Get Mystery Box with random crypto!

ነቢያችን”ﷺ” የነቢያት መደምደሚያ ናቸው፤ ወሕይ መውረድ እሳቸው ጋር ቆሟል፤ ከእርሳቸው በኃላ ሪሳ | የሀይማኖት ንፅፅር ☪️vs✝️

ነቢያችን”ﷺ” የነቢያት መደምደሚያ ናቸው፤ ወሕይ መውረድ እሳቸው ጋር ቆሟል፤ ከእርሳቸው በኃላ ሪሳላ መውረድ አሊያም ነበእ መውረድ ቆሟል፦
33፥40 ሙሐመድ ከወንዶቻችሁ የአንድንም ሰው አባት አይደለም፤ ነገር ግን የአላህ መልክተኛ እና *”የነቢያት መደምደሚያ”* ነው፤ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው። مَا كَانَ مُحَمَّدٌ أَبَا أَحَدٍ مِنْ رِجَالِكُمْ وَلَٰكِنْ رَسُولَ اللَّهِ وَخَاتَمَ النَّبِيِّينَ وَكَانَ اللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمًا
ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 8, ሐዲስ 2272
አነስ ኢብኑ ማሊክ እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”በእርግጥም መልእክተኛነት እና ነብይነት ተዘግቷል። ከእኔ በኃላ መልእክተኛም ነብይም የለም*። حَدَّثَنَا أَنَسُ بْنُ مَالِكٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ” إِنَّ الرِّسَالَةَ وَالنُّبُوَّةَ قَدِ انْقَطَعَتْ فَلاَ رَسُولَ بَعْدِي وَلاَ نَبِيَّ

ምን ትፈልጋለህ? ነቢያችን"ﷺ" ከእርሳቸው በኃላ የፈጣሪ ነቢይ ፈጽሞና ጨልጦ እንደማይመጣ ፍርጥ አርገው እንቅጩን ነግረውናል። እዚሁ ሐዲስ ላይ "ነቢይነት"Prophethood" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ኑቡወት" نُّبُوَّة ሲሆን “ነበእ” نَبَإِ ለሚለው ቃል ተለዋዋጭ ቃል ነው፤ ነቢይነት ከተዘጋ ትንቢትም ተዘግቷል። ከእርሳቸው በኃላ የሚመጣ ነቢይ እና መልክተኛ ከሌለ ከቁርኣን በኃላ የምሰማው ከፈጣሪ የመጣ መልእክት እና ትንቢት የለም። አለ የተባለው ሁሉ የሐሳዌ መልእክት እና ትንቢት ነው። “አድ-ደጃል” الدجّال‌‎ የሚለው ቃል “ደጀለ” دَجَلَ ማለትም “ቀላቀለ” ከሚል ግስ የመጣ ሲሆን “ቀላቃይ” ማለት ነው፤ እውነትን ከሐሰት ጋር የሚቀላቅል ማለት ነው፤ ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን ሃይማኖታዊ ፍቺው ደግሞ “ኀሳዌ” ማለትም “አሳሳች” “ውሸተኛ” “ቀጣፊ” ማለት ነው። ዋናው ደጃል “መሢሑል ደጃል” ማለትም “ኀሳዌ መሢሕ” ሲሆን እርሱ ከመምጣቱ በፊት የሚመጡ ሠላሳ ደጃሎች አሉ፤ “ደጅጃሉን” دَجَّالُونَ የሚለው ቃል “ደጃል” دجّال‌‎ ለሚለው ነጠላ ቃል ብዜት ነው፤ እነዚህ ወደ ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች “እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ” ወይም “እኔ የአላህ ነብይ ነኝ” ብለው ይነሳሉ፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 54, ሐዲስ 108
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው ነብዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *“የመጨረሻይቱ ሰአት አትቆምም ሠላሳ የሚቃረቡ ደጃሎች ቀጣፊዎች ተነስተውስ፦ “እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ” ብለው ቢናገሩ ቢሆን እንጂ”*። عَنْ أَبِي، هُرَيْرَةَ عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ” لاَ تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يُبْعَثَ دَجَّالُونَ كَذَّابُونَ قَرِيبٌ مِنْ ثَلاَثِينَ كُلُّهُمْ يَزْعُمُ أَنَّهُ رَسُولُ اللَّهِ
ሱነን አቢ ዳውድ :መጽሐፍ 37, ሐዲስ 13
የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *ከእኔ ኡማህ ውስጥ ሠላሳ የሚያህሉ ቀጣፊዎች፦ “ነብይ ነኝ” ብለው ይነሳሉ፤ ነገር ግን እኔ የነብያት መደምደሚያ ነኝ፤ ከእኔ በኃላ ነብይ የለም”*። وَحَتَّى تَعْبُدَ قَبَائِلُ مِنْ أُمَّتِي الأَوْثَانَ وَإِنَّهُ سَيَكُونُ فِي أُمَّتِي كَذَّابُونَ ثَلاَثُونَ كُلُّهُمْ يَزْعُمُ أَنَّهُ نَبِيٌّ وَأَنَا خَاتَمُ النَّبِيِّينَ لاَ نَبِيَّ بَعْدِي

