Get Mystery Box with random crypto!

እመቤታችን ድንግል ማርያም በገዳም አባቶች በኩል ለኢትዮ | Holy mood pic memory

እመቤታችን ድንግል ማርያም በገዳም አባቶች በኩል ለኢትዮጰያ ህዝብ የላከችው ።
በስመ አብ ወወልድወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ ኣምላክ ፣ለምወዳችው እና ለምትወዱኝ ኢትዮጵያውያን ልጆቸ በሙሉ ይህ መልዕክት ይድረሳችሁ።ኢትዮጵያ የአስራት ሀገሬ ፤ኢትዮጵያዊያንም በጣም የምወዳችሁ ልጆቸ ናችሁ።ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰሩ ኃጢኣቶች ከመቸውም ጊዜ የከፉና እጅግ የበዙ በመሆናቸው የተቀደሰችው ሀገር በኃጢአት ረክሳለች።ምድሪቱም እንደ ኖኅ ዘመን በእግዚአብሄር ፊት በግፍ ፣በመተት፣በጭካኔ፣በዝርፊያ እና በቅሚያ ፣በዝሙትና በግብረሰዶማዊነት ፣ፈጽማ ረክሳለች። እኔ ሁልጊዜ ኢትየጵያን እንዲምራት ባልጸልይ ኖረ እንዲሁም ሌሎች ወዳጆቸ ቅዱሳን ስለ ኢትዮጵያ ባይጸልዩ ኖሮ ከብዙ ዘመናት በፊት ልጀ በመቅሰፍቱ ባጠፋችው ነበር ።አሁን ግን ጥንቆላው እና መተቱ ፣ግፉና ጭካኔው ፣ቅሚያውና ዝርፊያው ፣ዝሙቱና ግብረሠዶማዊነቱ ፣ከልክ አልፎ የኃጢአት ጽዋው ስለሞላ መቅሠፍቱ እየወረደ ነው ።መቅሠፍቱ ገና መጀመሩ ነው ።ይሁን እንጅ በኔ ልመና የንስሐ ጊዜ እየሰጣችሁ ነው ።ስለዚህ ከመቅሠፍቱ ለመዳንና የኢትዮያን ትንሣኤ ለማየት የምትፈልጉ ሁሉ ባስቸኳይ ተለወጡና ንስሐ ግቡ ። እኔ ሳላቋርጥ ስለናንተ እያማለድኩ ነው ።እናንተ ግን ልባችሁ እንደ ድንጋይ ከጠጠረና ከክፉ ሥራችሁ አንመለስም ካላችሁ መጥፋታችሁ አይቀርም ።ልጀ መመንጠሪያውን ይዞ ስለተነሣ አንመለስም ያሉትን በሙሉ ይመነጥራቸዋል ።ክፉ ሥራችሁን ሣትተው ቤተክርስቲያን በመሄድ ፣በመፆምና በመጸለይ ፣እንዲሁም ገንዘብ ለቤተክርስቲያንና ለችግረኞች በመስጠት የምትማሩ የሚመስላችሁ አላችሁ ።ከላይ የተጠቀሱትን ኃጢአቶች እና ርክሰቶች ሳትተው የምታደርጉት ፆምጸሎትና የምትሰጡት ምጽዋት ሁሉ ከንቱ ነው ።በጥንቆላ ፣በመተት ፣በቅሚያ ፣በግፍ ፣በጉቦ ፣በዝሙት ፣እንዲሁም የጭፈራና የዝሙት ቤቶች ከፍቶ ሠውን ኃጢአት በማሠራት የተገኘ ገንዘብ በእግዚአብሄር ፊት የረከሠ ስለሆነ በጭራሽ ከይቀበለውም ።ንስሐ መግባት የምትችሉት የምትሠሯቸውን ኃጢአቶች አቁማችሁ ፣የተጣላችኋቸውን ሠዎች በሙሉ ታርቃችው ፣ከሠዉ የወሰዳችሁትን ገንዘብም ሆነ ንብረት መልሳችሁ ፣እንዲሁም ጨሌና ሌሎችየማምለኪያ ነገሮች በሙሉ ጥላችሁና በጠንቋይ ታዛችሁ ያደረጋችሁትንና የቀበራችሁትን በሙሉ ጥላችሁ እና ትታችሁ መሆን አለበት ።