Get Mystery Box with random crypto!

አለመጣደፍ….!!! ::;;;;;;;;;;;;;;;;;;; (ቡርሐን አዲስ ) የጥድፊያ መንፈስ ይታ | የስብዕና ልህቀት

አለመጣደፍ….!!!
::;;;;;;;;;;;;;;;;;;;

(ቡርሐን አዲስ )

የጥድፊያ መንፈስ ይታይብናል፡፡ በብዙ ነገሮች መረጋጋት የከዳን ይመስላል፡፡ ሰከን ማለትን ሳንጠላው አልቀረንም… ጥቂት አፍታ ወስዶ የሰዎችን የልብ መሻት፣ ወይም የነገሮችን ስረ-ግንድ ለማስተዋል የተዘጋጀን አልሆንም…፤ እጅግ ጥቂት የበለጡን ግለሰቦች ይኖራሉ፤ እነሱን አይመለከትም ጉዳየ፡፡
/////

በብዛት ግን… የተጣደፈ ወጨፎ አይነት ባህሪ እየናጠን ነው……

፣……..

ሳስብ የሚሰማኝ፤ ሰው ስሜቱን ሳይሻገር የሚያቀርበው አስረጂ ሁሉ ወደ ልክነት የመድረስ ንጥረቱ ዝቅተኛ እንደሆነ ነው፡፡ ስሜቱን መሻገር ከቻለ እንደጥላቻ፣ ንቀት፣ ማጥላላት፣ ማኮሰስ ወዘተ አይነት አሉታ አጸፋዎችን አያስተጋባም፡፡ ሰዎች በሚኖሩት ህይወት፣ በሚያነሱት ሀሳብ ወይም ባላቸው ማንነት እያስታከከ ጥቁር መልክት አይዘራም፤ ፊቱን አያጮናም፡፡



ስሜትን መሻገር ለምሳሌ በማህበራዊ ሚዲያ ‹ፕላት ፎርሞች› ላይ የስድብ ወይም ዘለፋ አስተያየት ከመስጠት ይልቅ በመረጃ መቃወም፤ ወይም በመረጃ ማጠናከር አይነት ስሜት ካለን እንደማለት ይሆናል፡፡ በተጨማሪም አስተያየት ሳይሰጡ ዝም ማለትንም ይይዛል፡፡

በየቀኑ ከሚኖረን መስተጋርና ውሎ አንጻርም ለሌሎች ያለን እይታ፣ የሚሰማን ስሜት እልህ፣ ቁጭት፣ ንቀት ጥላቻ በአንድ ጎናችን ሲታጨቅበት አልያም ከወሰን የበዛ አድናቆትና መደመም ውስጥ ሲከተን እዚህም ላይ ያልተሻገርነው የስሜት ባህሪ አለ ማለት ነው፡፡
….
እናም…

በአንዳች ጉዳይ ላይ የተሰማን ስሜት… በአወንታም ይሁን በአሉታ ስሜታዊ ካደረገን ራስን ታግሎ ሰከን ማለት ጥሩ መፍትሄ ነው፡፡ ለማድነቅም ለመተቸትም አለመቸኮል… ከፍሬያማ ውጤት ያደርሳል፡፡

ቡርሃን አዲስ

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence