Get Mystery Box with random crypto!

ለ1,704 ሴቶችን የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ ድጋፍ ተደረገ። ሂራ የልማትና መረዳጃ ተቋም ከምርኩዝ | ሂራ የልማት እና መረዳጃ ኢንስቲትዩት

ለ1,704 ሴቶችን የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ ድጋፍ ተደረገ።

ሂራ የልማትና መረዳጃ ተቋም ከምርኩዝ ቤተሰብ (ምርኩዝ 18 መድረክ) የሰበሰበውን ብር የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ግዢ በመፈፀም ለተፈናቃይ ወገኖች እንዲደርስላቸው ለነጃሺ የበጎ አድራጎት ድርጅት አስረከቡ።

ሂራ የልማትና መረዳጃ ተቋም በጊዜያዊ የነጃሺ በጎ አድራጎት ድርጅት መጋዘን በመገኘት የሴቶች የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ ( 71 ካርቶን) ለነጃሺ የበጎ አድራጎት ድርጅት ቦርድ አመራር ጋር በመሆን ለወገኖች እንዲደርስ ርክክብ አድርገዋል።

በርክክቡ ላይ የሚንበር ቲቪና የምርኩዝ መድረክ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ድጋፍ ላደረጉ የምርኩዝ ቤተሰቦች አመስግነዋል። ድጋፉም ለ1,704 ሴቶችን ተጠቃሚ ያደርጋል።

መስጠትን ይስጠን