Get Mystery Box with random crypto!

HAppy Mûslim

የቴሌግራም ቻናል አርማ heppymuslim29 — HAppy Mûslim H
የቴሌግራም ቻናል አርማ heppymuslim29 — HAppy Mûslim
የሰርጥ አድራሻ: @heppymuslim29
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.25K
የሰርጥ መግለጫ

ONLY SHORT ISLAMIC STORY‼️
Fôr Any Cømments👉 @HappyMuslim29bot

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 23:23:18 ➳ቢክራነት(ልጃገረድነት)እና ሴት እህቶቻችን



አሁን ላይ ቢክራ ( ልጃገረድ ) እንስቶች እንደ ዳይኖሰር ከምድረ ገፅ ከጠፉ ሰነባብተዋል የሚል ወሬ በረጅሙ ይናፈሳል ፡፡ ተጨባጩን ያስተዋሉ ደግሞ " የለም , ሙሉ ለሙሉ እንኳ አልጠፉም ፡፡ ባይሆን እንደኛዎቹ ዋልያዎች ብርቅዬ ናቸው " ሲሉ ይደመጣሉ ፡፡
የሆነው ሆኖ ሴቶቻችን ከዚህ በፊት የሚታወቁበት ቁጥብነትና ጨዋነት ርቋቸዋል ፡፡ በምትኩ ስርዐት አልበኝነትን መርጠው የማንም መጫወቻ እየሆኑ ነው ፡፡
ከአለባበስ ጀምሮ አካሄዳቸውንና የአነጋገር ስልታቸውን ያስተዋለ ጥሩ ተጨባጭ ላይ እንዳልሆኑ ይገለጥለታል ፡፡ ካፊሯ ላይ የማይስተዋለውን ደማማቅ ቀለማትና ሙሉ የሰውነት ቅርፅን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ቀሚስ ለብሳ አውራ ጎዳናውን የምታዥጎደጉደው የኛው እህት ነች ፡፡
አይደለም እንዴ ?
( ዋ ! አይደለም ብለህ ትዋሽና በብሎክ እንዳላሰናብትህ )
ወሏሂ ግን ሴቶችዬ በጣም እኮ ነው ያበዛችሁት ፡፡ አልታወቃችሁም አይደል ?
እንደው ጉዳችሁን እዚህ ህዝብ ፊት አልዘረግፈውም እንጂ በጣም መስመር ስታችኀል ፡፡
'
ከዚህ በፊት ቢክራነት ( ልጃገረድነት ) ትልቅ ክብር ነበረው ፡፡ እርሱን ለመጠበቅና በተገቢው ቦታ ለማኖርም ትልቅ ተጋድሎና ትንቅንቅ ይደረግ ነበረ ፡፡ አሁን ግን አንዲት እንስት ቢክራነቷን በሶስት ኪሎ ስኳር እንዳትቀይር ሁላ ይስሰጋል ፡፡ በቃ እንደውም አንዳንድ ቦታዎች ላይ ቢክራነት እንደፋርነት ሁላ እየተቆጠረ ነው ፡፡ አጂብ !
