Get Mystery Box with random crypto!

ህሊና የግጥም ገፆች✅

የቴሌግራም ቻናል አርማ helinas — ህሊና የግጥም ገፆች✅
የቴሌግራም ቻናል አርማ helinas — ህሊና የግጥም ገፆች✅
የሰርጥ አድራሻ: @helinas
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 631
የሰርጥ መግለጫ

@bisrei @bisrei
@bisrei @bisrei
ከንቱ አንሆንም ነበር !
ከቶ አንቀርም መና!!
ሰው ያየኛል ሳንል፤
ቢዳኘን ህሊና።
ሶና እንደገጠመው!
@bisrei
0911550441

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-12-07 18:19:23
ታዳጊው ድምጸ መረዎዉ ወጣት በአዲስ ነጠላ ዜማ ብቅ ሊል ነው ናሆም ሪከርድስ ላይ እንጠብቀው
406 views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-02 22:01:36 ከኔ በቀር የለኝም
ባይተዋር ነኝ ብቸኛ
ራሴ ለራሴ ቆሜ
ከራሴ ጋር የምተኛ

ኤኔ ነኝ የ እኔ አለቃ
ባረፍድም ብሄድ ብቀር
ገሳጭ ተቆጪ የለኝም
ከህሊናዬ በቀር!

==========
ብስሬ ነኝ!
458 views19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-30 16:21:57

shere like subscribe

ይሄንን አዲስ ዩቱበር ሰብስክራይብ በማድረግ አበረታቱት ሰዎችዬ
397 views13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-30 16:02:33
ናፈከኝ

ያልዋልንበት ጊዜ ውሎዬ ሲመስለኝ
ያላለፍነው መንገድ መንገዴን ሲመራኝ
ያላየነው ሁሉ ትውስታ ሲሆነኝ
ባልኖርኩት ትላንት ውስጥ ኖሬ ተገኘሁኝ
የኖርኩት ካልኖርኩት ገጥሞልኝ ባየው
ያልነበረው ሁሉ ተፈጥሮ ባገኘው
በልቤ መዝገብ ውስጥ ሰፍሮ ብመለከት
ያበድኩ መሰለኝ እራሴን ፈራሁት

ውስጤ ሰላም ሆኖ አይኔ ቢያማትር
ያልነበረን ሊያይ በስሜት ቢታትር
የሰፈነን ሰላም ሊያሸብር ቢጥር
አልገለጥ አለኝ የብዥታው ሚስጥር

ባልሄድኩት ጎዳና ሄጄ ባስተውለው
ባልኖርኩት ህይወት ውስጥ ህይወቴን ባኖረው
ባላሰብኩት ማእበል ሰምጦ ቢገኝ ነፍሴ
ሊቋረጥ ቢጣጣር ትንሹ እስትንፋሴ
አየሁት እራሴን የኖርኩት መሰለኝ
ባልኖርኩት ትላንት ውስጥ ትዝታህ መለሰኝ
የህይወቴ ዋሻ አንተን አስታወሰኝ
ዛሬ ሀቁን ላውራ በብዙ ናፈከኝ
═════════❁✿❁ ═════════
አንብባችሁ #ሼር #ሼር አድርጉልን የቴሌግራም ቻናላችንንም ግቡና Join አድርጉ ።
https://t.me/joinchat/AAAAAFAtO5kL7-YczXxg_Q
363 views13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 22:44:51 ይኮራል ይሉኛል
አዎን ነኝ ኩሩ
ከአያቴ አይደል ወይ
የኩሩነት ዳሩ

አልደፋም አንገቴን
አላይም የሰው እጅ
ኮራ በል ነው ውርሴ
እስክሞት እስክጃጅ።

=============
ብስሬ ነኝ!
331 viewsedited  19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 17:13:14 ውድ የግጥም አፍቃሪያን እንዴት ናቹልኝ
ሰላማቹ ይብዛ እያልኩኝ በቅርቡ በ ቲክ ቶክ አጫጭር ግጥሞቼን በድምጽ ይዤ ልመጣ እንደ ሆነ እየገለጽኩኝ ያለን የቴሌግራም አባላትን ቁጥር ለመጨመር የናንተን እርዳታ ስለሚያስፈልገኝ 5 አምስት የግጥም አፍቃሪ ጓደኞቻቹን አድ እንድታረጉ በአክብሮት እጠይቃለሁ!

ገጣሚ ብስራት ባይሳ(ሶና)
329 views14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 17:03:57 አያልቅ አይጎልብሽ
የፍቅር አውድማ
አያልፍ ወረት የለው
እየጠጡት የሚጠማ
ፍቅርሽ የትም የለም
ትለያለሽ እማ


ለእናቴ
===========
ብስሬ ነኝ!
413 viewsedited  14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-28 22:07:59 ካነሱም መረሳት
ከበዙም መከራ
ቦታክን ካልመረጥክ
ትሆናለክ ተራ

ካለቀቀህ እንጂ
የያዘህ አባዜ
ዋጋክን ካወከው
አይተርፍህም ጊዜ

መርጠው ካልረገጡ፤
ከአቻ ካልዋሉ፤
ወርቅ ካለቦታው
ከ ብር ያንሳል አሉ።

============
ብስሬ ነኝ!
344 viewsedited  19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-28 19:29:27 ትላንቷን አላውቅም
ዛሬዋ አልተገለጠ
ገና አንዳየኋት
ውስጤ ደነገጠ

ያሳሳል ገላዋ
ይርባሉ አይኖቿ
ብዙ አይቻለሁ
የሷን ግን እኔንጃ

ከዳሰስኩት አካል
ከነካሁት ገላ
የሷን አይኖች ማየት
እየሆነኝ መላ

እሷ ናት ለኔ መልስ
እሷ ናት ለኔ ሰው፤
ባይኔ እየገባች
ልቤን እምታርሰው።

============
ብስሬ ነኝ!
346 viewsedited  16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-18 12:33:41 ምን ይሆን?
=======
አንዳንዴ ይከፋኛል
ከመሬት ተነስቶ
ሳላጣ አንዳች ነገር
ሳይጎለኝ ተሟልቶ

በቃ ይከፋኛል
ይቀረኛል እምባ
እምበላው አይጥመኝ
ጽናት ውስጤ አይገባ

ይርቀኛል ደስታ
የርቀኛል ሳቄ
ክስል ይላል ፊቴ
በዝቶ መጨነቄ

ሆዴን ባር ባር ሲለው
ምን ይሆን ነገሩ?
በሰላም አለም ውስጥ
ልቤ መሸበሩ

ጥያቄ ዉስጥ ነኝ
አንተ ሰው አንቺ ሰው
ግጥሜን በግጥም
ማነው የሚመልሰው?
674 views09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