Get Mystery Box with random crypto!

How to write CV በቀጣሪዎች ዘንድ ተመራጭ CV እንዴት መፃፍ ይቻላል፡፡ CV ማለት የአንድ | Ethiopia

How to write CV
በቀጣሪዎች ዘንድ ተመራጭ CV እንዴት መፃፍ ይቻላል፡፡
CV ማለት የአንድ ሰው የትምህርትና ሌሎች professional ታሪኮቹን በአጭር መልኩ የሚገለፅበት መንገድ ነው፡፡ ብዙ ግዜ ለስራ ማመልከቻነት እንጠቀምበታለን የራሳችንንም ማንነት በጥሩና ቀለል ባለ መልኩ ለማቅረብ ያስችለናል፡፡ ታዲያ በዚህ ወቅት እንዲቀጥሩን ለምንፈልጋቸው ቀጣሪዎች አሰልቺ ያልሆነና ሳቢ የሆነ CV መፃፍ ትልቅ ትኩረት ለማግኘት ያስችለናል፡፡
ታዲያ እንዴት እንዲህ ያለውን CV መፃፍ እንችላለን እና ምን ምን መካተት አለበት የሚለውን እንመልከት፡፡
1 ከቀድሞ ስራ ጋር የተያያዙ የስራ ልምዶች፡፡
2 የትምህርት ሁኔታ እና ሌሎች ተዛማጅ ችሎታዎች
3 አፃፃፋችሁን ለማንበብ እና ለመረዳት ቀለል ባለመልኩ ይሁን
4 የስራ ልምድ ካላችሁ በቀደመው ስራችሁ ያሳካችኋቸውን ነገሮች ጥቀሱ፡፡ ጀማሪ ከሆናችሁ ደግሞ በነፃ አገልግሎት እንዲሁም በተማራችሁበት የትምህርት ተቋም ስታደርጉ የነበረውን መልካም እንቅስቃሴ ጥቀሱ፡፡
5 ፊደላት እና ቃላት አጠቃቀም ትኩረት ማድረግ ፡፡
6 እናንተ በመስሪያ ቤቱ ብትቀጠሩ ልታበረክቱ የምትፈልጉትንና እናንተ በመቀጠራችሁ በመስሪያ ቤቱ
ስኬት ላይ ልትጨምሩ የምትፈልጉትን ጥቀሱ
7 አድራሻችሁን ስትጠቅሱ የተለያዩ አማራጮችን አስቀምጡ፡ ስልክ ኢሜይል፡፡
8 ሪፈረንስ ስትጠቅሱ ስለእናንተ በደንብ ሊገልፅ የሚችል ሰው ይሁን፡፡
9 ከሁለት ገፅ ባይበልጥ መልካም ነው አሰለቺ እንዳይሆን ተጠንቀቁ፡፡