ታላቋን የምዕመናት ሞዴል የዒሳ ዐለይሂ ሰላም እናት የሆነችው መርየም ዐለይሃ ሰላም ዝንተ ዐለም በቁርዐን ስትወደስ የምትኖረው ቢክራ ስለነበረች እንጂ ከቶስ ሌላ ለምንድነው ?
ጌታችን አልሏህ ﷻ መርየም ዐለይሃ ሰላምን አስመልክቶ በተከበረው ቃሉ ( ቁርዐን ) እንዲህ ሲል እስከ ዕለተ ቂያማ የሚዘከርን ውዳሴ አውርዶላታል
'
وَإِذْ قَالَتِ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ يَٰمَرْيَمُ إِنَّ ٱللَّهَ ٱصْطَفَىٰكِ وَطَهَّرَكِ وَٱصْطَفَىٰكِ عَلَىٰ نِسَآءِ ٱلْعَٰلَمِينَ
.
መላእክትም ያሉትን ( አስታውስ ) ፡፡ « መርየም ሆይ ! አላህ በእርግጥ መረጠሽ ፡፡ አነጻሽም ፡፡ በዓለማት ሴቶችም ላይ መረጠሽ ፡፡ »
ሱረቱ አል ዒምራን 42
'
እነዚህ " ፋራ " ባይ ሰገጤዎች ያልተረዱት አንድ ትልቅ ቁም - ነገር አለ ፡፡ እርሱም ዛሬ ላይ ቢክራነቷን ጠብቃ የጨዋነት አክሊልን የሙጥኝ ያለችው እህት ልክ እንደሌሎቹ " አተራማሽ " እንስቶች የፈለገችውን ማድረግ ትችላለች ፡፡
አትችልም ?
ቀላል እኮ ነው ፡፡ ነገር ግን ያቺ ክብሯን ለማንም ወፈፌ ሲሳይ ያደረገችው እህት ግን ዳግም ክብሯን ልመልስ ብትል ሰማይ ትቧጥጣታለች እንጂ #ሙስተሂል ነው ፡፡
እና ታድያ ፋራው ማን ነው ?
'
እህ .... ቢክራ ሆኜ ምን አደርግበታለሁ ( ? ) ካልሽ , ያልገባሽ ሌላ ተጨማሪ ትልቅ ቁም ነገር አለ ማለት ነው ፡፡ እርሱም , አብዝሃኛው የሙስሊም ወንዶች ለቢክራነት የሚሰጡት ትኩረት በጣም የተለየ ነው ፡፡ ምንም እንኳ ከዚህ ቀደም የስድስት እንስትን ቢክራነት የገረሰሰ ቢሆንም ትዳር ሲያስብ ግን ማንም ያልተጨማለቀባትን ንፁኀን ቢክራዋን ይመኛል ፡፡ ለምን ( ? ) ስትዪው .... ኧረ ማንም የተጨማለቀባትን እኔ ምን ልትሰራልኝ ብሎ በድፍረት ይመልስልሻል ፡፡
በአጭሩ ምን ልልሽ ፈልጌ መሰለሽ .. ቢክራነትሽን እንደ ቀልድ ካስረከብሽ በኀላ የትዳርሽ ጉዳይ ፍፁም አሳሳቢ ይሆናል ፡፡ ውጫዊ ገፅታሽን ተመልክቶ ለትዳር ሲመለምልሽ በመጀመሪያ የሚጠይቅሽ ቢክራነትሽን ነው ፡፡

