Get Mystery Box with random crypto!

ለዳግማ ትንሳኤ ቤታችሁ ቤታችን የኛና የእናንተ ብዙ አመታት ሆነው ከተመሰረተ በዚህ ሁሉ መሀል በክ | ሁለንተናዊ ስኬት

ለዳግማ ትንሳኤ
ቤታችሁ ቤታችን የኛና የእናንተ
ብዙ አመታት ሆነው ከተመሰረተ
በዚህ ሁሉ መሀል በክፉም በደጉ
ለነብስ ብላችሁ ይህን የምታደርጉ
እህት ወንድሞቼ ታላቅ ብስራት ዜና
ይዘን ተገኝተናል በሉ ያድምጡና
በእለተ ዳግማ ትንሳኤ በታላቁ ድግስ
አዘጋጅቶ ሲጠብቆ የት ይሆኑ እርሶስ
በዚያች ታላቅ እለት መቅረት አይታሰብ
ይተዋወቃሉ ደሞ አዲስ ቤተሰብ
የት ለምትሉ እነሆ መልስ እነሆ ከእኛ
ቅርብ ነው አይርቅም ከደረሱ መገናኛ
22 አዲስ ህይወት ሆስፒታል አካባቢ
#ፍቅር_የኢትዮጵያዊያን_የአእምሮ እድገት_ውስንነት_ማህበር ግቢ
ብለው ቢጠይቁ ለምልክት አይከብድ
በታክሲ በእግር ከፈለጉ በራይድ
እንጠብቆታለን አደራ አይቅሩ
ማስታወሻ ጊዜ ለራሶ ያኑሩ
ፕሮግራሙ ይሳካ ዘንድ ትኬት ይሸጣሉ
እድል ከቀናዎ ያው ይሸለማሉ

ደሞ ሌላ ሌላ አዎ ደሞ ሌላ
.........................
የጠበበ ልብሶች የጠበቦ ጫማ
ሰጥተው ይደሰቱ በሉ ይፅደቁማ
ዱቄት መቆረኒ ፓስታ ሩዝ ላርጎ
የአቅማችሁን ያህል ላመጣ ፈልጎ
ሌላም ሌላም መጠበቂያ ንፅህና
ለነዚህ ህፃናት አስፈላጊ ነውና
በእለቱ ይገኙልን ጠሪ ነው አክባሪ
ልጆቹም ተጫዋች ድርጅቱም ጀማሪ
ይምጡ ይጎብኙ ያስተዋውቁ አደራ
በሰማይ ይታጨዳል በምድር የተዘራ

እናም ለዚህ ተግባር መሳካት ሁላችሁም የበኩላችሁን አስተዋፆ ታበረክቱ ዘንድ እንደ ሁል ጊዜዉ የኦንላይን እጣ ትኬት አዘጋጅተናል ። እናም እነዚህን ትኬቶች በመግዛት እዚህ የበረከት ስራ ላይ የበኩላችሁን ታበረክቱ ዘንድ በቅንነት ስም እንጠይቃለን

የትኬት ዋጋ : 15 ብር ብቻ !

እጣዉ : ከአንድ እስከ ሶስት የተካተቱ እጣዎች ሲኖሩ እጣዉ ምንድነዉ ለሚለዉ በእለቱ ይፋ የሚደረግ ይሆናል ምክንያቱም ከእጣዉ ይልቅ አላማዉን አግዝፈን እንድንሳተፍ ስለሚፈለግ ! ትልቁ እጣ ግን ሁላችን ከዚህ መልካም ተግባር በሁአላ የምናተርፈዉ የመንፈስ እርካታ ነዉ

ትኬቶችን ለማግኘት
@God_with_me26 ላይ ያናግሩኝ

ቅንነት በጎፈቃደኞች