አለዚያ ንስሐችሁ ተቀባይነት የለውም ።ከንስሐም በኋላ ሁለተኛ ላለመበደል ጥረት ማድረግ ይገባል ።ይሁን እንጅ ሠው ደካማ ስለሆነ ድንገት ብትሳሳቱ ወዲያውኑ እንደገና ንስሐ መግባት አለባችሁ ።ይህ ከሆነ እኔ ከናንተ ጋር ስለሆንኩ ምንም ነገር አይነካችሁምና አትፍሩ ።ከናንተ መሀል አንዳንዶቻችሁ ለሰማዕትነት ተጠርታችኋል ።እናንተም ለታላቅ ክብር የተመረጣችሁና የታደላችሁ ናችሁ ።ከዚህ በታች የተገለጹትን ኃጢአቶች የምታደርጉ ሁሉ ባስቸኳይ መለወጥ አለባችሁ ።
1.ጠንቋይ ፣አዋቂ ፣ቃልቻ ፣ባለውቃቢ ፣ወዘተ እያላችሁ እየሄዳችሁ የምታስጠነቁሉና መተት የምታደርጉ ሁሉ ሳይጣንን እያመለካችሁ እንደሆነ እወቁ ።የእናንተ ፆም፣ ጸሎትና ፣ምጽዋት እንዲሁም ለቤተክርስትያን የምትሰጡት ገንዘብ ፣አንዱንም እግዚያብሔር አይቀበለውም ።ይህንን የረከሠ ስራ ትታችሁ ባስቸኳይ ንስሃ ካልገባችሁ ልጀ ሁላችሁንም ሊያጠፋችሁ ተዘጋጅቷል ።
2.የገንዘብ ፍቅራችሁ ከልክ ያለፈ በመሆኑ ሌላው ቀርቶ በጣም የቅርብ ቤተሰቦቻችሁ እና ዘመዶቻችሁ ላይ ሳይቀር ለገንዘብ ስትሉ ግፍ ትሠራላችሁ ።ባሁኑ ጊዜ ከናንተ ብዙዎቻችው የምታመልኩት ገንዘብን ነው እንጅ እግዚአብሔርን አይደለም ፤አሁን ግን ያለፈው ይብቃችሁ እና አላግባብ ከሠው የወሠዳችሁትን ገንዘብና ንብረት አንድም ሳይቀር መልሱና ንስሐ ግቡ ።ምንም ያህል የቆየ ቢሆን አላግባብ ከሠው የተወሠደ ገንዘብና ንብረት መመለስ አለበት ።የናንተ ንፁህ ሠርታችሀ ያገኛችሁትና በውርስና በተለያየ መንገድ እግዚያብሔር የሠጣችሁ ብቻ ነው ።የተሠረቀና የተቀማ ንብረት የኃጢአት ገንዘብ ነው ።ከሠውና ከሌሎች ቦታዎች አላግባብ የወሰዳችሁትን ሳትመልሱ ንስሀ መግባት አትችሉም ።የቀማችሁትን ካልመለሳችሁና ንስሐ ካልገባችሁ በልጀ መመንጠሪያ ትመነጠራላችሁ ።
3.ወጣቶች ሴቶችና ወንዶች ከልክ ያለፈ በዝሙት ኃጢአት ረክሳችኋል ።ሴቶች የኔ ምሳሌና የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሆናችሁ ክብር ፍጥረታት ናችው ።ነገር ግን ከናንተ ብዙዎቹ ክብራችውን ንቃችዉና አዋርዳችው የዲያቢሎስ ማደሪያ ሁናችዋል ።ሰይጣን የሚስተምራችሁን ያለባበስ አይነቶች ያለምንም ሀፍረት እየተከተላችሁ ወንዶችን ከመፈተናችሁም በላይ ምድሪቱ በዝሙት እንድትረክስና የብዙዎች ትዳር እንዲፈርስ ምክንያት ሆናችኋል ።ስለዚህ ባስቸኳይ ተለወጡና ንስሀ ግቡ ።