ባለማወቅም ሆነ በማወቅ ይህን ቢክራነት ካጣን ለሚመጣው ወንድ
ለትዳር ያለውን ነገር በግልጽ መነጋገር
መልካም ነው።

ቢክራ ነኝ ብዬ ሸውጄ አገባዋለሁ ... ብለሽ እንዳታስቂኝ ፡፡ እህቴ ስንቶች ይህንን የጅል ቀመር ተጠቅመው አበሳቸውን እያዩ መሰለሽ ፡፡ ቢክራ መሆኗን ተናግራ ከተጋባች በኀላ ባል ሆዬ ፈልጎ ሲያጣ ሚስት ላይ ከፍተኛ ጫናና የጥላቻ ስሜት ማንፀባረቅ ይጀምራል ፡፡ ባገኘው አጋጣሚም ሞራሏን የሚያደቅበትንና ቂሙን የሚበቀልበትን ሁኔታዎች ያመቻቻል ፡፡ እንደውም አንዳንዱ በዚያው የመጀመሪያ የጫጉላ ምሽት " አይንሽን ላፈር ካጠገቤ ዞር በይ " ይላል።

አላህ ትክክለኛውን መንገድ ይምራን
መልካምን ነገር ከሚያወሩት ሳይሆን
ከሚተገብሩት ያርገን።
https://t.me/Al_Islam_Media_Et
533 viewsعرفات ابن صادق, 20:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 14:49:04 ታላቁ ሰሓባ ዐብዱላህ ኢብኑ ሑዛፋ ረ.ዐ. ከእስልምና በፊት ምንም ጥረትም ሆነ አስተዋጽኦ አልነበረውም፡፡ የአላህ ፈቃድ ሆነና እስልምናን ተቀበለ፡፡ ከሰለመ በኋላ በምርኮነት በሩም ንጉስ እጅ ወደቀ፡፡ ንጉሱም ሊገድለው አሰበ፡፡
‹ሃይማኖትህን የምትተው ከሆነ ይህን ያህል ሀብት እሰጥሃለሁ፡፡› አለው፡፡
ሑዘይፋም ‹በአላህ እምላለሁ ሃይማኖቴን እንድተው ብለህ ሙሉ ሀብትህን ብትሰጠኝ የምተው አይደለሁም፡፡› አለው፡፡
ቀጥሎም ‹ሃይማኖትህን ከተውክ ከሥልጣኔ አካፍልሃለሁ፡፡› በማለት ሊያግባባው ሞከረ፡፡
ሑዘይፋም ‹በአላህ እምላለሁ የዚህ ዓለም ስልጣን ለኔ ምንም አይደለም፡፡› አለው፡፡
‹እንግዲያውስ እገድልሃለሁ፡፡› አለው፡፡
ሑዘይፋም ‹የሻህን መስራት ትችላለህ፡፡› አለው፡፡
ንጉሱ ጋሻጃግሬዎቹን ‹በቀስት ወጋጉትና አሰቃዩት፡፡ አትግደሉት፡፡› በማለት አዘዛቸው፡፡
ከፍተኛ ስቃይ እስኪሰማው ድረስ እጆቹን በቀስት ወጋጉት፡፡
‹ሃይማኖትህን ተው፡፡› በማለትም ጠየቁት፡፡
‹ወላሂ አልተውም፡፡› አላቸው፡፡
‹በቀስቱ እግሩን ወጋጉት› አላቸው፡፡
‹ሃይማኖትህን ተው፡፡› አሉት፡፡
‹ወላሂ አልተውም፡፡› አላቸው፡፡
ንጉሱ በመቀጠልም ‹ሁለት ባልደረቦቹን አምጡና በበርሜል ዘይት በማፍላት እዚያ ውስጥ ክተቷቸው፡፡› አለ፡፡ ከሱ ጋር የነበሩትን ሁለት ሙስሊሞች አመጡና ዐይኑ እያየ በፈላ ዘይት ውስጥ ከተቷቸው፡፡ አሁንም ጠየቁት፡፡
‹ሃይማኖትህን ተው፡፡ አለበለዚያ …› አሉት፡፡
‹ወላሂ አልተውም፡፡› አላቸው፡፡
‹በሉ ውሰዱና ዘይቱ ውስጥ ክተቱት፡፡› አላቸው፡፡
ሊከቱት ወደ በርሜሉ ሲያስጠጉት ታላቁ ሑዘይፋ ረ.ዐ. አለቀሰ፡፡
ሰዎቹ ይህንኑ ለንጉሱ ነገሩት፡፡ ንጉሱም ‹መልሱት ወዲህ› አላቸው፡፡ መልሰው አመጡት፡፡
ንጉሱም ‹ማልቀስህ ተነግሮኛል፡፡› አለው፡፡ ሑዘይፋም ‹አዎን› አለው ለንጉሱ፡፡
‹እንግዲያውስ ሃይማኖትህን ተው፡፡› አለው፡፡
‹ወላሂ አልተውም፡፡› አለ፡፡
‹እንግዲያውስ ለምን አለቀስክ?› አለው፡፡
‹በአላህ መንገድ የምሰጠው ነፍስ አንዲት ብቻ መሆኗ ነው ያስለቀሰኝ፡፡ በሰውነቴ ላይ ባለው ፀጉር ልክ ነፍስ ቢኖረኝና በአላህ መንገድ አንድ በአንድ ብሰጥ እመኝ ነበር፡፡› አለው፡፡

@heppymuslim29
1.3K viewsɯɐɥlǝ, 11:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 23:47:30
ሴቶች እንኳን ደስ አላችሁ!

