Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ሄሎ ዶክተር ስለ ጭንቅላት ዕጢ ልትነግሩኝ ትችላላችሁ የጭንቅላ እጢ ምልክቶች ጤና ይስጥ | ሄሎ ዶክተር 👂👂👂🏥

ሰላም ሄሎ ዶክተር
ስለ ጭንቅላት ዕጢ ልትነግሩኝ ትችላላችሁ

የጭንቅላ እጢ ምልክቶች

ጤና ይስጥልኝ ውድ የዶክተር ቤዛ ቤተሰቦች ለዛሬ ለናንተ ተከታታዮቻችን ይዘንላችሁ ከቀረብናቸው መረጃዎች ውስጥ ስለ ጭንቅላ እጢ ምልክቶች ነው ተከታተሉን

አብዛኛዎቹ የጭንቅላት እጢ ቀጥለው ከተዘርዘሩት ውስጥ ቢያንስ ከሁለት በላይ ምልክቶች ሊያሳዩ /ሊኖርባቸው ይችላል ነገር ግን ምልክቶቹ ሁሉ የእጢ እና ዕጢ ብቻ የማይሆኑበት አጋጣሚም ይኖራል ስለሆነም በምርመራ የትኛው የአእምሮ ክፍል እና ምን አይነት ዕጢ ነው የሚባለው ነገር መታወቅ አለበት፡፡

ራስ ምታት:- በአብዛኛው እጢ ያላቸው ሰዎች የሚኖር ምልክት ሲሆን ረጅም ወይም አጭር ግዜ የቆየ በቀላል ማስታገሻ በደንብ የማይቀንስ ፣ ጥዋት ከእንቅልፍ ሲነሱ ፣ ወደ ፊት ስያጎነብሱ ፣ ሲያስሉ የሚጨምር ራስ ምታት ፤በአብዛኛው እጢ ያላቸው ሰዎች የሚኖር ምልክት ሲሆን ረጅም ወይም አጭር ግዜ የቆየ በቀላል ማስታገሻ በደንብ የማይቀንስ ራስ ምታት ይኖራቸዋል፡፡።

የእይታ ችግር: የዓይን የእይታ መቀነስ (እየባሰ የሚሄድ) ፣ ከፍሎ መጨለም ፣ ብዥታ ፣ አንድ ነገር ሁለት ሁኖ መታየት ፣ የዓይን መርገብገብ ፣ የዓይን መንሸዋረር ቀላል በማይባሉ ሰዎች የሚያጋጥም ምልክት ነው፡፡
የሚጥል በሽታ:- ሁሉም የሚጥል በሽታ ያላቸው ሰዎች በእጢ ወይም በተመሳሳይ እብጠት ምክንያት ነው ማለት አይደለም። ሆኖም ግን የሚጥል በሽታ ያለበት ሰው እጢ እና ከእጢ ጋር ተመሳሳይነት ያለው የአንጎል እብጠት አለመኖሩ በምርመራ ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

የሰውነት መስነፍ:- ይህ ምልክት አንድ እጅ ወይም አንድ እግር ወይም በአንድ በኩል እጅ እና እግር (ግማሽ ሰውነት ከፍሎ) ወይም ሁለቱም እግር መስነፍ ወይም ሙሉበሙሉ አልታዘዝ ማለት
መንገዳገድ (ባላንስ አለመጠበቅ)፡- መንገድ ሲራመዱ መስመር አለመጠበቅ እና ይህ ለማካካስ እግር ሰፋ አድርጎ መርገጥ እና መራመድ ፣ ወደ አንዱ አቅጣጫ ማጋደል /አዝማምያ ይኖራቸዋል።
ምንም ምልክት አለመኖር፡- ለሌላ ተብሎ በተሰራ ምርመራ አጋጣሚ የአንጎል እጢ ሊገኝ ይችላል። የእጢው እድገት እና ባህሪ ታይቶ ኦፕራስዮን ወይም ሌላ የሕክምና አማራጭ ሊያስፈልገው ስለሚችል ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል።

