Get Mystery Box with random crypto!

እኔነቴን ላድምጥ እስኪ ራሴን ላዳምጥ እኔን እኔ ልስማው ፤ ሲናገረኝ ቢውል አላውቅም አምኜው ግን | ስለ -ህይወት 👉🎤🎧📒📗📖

እኔነቴን ላድምጥ

እስኪ ራሴን ላዳምጥ
እኔን እኔ ልስማው ፤
ሲናገረኝ ቢውል
አላውቅም አምኜው
ግን እኔ ለራሴ ስነግረው እውነቱን
ቢሰማኝ ባይሰማኝ
ባይረዳው ሀቁን፤
እኔነቴ ከቶ መናገሩን አይተው፣
ይተነፍሰዋል ማንም አያቆመው::
ታዲያ እኔነቴን ማዳመጥ ሲሳነኝ
ከንቅልፌ ስባንን ሁሌም ተጠቂነኝ፡፡
ደምቼ ቆስዬ፣ ተፈነካክቼ
ድንግት እነቃለሁ፣ እኔነቴን ስቼ
ግን ግን እኔነቴ በዚህ ሳይከፋ
መናገሩን አይተው በመደመጥ ተስፋ
እስቲ አደብ ልግዛና እኔን እኔ ልሰማው
አንዳንድ ቀን እንኳን እራሴን ልመነው
ነፍሱ በሱነቱ ሁሌም ሀቅን ይዛ እየነገረችው
ሰው የፊት የፊቱን ዝብርቅርቁን አለም በልጦ ያዳመጠው፣
አለ በመከራ
በስህተት ጐተራ፣
ሁሌ እንደማቀቀ
ከውነት እንደራቀ ::
ከመላው አለሙ ከሚተራመሰው
ከዚህ ሁሉ ፍጥረት ወድቆ የሚቀረው፣
የነፍሱን ኡኡታ ማዳመጥ ያቃተው፣
እሱነቱ ነግሮት ያልሰማ ብቻ ነው::

@historysharee