ለሴት ልጅ ያስፈልጋታል ተብሎ የሚታሰበውን ነገር ሁሉ የያዘ ገራሚ ቻናል ተቀላቀሉ

ለኛው ለሴቶች ብቻ

አንቺም ከታች #JOIN የሚለውን አንዴ ብቻ በመንካት አባል መሆን ትችያለሽ።
አንተም ለሴት እህቶችህ #Share ማድረግ አትርሳ
65 viewsŹëbũrà Films, 20:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-28 10:19:30 የሰረቅኩት..!

ከቤት በጠዋት ነበር የወጣሁት 2 ሰዓት ላይ ለህክምና ቀጠሮ ስለነበረኝ እንዳላረፍድ በማሰብ ነበር በጠዋት የወጣሁት ከቀጠሮዬ ቦታ ከሰዓቱ ቀድሜ 1:40 ላይ ደረስኩ :: እዛው ቆይቼ በሰዓቴ ህክምናዬን ካከናወንኩ በኋላ በዚሁ ለምን መንጃ ፈቃድ አላድስም ብዬ ወደ መንገድ ትራንስፖርት አመራሁ እዛ እንደደረስኩ ወረፋ ስለነበረው ወረፋ እየጠበቅኩ ስልኬን ፍለጋ ወደኪሴ ስገባ ስልኬን አጣሁት ።

ስልክ ድንገት ከኪስ ሲጠፋ ስሜቱን ታውቁታላችሁ መቼም ። የት እንደጣልኩት ማሰብ ጀመርኩ ከሆስፒታሉ ስወጣ ሰዓት ለማየት ኬሴ ውስጥ እንዳወጣሁት አስታወስኩ ስለዚህ ታክሲ ውስጥ ሻሻ እንደሰሩኝ ገባኝ ። ቀድሞ አዕምሮዬ ላይ የመጣው እና የቆጨኝ ነገር ሃይደርን ከተወለደበት ቀን ጀምሮ ማስታወሻ ይሆናሉ ብዬ በየቀኑ የማነሳው ፎቶዎች መጥፋት ነበር ። በጣም የምወዳቸው ፎቶዎች ነበሩ ።

ወረፋዬን ጠብቄ መንጃ ፈቃዴን አድሼ ከመንገድ ትራንስፖርት ወጣሁ :: የሚገርመው ነገር የተፈጠረው የዛኔ ነው የሆነ ህፃን ልጅ ስልኩን እና የሆነ ወረቀት ሰጠኝ ስልኩን ሳየው የራሴ ስልክ ነው ። ከዛ ወረቀቱን ስከፍተው ስልኩን ለመስረቅ የተገደድኩት ልጄ ስለታመመብኝ ለአስቸኳይ ህክምና እና ለወተት ብር ስላስፈለገኝ ነበር ግን Wallpaper ላይ ካደረከው የልጅህ ፎቶ ላይ የፃፍከውን ፅሁፍ ሳየው የሆነ ስሜት ፈጠረብኝ እና ስልኩን መመለስ እንዳለብኝ ተሰማኝ ልጅ) ስላለህ ትረዳኛለህ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ በጣም ይቅርታ ልታግዘኝ ከፈለክ ግን በዚህ ስልክ ቁጥር ታገኘኛለህ ተብሎ ቁጥሩ ተፅፎበታል ።

በጣም አሳዘነኝ ምን አልባት እኔ በሱ ቦታ ብሆን ልጄ ቢታመምብኝ ለልጄ ቅድሚያ በመስጠት ስልኩን ሁሉ የምመልስለት አይመስለኝም ነበር ። በተፃፈው ቁጥር ደወልኩለት አነሳው ሰላም ካልኩት በኋላ ባለስልኩ መሆኔን ነገሬው እጄ ላይ ብር የለም ወተት የምትፈልግ ከሆነ ግን እቤት አለ ልላክልህ አልኩት እሺ አለኝ ስልኩን እና ወረቀቱን የሰጠኝ ልጅ አብሮኝ እንዲሄድ ነገረው ወደ ቤት እየሄድን አብሮኝ ከነበረው ልጅ ጋር ብዙ ነገሮችን አወራን ልጁ የምሩንም እንደሆነ ተረዳሁ ።

