Get Mystery Box with random crypto!

ሶልያና ' የተሰኘ ሥራው ከግጥሙም ጭምር ፍቅር ያስያዘኝ ግጥም ነው። ስሜቱን በግልጽ ሚከተብ ገጣሚ | Henok Abayneh Gebrehiwot

ሶልያና ' የተሰኘ ሥራው ከግጥሙም ጭምር ፍቅር ያስያዘኝ ግጥም ነው። ስሜቱን በግልጽ ሚከተብ ገጣሚ ነው። ሥራዎቹ  በፍቅር የተጎዳ ማንነት ያለው ፣ ትዝታ የለበለበው ፣ ፍቅር ማጣት የእግር እሳት የሆነበት የግልጽነት ስሜት ያለባቸው ናቸው። እኛኝ ሚመስሉ ናቸው። ብሶት አላቸው ፣ ህይወት አላቸው ፣ እውነት አላቸው ፣ ፍልስፍና አላቸው።

'' ፍቅር እዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር '' ብሎ ትዝታን ያስታምማል። '' ውሸት ነው '' ብሎ ለምናብ የሚተው ሀሳብ ይዘይራል። በድምጽ ቀድቶ ያደረሰን ግጥሙ መመሸግያ ነው። ቆሌዬ ይወደዋል። ደግሞ አገኘሁት ፣ ጠየቅኩት ፣ አመሰገንሁት። አስበኸው ሳይሆን ሆነኸው ምታገኘው ደስታ አለ አይደል ? ...እንዲያ ነው የተሰማኝ።  

@henokpk @henokabayneh