Get Mystery Box with random crypto!

በፍጹም አልወቅስም ኑሮን አማርሬ እስቃለሁ እንጂ እራሴን ኮርኩሬ ጠፍቶ ለማያውቀው የዝች አለም ጣ | ህሊና የግጥም ገፆች✅

በፍጹም አልወቅስም
ኑሮን አማርሬ
እስቃለሁ እንጂ
እራሴን ኮርኩሬ

ጠፍቶ ለማያውቀው
የዝች አለም ጣጣ
የኔ ኩስኩስ ግምባር
ምን ለውጥ ሊያመጣ

ይልቅ ላመስግናው
የሱ ነው ብርታቱ
ይጨምርልኛል
የማያልቅበቱ!

==========
ብስሬ ነኝ!