አሳዘነኝ ብችል እና እጄ ላይ ገንዘብ ቢኖረኝ ልጁን ባሳከምኩለት ግን ብር አልነበረኝም ። ቤት | እንደደረስን ለሃይደር የገዛሁት ግን አሁን ሃይደር እዚህ ስለሌለ የተቀመጡ 3 የቆርቆሮ ወተቶች ነበሩ እነሱን አብሮኝ ለመጣው ልጅ ሰጠሁለት እና ሄደ ። ቆይቶም ወተቶቹ እንደደረሱት ለሰራው ነገር ይቅርታ ጠይቆ እንደሚያመሰግነኝም ነግሮኝ እኔም አይዞህ ይሻለዋል ብዬው ስልኩን ዘጋሁት ።

ከመስረቁ በላይ ለልጄ ፍቅር Wallpaper ላይ በፃፍኩት ፅሁፍ ሀሳቡን ቀይሮ ስልኩን መመለሱ አስገረመኝ የልጅን ፍቅር ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው ነው ። ማጣት ከምንም በላይ የሚያመው ለልጅህ የሚያስፈልገውን ነገር ለማሟላት አቅም ሲያንስ ነው :: ስትወልድ የምትኖረው ለልጅህ ነው ለራስህ ማሰብ ታቆማለህ አባትነት ስሜቱ ጥልቅ ነው ለልጅህ ስትል የማይሆን ነገር ውስጥም ትገባለህ። አላህዬ ልለምንህ ማንም አባት ለልጁ ሲል አይቸግረው!! ልጁንም አላህ አፊያ ያድርግለት

@heppymuslim29
784 viewsɯɐɥlǝ, 07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 19:18:36 በቂያማ ትርምስ መሀል ድንገት ተጣሪ ስምህን ከሰዎች ለይቶ በጩኸት ይጠራኻል። ትርበተበታለህ፣ ትወለጋገዳለህ፣ እግሮችህ አንተን መሸከም ይሳናቸዋል።

ያሳለፍከውን የአመፅ ህይወት እያወራረድክ በመላዕክት ተቀፍድደህ ከተጠራህበት ስፍራ ላይ ብቻህን እንድትቆም ትደረጋለህ።

ስትፈራ፣ ስትቸር፣ ስትርበተበት አንገትህን አቀርቅረህ የምትገፈተርበትን የጀሀነም ሸለቆ እያሰብክ ሳለ ድንገት ከፊትህ መዛግብት ይዘረጋልኃል።

አንዱ መዝገብ የአይንህን አድማስ ተሻግሮ ትመለከተዋለህ። ጫፉን አታየውም፣ ትደነግጣለህ። የሱ ድንጋጤ ሳይለቅህ ሌላ ተመሳሳይ 99 መዝገቦች ከፊትህ ይዘረጋጋሉ።

ውስጡን እንድታይ ትደረጋለህ፤ ስትመለከተውም ከህይወት ጅማሬ እስከፍፃሜው የቀጠፍካቸው ወንጀሎች በሙሉ ሰፍረው መልካም ስራዎችህን ውጠዋቸው ታገኘዋለህ።

ተስፋ ትቆርጣለህ፣ አፍህ ይሎገማል፣ ጀሀነም ላይ ክፍል እንደተዘጋጀልህ ታስባለህ። ያኔ አፈር ሁነህ ብትቀርም ትልቁ ምኞትህ ይሆናል።

ድንገት የመዝገቦቹ ተሳሳቢህ፦‹‹የምታስተባብለው አለን?›› ሲል ይጠይቅኃል!
ተስፋ በቆረጠ አንደበት፦‹‹አላስተባብልም›› ብለህ በገዛ ነፍስህ ላይ ምስካሪ ትሆናለህ።