በነቢያችን"ﷺ" ኡማህ ውስጥ የሚነሱት እነዚህ ሐሰተኛ ነቢያት ሲሆኑ በክርስትናው ደግሞ የተነሱት እልፍ አእላፍ ናቸው። "ነቢይ ነኝ" ብለው የተነሱት ባሃኦላህ፣ ረሺድ ኸሊፋህ፣ ጉላም አሕመድ ወዘተ መነሻቸው "ለወልይ የሚሰጥ ከራመት አለኝ" በሚል ሽፋን ነው፤ "ዶሮን ሲያታልሏት፥ ሙቁ ውኃው ለገላሽ ነው አሏት" ይባል የለ? የወደፊቱን ክስተት፣ ክንውን፣ እና ድርጊት ዕናውቃለን የሚሉት ጋር ሄዶ ማመን ትልቁ ሺርክ ነው፥ ከኢሥላም አጥር ያስወጣል፤ ድርጊቱ ኩፍር ነው፦
ሱነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 1, ሐዲስ 682
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ” እንዳለው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ ማንም በሓይድ ላይ ካለች ሴት ወይም በመቀመጫዋ በኩል ተራክቦ ቢያደርግ *"አሊያም ወደ ተንባይ ቢሄድና የተነገረውን ቢያምን በሙሐመድ”ﷺ” ላይ በተወረደው ክዷል"*። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏ "‏ مَنْ أَتَى حَائِضًا أَوِ امْرَأَةً فِي دُبُرِهَا أَوْ كَاهِنًا فَصَدَّقَهُ بِمَا يَقُولُ فَقَدْ كَفَرَ بِمَا أُنْزِلَ عَلَى مُحَمَّد

"ካሂን" كَاهِن የሚለው ቃል "ከሀነ" كَهَنَ‎ ማለትም "ተነበየ" ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን "የሩቅ ነገር ተንባይ" ማለት ነው፤ እነዚህ የሩቅ ነገርን ዕናውቃለን የሚሉ ጠንቋዮችንም ያመለክታል። ስለዚህ ትንቢት ተነበዩ የተባሉት በዓለማችን ውስጥ ኖስትራዳመስ"Nostradamus" እንዲሁ በአገራችን እዩ ጩፋ፣ እኅተ ማርያም ሆነ ሼህ ሑሤን ጅብሪል ከአላህ ያልሆነ የሐሳዌ ጽርፈት መሆኑን ከወዲሁ መጠንቀቅ ነው። በተለይ ክርስቲያኖች የሼይኽ ሑሤን ጅብሪል ትንቢት እያሉ የሚያናፍሱት፣ የሚደርሱትና የሚጽፉት እሥልምና ትክክል መሆኑን ለማሳወቅ ሳይሆን ቅቤ አንጓችና አስብቶ አራጅ ስለሆኑ ነው። "አሞኛችሁ ዘንድ ዐይናችሁን ጨፍኑ፥ ጆሮአችሁን ድፈኑ" ብንባል ፍንክች የአባ ቢላዋ ልጅ ብለናል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቤ እሥልምና ወሒድ
@islam_ustaz_abuhayder

ወሠላሙ ዐለይኩም