Get Mystery Box with random crypto!

ሑጃጆች ልብ ይበሉ! የቂራን ወይም የተመቱዕ እርድ ግዴታ የሆነበት ሰው የማረድ አቅም እያለው ማ | Hijra Tube [Official]

ሑጃጆች ልብ ይበሉ!

የቂራን ወይም የተመቱዕ እርድ ግዴታ የሆነበት ሰው የማረድ አቅም እያለው ማረዱን ትቶ መጾም አይፈቀድለትም::
ምክንያቱም የቁርኣን አንቀጹ "የሚያርደውን እንሰሳ ያላገኘ... ይጹም" ነውና የሚለው። -(አልበቀረህ 196-)
ማረድ እየቻሉ ወደ ጾም መሸጋገር የሚቻለው እንደ- ጸጉርን መላጨት፣ ሽቶ መቀባትና ወዘተ. መሰል በኢሕራም ምክንያት የተከለከሉ ነገሮችን ላደረገ ሰው ነው።
ገንዘብ እያለ በመሰሰት ወይም ገዝቶ እራስ ማረድን እንኳ ባይችሉ ፈቃድና እውቅና ላላቸው ተወክለው ለሚያርዱ ተቋማት አለመስጠት ሐጅ/ዑምራን ያጎድላል (ወንጀለኛ ያደርጋል)።
ልክ እንደዚሁ የሐጅ ቀናት ሳይጠናቀቁ በፊት መጾም አለበት የተባለን ጾም በግዴለሽነት ሳይጾም የሐጅ ቀናት ያለቁበት ሰው ወንጀለኛ ይሆናል።
ፈጥኖ መቶበትና ጊዜው ቢያልፍም ያለበትን ጾም መክፈል ይኖርበታል።

ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም
@ዛዱል መዓድ
           


https://telegram.me/ahmedadem

"ዒልም ማለት አላህን መፍራት ነው!
አል-ኢማሙ ማሊክ