Get Mystery Box with random crypto!

ሰሞኑን 50 ሹፌሮች እና መንገደኞች ታግተው ከ50 ሚልዮን ብር በላይ ሲጠየቅባቸው እነርሱን ለማስፈ | የስብዕና ልህቀት

ሰሞኑን 50 ሹፌሮች እና መንገደኞች ታግተው ከ50 ሚልዮን ብር በላይ ሲጠየቅባቸው እነርሱን ለማስፈታት የከተማው ህዝብ መንገድ ዳር አንጥፎ ሲለምን  እነዚህ ሚድያዎች አንድ ነገር እንኳን ትንፍሽ አላሉም ነበር፣ አሁን ግን...

ሳትታገት ታገትኩ ብላ ብር ስለጠየቀች ሴት እንደ ትልቅ ዜና አድርገው አራግበውታል።አሁን ላይ እየተሰራው ካለው ግፍ አንፃር ይሄ እንደዜና  መቅረብ አልነበረበትም ። ነገር ግን መንግስት  በየጊዜው ታግተው የሚሞቱ ሰዎችን እውነት እንዲዳፈን ስለሚፈልግ ይሄን ዜና በሰፊው አራግቦታል።

በኦሮሚያ ብዙ አካባቢ ማገት እንደ ስራ ከተቆጠረ ሰንብቷል ዜጎች የመኖር ዋስተናቸውን አጥተዋል። ገንዘብ መክፈል ያልቻሉ ዜጎች ህይወታቸውን እያጡ ነው።ገንዘብም ከፍለው ህይወታቸውን ያጡም አሉ።ስርዓት አልበኝነት ነግሷል ዜጎች ሰርተው ሀብት የማፍራት መብታቸው ተነፍጓል።ሌላ ሀገር ቢሆን ትልቅ ሽፋን ይሰጠው ነበር። የኛ ሀገር ሚዲያዎች ግን በህዝብ ግብር እየሰሩ የህዝብ ድምፅ ከመሆን ይልቅ ለመጣው መንግስት የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ መሆናቸውን ቀጥለዋል።