መስማት መቀነስ:- አዲስ ወይም ቀስ በቀስ እየባሰ የሚሄድ የመስማት ችግር ፣ ጆሮ ውስጥ የጩሀት ስሜት መኖር ሊኖራቸው ይችላል። አብዛኛው ግዜ በአንድ ጀሮ ብቻ የሚያጋጥም ሲሆን አልፎ አልፎ በሁለቱም ጆሮ ላይ ሊያጋጥም ይችላል።
ሽንት ወይም ሰገራ መቆጣጠር አለመቻል ፡- ሽንት ማምለጥ ፣ ሰገራ አለመቆጣጠር ወይም ሁለቱም ያለመቆጣጠር ችግር ሊኖር የእጢ ሁኔታ /እድገት እየተባባሰ ሲመጣ የሚታዩ ችግሮች ናቸው ።

ትንታ (chocking):- ውሃ ወይም ሌላ ፈሳሽ ነገር ሲጠጣ ተደጋጋሚ የሆነ ትንታ መኖር እና ከዚህ ጋር በተያያዘም የሳንባ ኢንፈክሽን መፈጠር (Aspiration pneumonia) ፣ በተደጋጋሚ ሳል መኖር ።
ማስመለስ:- ከአንጎል እጢ ወይም ተመሳሳይ ባህሪ ያላቸው ችግሮች ጋር ተያይዞ የሚኖረው ማስመለስ ከማቅለሽለሽ ጋር ያልተያያዘ ፣ ድንገት የሚመጣ (projectile vomiting) ሲሆን ፣ ብዙ ግዜ አብሮ ራስ ምታት ይኖራቸዋል።

የመናገር ችግር:- እንደ እጢው ወይም እብጠቱ ያለበት የአንጎል ክፍል ምንም መናገር አለመቻል ፣ ሰው የሚናገረው ሐሳብ አለመረዳት ፣ ሲናገሩ መኮላተፍ (ሙሉ ዓረፍተ ነገር ወይም ቃል በደንብ አለማውጣት) ፣ የተኗገሩትን ነገር ደግሞ አለመናገር ።

የማስታወስ ችግር (መርሳት)፡- የቅርብ ወይም የረዥም ግዜ ክንውኖችን የማስታወስ ሁኔታ መቀነስ ፤ ሰው ፣ ቦታ ፣ ግዜ ያለማስታወስ ሁኔታም ሊኖራቸው ይችላል።

የፊት እና አገጭ ላይ ከባድ ህመም ወይም የመደንዘዝ ስሜት። እንደ እጢው ባህሪ አብዛኛው ግዜ የተወሰነ የፊታችን ክፍል ወይም አገጭ ላይ ወይም ሙሉ ግማሽ ፊታችን ላይ ቶሎ ቶሎ የሚመላለስ ከባድ የሆነ ህመም ወይም የመደንዘዝ ስሜት ሊኖር ይችላል።

የንቃት መቀነስ:- የአንጎል እጢ ያለበት ሰው የንቃት ደረጃው መቀነስ በደንብ ካለማውራት እስከ ምንም አለመናገር ሊደርስ የእውቀት ችግር ሊሆን ይችላል።

የጭንቅላት መጠን መጨመር:- አብዛኛው የአንጎል እና የጭንቅላት አጥንት እድገት የሚኖረው በመጀመርያዎቹ ሁለት የዕድሜ ዓመታት ነው። እጢ ወይም ተመሳሳይ እብጠት እና ከነዚህ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ችግር ያላቸው ልጆች ላይ ከልክ ያለፈ የጭንቅላት እድገት ሊኖር ይችላል፤ብዙ ግዜ ከሁለት ዓመት በታች ያሉ ህፃናት ላይ የሚታይ ምልክት ሲሆን ቀጥታ በእጢው ምክንያት ወይም ከእጢው ጋር ተያይዞ በሚፈጠር ሁኔታ ሊሆን ይችላል።

ከልክ ያለፈ የሰውነት መጠን መጨመር:- አዲስ የሆነ ከልክ ያለፈ ክብድት መጨመር ፣ ከልክ ያለፈ ቁመት ፣ ከልክ ያለፈ የእጅ እና የእግር ፣ የአገጭ መግዘፍ ሊያጋጥም ይችላል።