Get Mystery Box with random crypto!

በርካታ ቁጥር ያላቸው የቻይና ወታደሮች ሩሲያ ገቡ የቻይና ጦር በሩሲያ ግዛት ውስጥ በሚካሄደው ወ | ሁሌ አዲስ ሚዲያ (Hule Addis Media)

በርካታ ቁጥር ያላቸው የቻይና ወታደሮች ሩሲያ ገቡ

የቻይና ጦር በሩሲያ ግዛት ውስጥ በሚካሄደው ወታደራዊ ልምምድ ላይ ለመሳተፍ በትናትናው እለት ሞስኮ መድረሱ ተነግሯል።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ትናንት በለቀቀው የቪዲዮ ምስል ላይ የቻይና ጦር ለግዙፉ ወታደራዊ ልምምድ ዝግጅት ሩሲያ መድረሱን ያሳያል።

ቮስቶክ 2022 የሚል መጠሪያ የተሰጠው ወታደራዊ ልምምድ ከነገ ጀምሮ ለ7 ቀናት በሩቅ ምስራቅ ሩሲያ እና በጃፓን ባህር ላይ የሚካሄድ መሆኑ ተነግሯል።

ቻይና እና ሩሲያን ጨምሮ ስድስት ሀገራት የጦር ልምምድ ሊያደርጉ መሆኑን አስታወቁ
በዚህ ወታደራዊ ልምምድ ላይ አዘጋጇ ሩሲያን ጨምሮ ቻይና፣ ቤላሩስ፣ ታጃኪስታን፣ ህንድ፣ ሞንጎሊያ እና ሌሎችን ሀገራት ይሳተፋሉ ተብሏል።

ለወቅታዊ እና ለፈጣን መረጃዎች የሁሌ አዲስ ሚዲያ የማህበራዊ ሚዲያዎችን ይቀላቀሉ።

Facebook : https://www.facebook.com/Huleadissmedia/
Telegram : https://t.me/Hulaadiss
YouTube Channel
https://www.youtube.com/channel/UCk934znIu60LV3czcIVZ9Bg
Twitter: https://twitter.com/Huleaadis_Media