‹‹መዝጋቢዎቹስ በድለውኃልን›› ብሎ ዳግም ይጠይቅኃል?
አንገትህን እንዳቀረቀርክ፦‹‹አልበደሉኝም›› ትላለህ ስራህን ስለምታውቅ።

‹‹ታድያ በምን ታስተባብላለህ? ከዚህ ሚታደግህ መልካም ትግበራ ይኖርሃል? ›› ብሎ ይጠይቅኃል።

‹‹የለኝም›› ትላለህ ሁሉ ጨልሞብህ።
‹‹አንድ መልካም ስራ እኛ ዘንድ አለችህ፤ እሷም ትመዘናለች ዛሬ እኛ ዘንድ ማንም አይበደልም›› ይልህ ና አንዲት ብጣሽ ወረቀት ይመዝልኃል።

‹‹ጌታዬ እሷን ባትመዝናትስ? ይኼን ሁሉ የሀፅያት መዝገብ ከዚህች ብጣሽ ወረቀት ልታመዛዝን›› ትለዋለህ።

ንግግርህ ወድያ ተትቶ ሚዛንህ ላይ አድማሳትን ያካለለው የሀፅያት መዛግብትና ይህች ብጣሽ ወረቀት ይጫናሉ። ብጣሿ ወረቀት ያን ሁላ መዛግብት ከመመዘን አልፈም መዛግብቱን ትበታትናቸዋለች በሰማይህም ላይ ይበታተናሉ።

ደስታ ምትሆነውን ያሳጣኃል፣ ተስፋህ ይለመልማል፣ ህይወት ታጓጓኃለች፣ ዕጣፋንታህን ቀይራ ለጀነት የዳረገችህን ወረቀት ስትመለከትም የጌታህን እና የነበይህን ስም ተፅፎበት ታገኘዋለህ።

‹‹ላ ኢላሃ ኢለላህ ሙሐመዱን ረሱሉላህ››

@heppymuslim29
1.5K viewsɯɐɥlǝ, 16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 22:27:40 በእናንተ ናፍቆት አይኑ ባነባላቹ በደጉ ሙሐመድ ላይ ሶለዋት አውርዱ

اللهم صلي وسلم وبارك على أشرف الخلق
1.3K viewsɯɐɥlǝ, 19:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 17:09:15 ☞በድሮ ግዜ አንድ ሰውየ ሱቢህ ሶላት ለመስገድ በለሊት ወደ መስጅድ በሚሄድበት ሰአት በሰአቱ ዝናብ ጥሎ ስለነበር ከሆነ ቦታ ላይ መሬቱ ያዳልጠውና ይወድቃል ።

ከዛም ጀላብያው በጭቃ ሲበከልበት እንዲህ_አለ "ዛሬማ የሱቢህን ሶላት የግድ በጀማዐ መስገድ አለብኝ አለና ወደ ቤቱ ልብስ ለመቀየር ሄደ።

እንደገና ልብስ ቀይሮ ሲመለስ መጀመሪያ ከወደቀበት ቦታ ላይ ሁለተኛ ወደቀና የለበሰው ጀላብያ በጭቃ ተበከለ።የሚገርመው ግን ይሄ ሰውየ ተስፍ አልቆረጠም ነበር ይልቁንስ የሱቢህ ጀማዐ ሶላት አያመልጠኝም አለና ወደ ቤቱ ልብስ ለመቀየር ተመለሰ።

አሁንም ሶስተኛ ግዜ ልብሱን ቀይሮ ወደ መስጅድ በሚሄድበት ሰአት ሁለት ግዜ ከወደቀበት ቦታ ላይ ለሶስተኛ ግዜ ሊወድቅ ሲል ምን ቢከሰት ጥሩ ነው አጅሬ ሸይጧን በሰው ተመስሎ ይመጣና ደገፍ አድርጎ ያሳልፈዋል።

ከዛም ይሄ ሰው ተገረመና አንተ ማነህ ብሎ ጠየቀው?  ሸይጧን ነኝ አለናም መለሰለት።

ከዛም ይሄ ሰው እንዲህ አለው "ሸይጧን ከመቼ ወዲህ ነው ለሰው ኸይር የሚሰራው"አለው?

