Get Mystery Box with random crypto!

𝐈𝐭’𝐬 𝐨𝐤𝐚𝐲 ይህች ምስሉ ላይ የምታዪት ወጣት 𝐉𝐚𝐧𝐞 𝐌 ('#𝐍𝐢𝐠𝐡𝐭𝐛𝐢𝐫𝐝𝐞' ) ትባላለች | የስብዕና ልህቀት

𝐈𝐭’𝐬 𝐨𝐤𝐚𝐲

ይህች ምስሉ ላይ የምታዪት ወጣት 𝐉𝐚𝐧𝐞 𝐌 ('#𝐍𝐢𝐠𝐡𝐭𝐛𝐢𝐫𝐝𝐞' ) ትባላለች በቅርቡ በተደረገው 𝐀𝐦𝐞𝐫𝐢𝐜𝐚'𝐬 𝐆𝐨𝐭 𝐓𝐚𝐥𝐞𝐧𝐭 ተሳትፋ ከሳይመን 𝐆𝐨𝐥𝐝𝐞𝐧 𝐁𝐮𝐳𝐳𝐞𝐫 ተበርክቶላታል።
𝐈𝐭𝐬 𝐨𝐤𝐚𝐲 በሚል ርዕስ ግለ ታሪኳን ታቀነቅናለች...

በፈገግታ የታጀበችው እንስት ከርቀት ስትታይ ምንም ችግር ያላያት ወይም የማታውቅ ትመስላለች .....ታምናላችሁ ከዚህ ፈገግታ ጀርባ  የሳንባ ፣ የአከርካሪ እንዲሁም የጉበት ካንሰር ተጠቂ ናት የመኖር እድልሽ ሁለት በ መቶ ነው ተብላ  ...𝐈𝐭'𝐬 𝐨𝐤 እያለች ታቀነቅናለች "#ምንም ማለት አይደለም" እንደማለት ነው።

ሁለት ፐርሰንት ዜሮ ማለት አይደለም ተስፋ አለኝ ትላለች።  ብዙ አነቃቂ ንግግሮችን ሰምታችሁ .. አይታችሁ አልያም አንብባችሁ.. ..ይሆናል የተኖረ ማነቃቂያና ጥንካሬ ከዚህ በላይ አለ ብዬ አላስብም ....እስኪ ቆም ብለን እናስተውል እኛ በስንት ነገሮቻችን ፈጣሪን አማረናል ..? እድል ፊቶን አዞረችብን ብለን ተስፋ ቆርጠናል..? መልሱ እናንተውጋ ይቆይ

እኔ በሷ ውስጥ ሶስት ነገሮች ጎልተው ታዩኝ

#ተስፋ ...በምንም አይነት ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታዎች ውስጥ ብትሆን ተስፍ ካለህ ነገን ታያለህ።

#ትልቁ ውበት ደግሞ... ከውስጥ የመነጨ እውነተኛ ፈገግታ እንደሆነና #ጥንካሬን አየሁ።

በግርድፉ ወደ እኛ ስናመጣው "#ደስተኛ ለመሆን ህይወት ፈተና አልባ እስክትሆን መጠበቅ አይገባንም  በችግሮቻችን መሀልም ሆነን ደስተኛ መሆን ይቻላል" ትላለች!

ተስፋ አለመቁረጥ ማለት መቀየር የማንችለውን ነገር መቀበል እውነታውን መጋፈጥ.... መቀየር የምንችለው ላይ አቅማችንን ማዋል ስንችል ነው። ብዬ አሰብኩ።

𝐇𝐚𝐧𝐚 𝐅𝐚𝐧𝐭𝐮

@Human_Intelligence