Get Mystery Box with random crypto!

ኢማሙ አቡ ሀኒፋ ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሂም ወቢሂ ነስተዒኑ ዐውነከ ያከሪም አልሀምዱ ሊላሂ ረቢል ዐ | ኢማሙ አቡ ሀኒፋ

ኢማሙ አቡ ሀኒፋ

ቢስሚላሂ ረህማኒ ረሂም ወቢሂ ነስተዒኑ ዐውነከ ያከሪም አልሀምዱ ሊላሂ ረቢል ዐለሚን ወሶላቱ ወሠላሙ ዐላ ሠይዲና ሙሀመድ ወአሊሂ ወሷህቢሂ አጅመዒን

የትጥበት አይነቶች

የትጥበት አይነቶች 10 ናቸው።

ከነዚህም ውስጥ 4ቱ ፈርድ፣ 4ቱ ሡና፣1ዱ ዋጂብ 1ዱ ደግሞ ሙስተሀብ ናቸው።


1፦ ፈርድ፦
1 ሴት እና ወንድ ልጅ ግንኙነት ማድረግ ይህም ሲባል የወንድ ልጅ ብልት ከክርክራቱ በላይ ከሴት ልጅ ብልት ከገባ በሁለቱም ላይ ትጥበት ግዴታቸው ነው የዘር ፈሳሽ ባይወጣም እንኳን።

2 በእንቅልፍ ልቡ የዘር ፈሳሽ ካዬ ፣ ብልቱን በመነካካት ወይንም ደግሞ በክጃሎት (በፍላጎት) መልኩ ሲወጣ ደግሞ የመፈናጠር ባህሪ ካለው ትጥበት ግዴታ ነው።

3 ሴቷ ደግሞ የወር አበባ ካየች

4 ኒፋስ፦ ኒፋስ ብሎ ማለት ሴቷ ከወለደች በኋላ የሚወጣ ፈሳሽ ደም ማለት ነው። ከላይ ከጠቀስናቸው ውስጥ አንዱ ከተከሠተ ትጥበት ግዴታ ይሆናል።



2፦ሡና፦
1 ጁሙዐ ቀን መታጠብ
2 የኢድ ቀን መታጠብ
3 የአረፋ ቀን መታጠብ
4 ወደ ሀጅ ጉዞ ሲየደርግ ከሀረሙ ከመድረሱ በፊት መታጠብ ሱና ነው ።


3፦ ዋጂብ፦
1 የሞተን ሠው ማጠብ ሙስሊም ሁኖ ከሞተ። ከላይ የጠቀስነው ነገር ከተከሠተ አንድ ሠው ከሠራው ለሌላው ይብቃቃል።


4፦ ሙስተሀብ፦
1 ካፊር የነበረ ልጅ ወደ እስልምና ሲገባ መታጠብ ይወደዳል ጀናባ ካልነበር ባይታጠብ ችግር የለውም። ግን
ካፊር በነበረበት ጊዜ ጀናባ ከነበር መታጠብ ግዴታ ነው።


ኢንሻአላህ በቀጣይ ካቆምንበት እንቀጥላለን አላህ ያቆየን






𝕤𝕙𝕒𝕣𝕖 & 𝕛𝕠𝕚𝕟 𝕦𝕤!

@imamuabuhanifa
@imamuabuhanifa
@imamuabuhanifa

For any Comment

@AmuAmii