ሸይጧንም እንዲህ አለው"እኔ ላንተ አስቤ አይደለም ግን መጀመሪያ ስትወድቅ አሏህ ያንተን ወንጀል ሲምርልህ አየሁ ሁለተኛ ስትወድቅ ደግሞ አሏህ የቤተሰብህን ወንጀል ሲምርላች አየሁ ሶስተኛ ብትወድቅ የ ሰፈሩ ሙስሊም ሰዎች ወንጀላቸውን አሏህ ስለሚምራቸው ከሚማሩማ ደግፊ ላሳልፍህ ብየ ነው አለው።

አሏህ ከሸይጣን ተንኮል ይጠብቀን
@heppymuslim29
2.0K viewsɯɐɥlǝ, edited  14:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 18:54:32 ረሱል ጋር ሁሌ ኸምር እየጠጣ ለመገረፍ የሚመጣውን ሰው ሰሀቦች ሲሰድቡት "ተዉት እሱኮ አላህና ረሱሉን ይወዳል" ነበር የረሱሌ መልስ

ሁላችንም ነፍሳችን አሸንፋን ወንጀል
እንሰራ ይሆናል ግን ሁላችንም እንደዛ ሰው አላህንና ረሱሉን እንወዳለን



صلى الله عليه وسلم
@heppymuslim29
2.9K viewsɯɐɥlǝ, 15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-18 12:06:25 ነቢዩላህ ዳውድ በዙፋናቸው ላይ ተቀምጠው ሳለ አንዲት ሴት መጥታ እንዲህ አለቻቸው፡
«ጌታህ ፍትሀዊ ነው ወይስ በዳይ?» የሚል ድንገተኛ ጥያቄን ሰነዘረች ለምን እንደዚህ እንዳለች ምክንያቷን ታብራራ ዘንድ ጠየቋት

«አባታቸው የሞተባቸውን ሶስት የቲም ልጆችን አሳድጋለሁ። ጉሮሯቸውን የምደፍነውም ጥጥ በመፍተልና በመሸጥ ከማገኘው ገንዘብ ነው። ዛሬ ግን ጥጤን ፈትዬ በጨርቅ ከረጢት ውስጥ አድርጌ ልሸጥ ወደ ሱቅ አመራሁ።

በመንገዴ ላይ ሳለሁ አንድ አሞራ ከረጢቴን ይዞብኝ በረረ። ለልጆቼ ዳቦ መግዣ አጣሁ በርሀብ እየተንገላቱ ነው ···· » ንግግሯን ሳትጨርስ በሩ ተንኳኳ። ፈቃድ ተሰጣቸውና ወደ ውስጥ ገቡ። አስር ነጋዴዎች ነበሩ። በእጃቸው 1000 ዲናር ይዘዋል ከመሐላቸው አንዱ መናገር ጀመረ
«አንቱ የአላህ ነብይ ባህር ላይ እየተጓዝን ሳለ መርከባችን ተቀደደና መስመጥ ጀመረ። ሞታችንን በመጠባበቅ ላይ ሳለን አንድ አሞራ የተፈተለ ጥጥን የያዘ ቀይ የጨርቅ ከረጢት ከላይ ጣለልን። ቀዳዳውን በጨርቁ ደፈንን መርከባችንም ወደ ላይ ተንሳፈፈ። ከሞት ዳንን።

አላህ ለዋለልን ውለታ ምስጋና ይሆን ዘንድ እያንዳንዳችን መቶ መቶ ዲናር ለመስጠት ቃል ገባን። ይሄው ገንዘባችን እርስዎ ዘንድ ላሉ ሚስኪኖች ሰደቃ ይስጡት » በማለት ብሩን እንዲቀበሏቸው እጃቸውን ዘረጉ።

ነቢዩላህ ዳውድም ወደ ሴትዬዋ በመዞር《ጌታሽ አንቺን ከድካም አሳርፎ በየብስና በባህር ይነግድልሻል አንቺ ግን በዳይ ትይዋለሽ በይ ገንዘቡን ተቀብለሽ ይዘሽ ሂጂ 》በማለት አዘዟት።

