Get Mystery Box with random crypto!

ሁሌም የውስጥ ሰላምህን ጠብቅ 'አንድ ሰው በራሱ ጉዳይ ተረብሾ መጥቶ ቢለክፍህና አሉታዊ በሆነ መ | Hoora cast/talent Factory

ሁሌም የውስጥ ሰላምህን ጠብቅ

"አንድ ሰው በራሱ ጉዳይ ተረብሾ መጥቶ ቢለክፍህና አሉታዊ በሆነ መንገድ ቢናገርህ እራስህን መቆጣጠር እንጂ መናደድ የለብህም፤ የመጣው ሰው ሁሉ እንዲያናድድህ፤ የመጣው ሰው ሁሉ እንዲያቃጥልህ፤ የመጣው ሰው ሁሉ እንዲያሳብድህ በፍፁም አትፍቀድ፤ አንተ የትልቅ ሕልም ባለቤት ነህ፤ እንዴት የትልቅ ሕልም ባለቤት የሆነ ሰው የውስጡ ሰላም እንዲረበሽ ይፈቅዳል? የራስህን ሰላም ሌላ ሰው በሚያደርገው ድርጊት በመናደድና ምላሽ በመስጠት የምትለወጥ ከሆነ፤ የደስታህን ቁልፍ ለሌላ ሰው በፈቃድህ ሰጥተሃል ማለት ነው፤ ስለዚህ የሰላምህ በር ቁልፉ ምንግዜም በራስህ እጅ ብቻ ይሁን"

ዳዊት