ጭን ፣እንብርትና ጡት የሚያሳዩ ቀሚሶች ፣ሰውነትን እንደ መስታውት የሚያሳዩ ስስ ቀሚሶችና ሸሚዞች ፣የሠውነትን ቅርፅ አንድበአንድ የሚያሳዩ ሠውነት ላይ የተጣበቁ ሱሪዎችና በየቦታው የተተለተሉ ሱሪዎችን የመሳሰሉ ሠውነትን የሚያጋልጡ ልብሶች በአጠቃላይ ሰይጣናዊ አለባበስ ስለሆኑ ይህንን አንተውም ያላችው ሁሉ ቅጣታችሁን ትቀበላላችሁ ።ክርስቲያናዊ አለባበስ ከጉልበት በደንብ ዝቅ ያሉ ቀሚሶች እስከአንገት ድረስ የሚሸፍኑ ሸሚዞች ወይም ልላ ተመሳሳይ ልብሶች ፣የሠውነትን ቅርፅ የማያሳዩ ሰፋፊ ሱሪዎች የመሳሰሉት ናቸው ።ወንዶች የጫትና የሲጋራ እንዲሁም የመጠጥ ሱሳችሁን አቁማችሁ በጊዜ ወደየቤታችሁ ግቡ ።የትዳር ጓደኛ ይዛችሁ በአንድ ሴት እርጉ ።የዝሙት ሱስ ያደረባችው ሠዎችና ግብረሠዶማውያን በነፍስም በስጋም ጠፍታችኋል ።ስለዚህ ከዚህ ለመዳን ንስሀችውን ቸናዛችሁ በቀን አንዴ ቀላል ምግብ እየበላችሁ በቀን በቀን ጸበል መጠመቅ አለባችሁ ።ብትችሉ ወደ ገዳም ሄዳችሁ በፆም በጸሎትና በስግደት የዝሙቱና የግብረሰዶሙ አጋንንት እስኪለቃችሁ ታገሉ ፤ካልቻላችሁ ባላችሁበት ሁናችሁ በፆም በጸሎትና በስግደት እየደከማችሁ ጸበል ተጠመቁ ።ይህ ሲሆን ቀስ በቀስ ያደረባችሁ አጋንንት ይለቃችኋል ።ዘማውያን ሁሉ ካልቸመለሳችሁ መጥፊያችሁ ደርሷል ።
አሁን የልቅሶና የንስሀ ጊዜ ነው ።ከዚህ መቅሰፍት ለመዳን የምትፈልጉ ሁሉ መዝናናታችሁን አቁማችሁ ንስሀ ገብታችሁ ስለ ኃጢአታችሁ አልቅሱ ።አሁን የሀዘን ጊዜ ስለሆነ ዘፈን ማዳመጥ ይቅርና በሱ ፈንታ መዝሙርና ስብከት ብቻ አዳምጡ ።ሁላችሁም ከልብ ከተመለሳችሁ ባጭር ጊዜ ምህረት ታገኛላችሁ ።አለዚያ ግን የመከረው ጊዜ ይረዝማል ።ከዚያም የተመለሱትን አድኖ እምቢተኞችን ያጠፋቸዋል ።ይህንን መልዕክት ተቀብላችሁ ስራ ላይ ለማዋል ልቦናችውን ይክፈትላችው ።


1.ይህንን መልክት ቢያንስ ለ7 ሰው አብዝታችሁ ስጡ ።ብትችሉ ለ14 ፣ለ 21 ፣ወይም ለ40 ሰው አባዝታችሁ ብትሠጡ ህይወታችሁ ይስተካከልላችኋል ።እንዲሁም የተለያዩ ታምራት ታያላችሁ ።አንዲት ሴት መልዕክቱ እንደደረሳት ህይወቷን ለውጣ ንስሀ ገባች ።ከዚያም ለ40 ሰዉ አባዝታ ሰጠች ።በዚህ ጊዜ ትልቅ ታምራት በገሀድ አየች ።ሌሎች ከ7ሰው ጀምሮ አባዝተው የሰጡ ሠዎች የተለያዩ ታምራት እያዩ ነው ።
2.አንድ ሰው ይህንን መልዕክት አንብቦ ቀዶ ጣለው ፤ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ህይወቱ ተመሰቃቀለበት ።
የተዋህዶ ልጆች ሆይ ይህ መልዕክት በወረቀት ነበር ፤ ነገር ግን ለብዙ ሰዎች እንዲዳረስ ብየ ነው በዚህ የጻፍኩት ።እናም አይዞን አይዞን አይዞን እናታችን ሁሌም ከጎናችን ናት ፤ከኛ የሚጠበቀው የተባልነውን መፈፀም ብቻ ነው ።አማላጅነቷ ከእኛ