Get Mystery Box with random crypto!

. ተስፋ አትቁረጥ በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ልትወድቅ ትቸላለህ፣ ሰዎች ላ | የሂዲ ❤ ፅሁፎች

. ተስፋ አትቁረጥ

በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ልትወድቅ ትቸላለህ፣ ሰዎች ላይረዱህ ፣ ቦታ ላይሰጡህ፣ ስም ሊያወጡልህ ፣ አሊያም ሊስቁብህ ፣ ይችላሉ ግን ልብህ ቅንና ሀሳብህ መልካም ይሁን። ህልምህን ለማሳካት ተስፋ አትቁረጥ! ጊዜ ሊወስድ ይችላል ፣ ዋጋ ሊያስከፍልህ ይችላል ፣መስዋእት የምታደርጋቸው እና የምትተዋቸው ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ያሰብከውን እስክታገኝ መንገዱ ቀላል አይደለም ፣ በህልምህና ዛሬ ባለህበት
ህይወት መካከል ያለው ልዩነት ህልምህን ተራምኞት ያስመስለው ይሆናል ግን ልንገርህ በዚህ ምድር ላይ ካንተ በቀር አንተን ሊያስቆም የሚችል
ኃይል የለም ፣ አንተ አይምሮህን ካሳመንከው ታደርገዋለህ!
ዞር ዞር ብለህ ብታይ በዙርያህ ያሉት ነገሮች በሙሉ ከመሆናቸውና ከመታየታቸው በፊት ሐሳብ ነበሩ ፣ ለብዙዎችም እብደት እና ሞኝነት ይመስላቸው የነበረነው። ልክ እንደዛ ብዙሃኑን መምሰልም አይጠበቅብህም ስትፈጠርስ ብቻህን አይደል የተፈጠርከው ያንተ ሐሳብ ከዚህ ብዙ የራቀ አይደለም ሞክር ፣ ደጋግመህ ሞክር አንዱ እምቢ ቢልህ በሌላው ፣ መንገድህን እየቀያየርክ ፣ ያልተሞከሩ መንገዶችን እየሞከርክ ፣ አይንህን እና ጆሮህን ለመፍትሔ እንጂ ለተራ ወሬ እና አሉባልታ ሳትሰጥ፣ ሀሳብህ ሳይበታተን ፣ የሚጎድልህን ችሎታ እና እውቀት ተማር

አንድ ቀን በሄደ ቁጥር ወደ ህልምህም ወደ ሞትህም እየተጠጋህ ነውና ሌላው ትርፍ ነው። በመጨረሻዋ ሰዓት አንተ እና አንተ ሆናችሁ የምትነጋገሩት ነገር በህይወትህ ማድረግ እያለብህ ስላላደረከው፣ስላባከንከው ጊዜ እና ተሰጥኦ ነው እንጂ ስለሰዎች
አይደለም። እናም ተስፋ ሳትቆርጥ የተመኘኸውን ፣በህይወትህ ማድረግ ያሰብከውን አድርግ።