<< አሏህ ለኛ የተሻለውን እንጂ አያደርግም!!>>

@heppymuslim29
2.5K viewsɯɐɥlǝ, 09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 13:54:33 ጨካኙ አባት

ሴት ልጁ እንዲህ ትላለች ....
" 6 አመታትን ያህል አባቴ ባልገባኝ ምክንያት ለትዳር ጥያቄ የሚያቀርቡልኝን ወንዶች ሁሉ እንቢ አለ ። በዚህም ጉዳይ ምንም አይነት ውይይት አይቀበልም ።
እኔን ፍለጋ በሩን የሚያንኳኩ ሰዎችን ሁሉ አባቴ በእንግዳ ማረፊያው ክፍል ለግማሽ ሰዓት አንዳንዴም ከዛ ያነሰ ያህል ያወራቸዋል ፣ ከዚያም የመጣው ወጣት በፍጥነት ይወጣል

እናቴ አባቴን ለመጠየቅ ቸኮለች" ምንድን ነው የሆነው "
እንዲህ ሲል መለሰላት፡- ጥሎሹን አልወደድኩትም የእሱ አቻ በቤታችን ውስጥ የለችም !

የመንፈስ ጭንቀት ወደ እኔ ዘልቆ መግባት ጀመረ ። አባቴ በኔ ድርሻ እና በኔ ደስታ መጋረጃ በመሆኑ በሱ መቆጣት ጀመርኩ። ራሴን እጠይቅ ነበር "እንዴት ሊሆን ይችላል? ለገንዘብ ብሎ ለአንዲት ሴት ልጁ የማይቻለውን ጥሎሽ ይመኛል !

አሁን ተዓምር ተፈጠረ ።
አባቴ ከአመልካቾች ከአንዱ ተስማማ ።
ባለቤቴ ስለከፈለልኝ ጥሎሽ አባቴ ሳይነግረኝ ትዳራችን ተፈፀመ...

የሚገርመው ነገር ባለቤቴ በአማካይ የኑሮ ሁኔታ ላይ ያለ እንጂ ቀድመውት ከጠየቁት ሰዎች አንፃር ከብዙዎቹ ድሃ ነበር
እሱም ከአባቴ ጋ ስለተስማሙበት ጥሎሽ (መህር)አልነገረኝም

በትዳራችን አስር አመታት አለፉ ። ከባለቤቴ ምንም ክፉን ነገር አላየሁም። ያየሁት ርህራሄን, ደግነትን እና ስስትን ብቻ ነው

ዕድሜዬ እየጨመረ ቢሆንም በባለቤቴ እንክብካቤ ምክንያት ምንም የመከፋትም የመረበሽ ስሜት አይሰማኝም ነበር ።
አባቴ ጥሎን ወደማይቀረው ጉዞ እስኪሄድ ድረስ..

ከቀብር ሥነ ሥርዓቱ በኋላ ባለቤቴ ወደኔ መጣ ወደ ደረቱ አቀፈኝና “ትንሿ አትዘኚ " አለኝ ።
" ትንሿ " በምትለው ቃል በጣም ተገረምኩ ።
በስስት አየኝና ... ‹‹አዎ ትንሼ ነሽ ።
.....
ለጋብቻ አንቺን ስጠይቅ አባትሽ ምን ማድረግ እንደምችል ጠየቀኝ። ትንሽ አሰብኩና ፡- አጎቴ ብዙ ምሰጠው የለኝም ። ግን ምዬ የምነግርህ ነገር ቢኖር አንተን በሞት ብታጣህ እንኳ የቲምነት እንዳይሰማት አደርጋለሁ። ልክ የአብራኬ ክፋይ እንደሆነች ሴት ልጅ እንከባከባታለሁ " አልኩት ።

አባትሽም ፈገግ አሉና ፡- "ሚስትህ ልጄ ናት"አሉኝ

@heppymuslim29
2.6K viewsɯɐɥlǝ, edited  10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