Get Mystery Box with random crypto!

እይዝ እይዝና በመዳፌ ገብቶ እንደጉም ይተናል አጓግቶ አጓግቶ ! ማሰብ ፈለኩና አልፈቀደም ብ | ህሊና የግጥም ገፆች✅

እይዝ እይዝና
በመዳፌ ገብቶ
እንደጉም ይተናል
አጓግቶ አጓግቶ !

ማሰብ ፈለኩና
አልፈቀደም ብዬ
ለምን ያሳየኛል
ካልበላሁ አብስዬ!

ማግኘትና ማጣት
ሆነች ብልጭ ብልጭ
ይጫወታል እንዴ
እርሱም እንቁልልጭ ?

===========
ብስሬ ነኝ!