Get Mystery Box with random crypto!

ህይወት ያላቸው ሮቦቶች ተሰሩ የሳይንሱ ዓለም በየእለቱ አዳዲስ ግኝቶችን እያሰማን ሲሆን፤ አሁን | የስብዕና ልህቀት

ህይወት ያላቸው ሮቦቶች ተሰሩ

የሳይንሱ ዓለም በየእለቱ አዳዲስ ግኝቶችን እያሰማን ሲሆን፤ አሁን ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊራቡ የሚችሉ ሕይወት ያላቸው ሮቦቶችን መፍጠር መቻሉን አሰምቶናል።
ሊራቡ ይችላሉ የተባሉት ሮቦቶቹ “ዜኖቦትስ” የሚል መጠሪያ ያላቸው ሲሆን፤ ተመራማሪዎች ህይወት ካሏቸው ህዋሶች እንደሰሯቸው ተነግሯል።

አዲስ የተሰሩት “ዜኖቦትስ” ሮቦቶች ልክ እንደሌሎች ሮቦቶች የተሰጣቸውን ተልእኮ በአግባቡ የሚፈጽሙ ናቸው የተባለ ሲሆን፤ ከሌሎች ለየት የሚያደርጋቸው ደግሞ መራባት መቻላቸው ነው።

ሆኖም ግን “ዜኖቦትስ” ሮቦቶች የሚራቡበት መንገድ ሌሎች ህይወት ያላቸው ፍጥረታት ከሚራቡበት መንገድ የተለየ እንደሆነም ነው ተመራማሪዎች ያስተወቁት።

ዜኖቦት ሮቦቶች ጥፍር ካላቸው የአፍሪካ እንቁራሪት ሽሎች የተገኙ የቆዳ ሴሎችንና የልብ ጡንቻ ሴሎች በመቀላቀል እንደተፈጠሩ ተመራማሪዎች አስታውቀዋል።

ዕቃዎችን መሸከም እና መግፋት የመሳሰሉ ተግባራትን ያሉ ተግባራትን እንዲከውኑ ታስበው የተሰሩት ሮቦቶቹ በኋላ ላይ ግን ራሳቸውን ማባዛት ሁሉ እንደሚችሉ ለማወቅ ተችሏል።

ሮቦቶቹ ራሳቸውን የሚያበዙት ሌሎች ህይወት ያላቸው እንቁራሪቶች በሚራቡበት መንገድ ሳይሆን “ኪነማቲክ” በተባለ የማባዛት ስርዓት
እንደሆነም ተመላክቷል።

“ኪነማቲክ” በተባለ የማባዛት ስርዓት የሚፈጠሩት ዜኖቦት ሮቦቶች በሕይወት ቆይተው እና አድገው ልክ እንደ ሌሎች ሮቦቶች ስራ እንዲከውን የሚያስችል ምርምር እየተካሄደ መሆኑንም ተመራማሪዎች አስታውቀዋል።

@Human_Intelligence