Get Mystery Box with random crypto!

[ Photo ] እንኳን ደስ አላችሁ! ************************ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ | የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ዋና ህብረት ጽ/ቤት

[ Photo ]
እንኳን ደስ አላችሁ!
************************
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎችን ነሀሴ 28/2014 ዓ.ም በድምቀት ያስመርቃል፡፡ በዕለቱ በተለያዩ መርሀ- ግብሮች ተምረው ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ከ5531 በላይ ተማሪዎች በቅድመ- ምረቃና በድህረ- ምረቃ ፕሮግራሞች ይመረቃሉ፡፡
ውድ እጩ ተመራቂ ተማሪዎቻችን፣ የተመራቂ ቤተሰቦች፣ መምህራን እና አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አካላት እንኳን ደስ አላችሁ!
የምረቃ ስነ ስርዓቱ በዋልታ ቴሌቪዥን በቀጥታ ስርጭት ስለሚተላለፍ መርሀ ግብሩን በቦታው ተገኝታችሁ መታደም ያልቻላችሁ ፕሮግራሙን በቀጥታ በዋልታ ቴሌቪዥን መከታተል የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
**********************
ለልህቀት እንተጋለን
ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ነሀሴ 18/2014 ዓ.ም