Get Mystery Box with random crypto!

ዮም ሠረቀ ለነ ወርኃ መስከረም ቡሩክ ወዘመነ ማርቆስ ሐዋርያ ያብጽሐነ እስከ ዘመነ ሉቃስ በዳኅና | አቡሻኽር

ዮም ሠረቀ ለነ ወርኃ መስከረም ቡሩክ ወዘመነ ማርቆስ ሐዋርያ ያብጽሐነ እስከ ዘመነ ሉቃስ በዳኅና ወበሰላም
"ሰላም ለስዕርተ ርዕስከ እንተ ደለዎ እኳቴ፤ ወለርዕስከ ሰላም ዘተመትረ ከመ ናቡቴ ። ርእሰ ዓውደ ዓመት ዮሐንስ ወላዴ መጥቅዕ ወአበቅቴ ። መብልዕ ዜና ፍቅርከ ወነገነ ቃልከ ስቴ። ያስተፌሥሕ መላእክተ ወሰብአ መዋቴ።
እንደ ናቡቴ ለተቆረጠው ራስህ እና ምስጋና ለሚገባው የራስህ ፀጉርህ ሰላምታ ይገባል አበቅቴንና መጥቅዕን የምታስገኝ የዓውደ ዓመት ርእስ (አለቃ) ዮሐንስ የፍቅርህ ዜና ምግብና የቃልህ ነገር መጠጥ የሚሞት ሰውንና መላእክትን ያስደስታል" መልክዓ ዮሐንስ

እንቋዕ አብጽሐክሙ መትልዋነ ምኅላፍነ
የምኅፋችን( ቻናላችን )ተከታታዮች እንኳን አደረሳችሁ ።