Get Mystery Box with random crypto!

የደመቁ ገፆች . . . . . . አደፍርስ የዘመናዊ ስነ ፅሁፍ ፋና ወጊ በአብዮቱ አቅራቢያ የአማ | ሁሱ ዜማ

የደመቁ ገፆች . . . . . .

አደፍርስ የዘመናዊ ስነ ፅሁፍ ፋና ወጊ በአብዮቱ አቅራቢያ የአማርኛ ልብ ወለድ አብዮት ያስነሳ በደረጃው ላቅ ያለ ስራ ነው ። የታሪክ ውቅሩ መልዕክት ሚያሻግርባቸው ቦታና ሰአቶች በደንብ የለየ ባህላችንን እንዴት ከፍልስፍናና ከዘመናዊነት ጋር ማስታረቅ እንዳለብን አስምሮ ያሳየ ፅድት ያለ ስራ ነው ። ጋሽ ዳኛቸው ወርቁ አፈሩ ይቅለላቸው ህያው ሆነው አልፈዋል ። በገፆቹም እንዲህ ይሉናል . . . .


" ንብና : የወባ : ትንኝ : ሁለቱ : የተለያዩ : ነፍሳት : አበባን ይቀስማሉ ። ንብ : ከአበባ ባገኘችው : ንጥር : ማርን : ትሠራለች።
ለራሷ : በቅታ : ለሰው : ትተርፋለች። የወባ : ትንኝ: ደግሞ: ከዚያው : ካበባ : በተገኘው : ንጥር : መርዟን : ትሰራለች ። በመርዟም :የወባ : በሽታን : ታስተላልፋለች ። እንግዲህ : አንደኛው : ለደግ : ሌላው : ለክፉ : ስላዋሉት : አያስፈልግም : ለማለት : አንችልም . . . .


" ባጭሩ : ስልጣኔ : እንደተቀባዩ :ነው ።

" እኛ : ሀገር : የሚታየው : ያሠለጣጠን : ሁኔታ : የወባ : ትንኞቹን :መንገድ : የተከተለ : ነው ። ያለንን : ሳናውቅ : የሌለንን : ለማግኘት : የምናደርገው : ጥረት : ሁሉ : ከንቱ : ነው ።

" ውርደት : የፈለጉትን : ማጣት : እንጂ : የፈለጉትን : ለማግኘት : ሲባል : የሚደርሰው : እርግጫ : እና : ግልምጫ አይደለም "


" ሀገርና : መንግስት : ርስትና : ሹመት : ብቻ አይደለም ። ርስትና: ሹመት : የትም ቢሄዱ : ማንም : ቢገዛ : አይታጣም ። ሀገርና መንግስት : አለኝ የሚያሰኙ : ልማድ : ወግ : ቅርስ : ሌሎችም የጠቀስናቸው :ባህሎች : በሰው: ላይ : አድረው : ውህደታቸው : ደም : ግባትና : ትከሻ : ክብደት: ሲያመጣ: ነው ። አለዚያ ሀገረ ቢስ : ወይም : ውቃቤ ቢስ : ነሽ እንጂ : ባለ ሀገር : ባለ መንግስት አይደለሽም ። "


" እኛ : የምንለው : ዘመናዊን : ስልጣኔ : ለመቀበል : ከብረት : ምሰሶ : የጠና : ሰውነት : እንዲኖረን ያሻል ። ለማኝ : እንኳን አቆማዳውን : ሳያስተካክል : ለልመና : አይወጣም - - - - - - ስለዚህ : ዘመናዊን : ስልጣኔ : ለመቀበል : መጀመር : መቀበያ : ስብእናችንን : እናጠንክር : ነው : የምንለው : ባህላችንን : ወጋችንን : ልማዳችንን : ቅርሳችንን : እንመርምር . . . መርምረን ያገኘነውን : ይዘን : ያላገኘነውን እንፈልግ : አለዚያ : ነፍስ : እንደተለየችው : ስጋ : ሆነን : ብንቀርብ :በመዘውር : የሚሄድ : ስብዕና : ነው : የምናተርፈው : ነው የምለው . . . .

@KALIDakelu