራሪ ነኝ። አላህን እንጂ ሌላን አትገዙ፤ እኔ በናንተ ላይ የአሳማሚን ቀን ቅጣት እፈራላችኋለሁና።

"ሁድ"
11:50 ወደ ዓድም ወንድማቸውን ሁድን ላክን አላቸው ፦ ወገኖቼ ሆይ አላህን ተገዙ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፤ እናንተም ቀጣፊዎች እንጂ ሌላ አይደላችሁም።

"ሷሊህ"
11:61 ወደ ሠሙዶችም ወንድማቸውን ሷሊህን ላክን፤ ፦ሕዝቦቼ ሆይ አላህን ተገዙ፤ ከርሱ ሌላ ለናንተ አምላክ፣ የላችሁም፤ .. አላቸው።

"ኢብራሒም"
19:48 እናንተንም ከአላህ ሌላ የምትግዙትንም እርቃለሁ፤ ጌታየንም እግዛለሁ፤ ጌታየን በመገዛት የማፍር አለመኾኔን እከጅላለሁ።

ሹዐይብ"
11:84 ወደ መድየንም ወንድማችውን ሹዐይብን፣ ላክን፤ አላቸው ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፤ ከርሱ ሌላ ለናንተ አምላክ የላችሁም፤ ስፍርንና ሚዛንንም አታጉድሉ፤ እኔ በጸጋ ላይ ሆናችሁ አያችኋለሁ፤ እኔም በናንተ ላይ የከባቢን ቀን ቅጣት እፈራለሁ።

"ሙሳ"
7:104-105 ሙሳም አለ፦ፈርኦን ሆይ! እኔ ከዓለማት ጌታ የተላክሁ መልክተኛ ነኝ፤ በአላህ ላይ ከእውነት በቀር አለመናገር ተገቢዬ ነው፤ ከጌታችሁ በታምር በእርግጥ መጣኋችሁ፤ የእስራኤልንም ልጆች ከኔ ጋር ልቀቅ።

ኢሳ"
3:51 አላህ ጌታየና ጌታችሁ ነዉ፤ ስለዚህ ተገዙት፤ ይህ ቀጥተኛ መንገድ ነዉ አላቸዉ።