Get Mystery Box with random crypto!

#የፈተነችህ የዝሙት ጾር ብትርቅህ ተጠንቀቅ!!! (#ካብኩህ ካብኩህና ቁልቁል አፈረጥኩ!!!) | ሄላንሳን

#የፈተነችህ የዝሙት ጾር ብትርቅህ ተጠንቀቅ!!!
(#ካብኩህ ካብኩህና ቁልቁል አፈረጥኩ!!!)

። እንኳን አደረሳችሁ ።
ውድ የሄላንሳን ቻናል ቤተሰቦች እንደምን አላችሁ? ቸር አምላክ እንደ እኛ ኃጢአትና በደል ብዛት በፊቱም እንደ መርከሳችን ሳያጠፋን እድሜ ለንስሃ እየሰጠን ይኸው አለን። መሃሪ የሰላም አባት ልዑለ ባህርይ ለሆነው #ለእግዚአብሔር ክብር ምሥጋና ይግባውና ሄላንሳን ማዕዳችሁ ዛሬ በአብይ ጾም አራተኛ ሳምት ጅማሬ ማዕድዋን ልታቀርብልኝ የቀድሞን ውብ የትውስታ ማዕድ ይዛ በድጋሜ አቅርባለች የጎደለ ማዕድ እንኳን ቢኖር ከቅድም ውስንነት ነው ብላችሁ ያቀረበችውን ተመገቡላት ።፤ ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን። አሜን
@helansane
የክፋት ስልት ባለቤት የሆነው የጨለማው ዓለም ግዞት ስልጣን የተሰጠው የክፋት አባት የዝሙት ጠንሳሽ የሆነው ዲያብሎስ በዘመናችን ስልቱ የበዛ መንገዶች እየተጠቀመ የእኛን ዘመን እንዲህ አድርጎታል! #እንደምናየው የክፍት ስልት ባለቤቱን በግድ የለሽነት በጣለብንም ዐዚም መንቃት አቅቶን እየወደቅን ያለን ዛሬ....አሁን የመንፈስ ዓይናችንን እንግለጥ ከተኛንበት እንቃና የመዳን ቀን ዛሬ ነው ወደ ካህናት አባቶቻችን እንሩጥ በንስሃ እንባ እንታጠብ የሰላም ንጉሡ ሳይመጣ!!!

ብዙ ጊዜ በወጣትነት እድሜ ላይ ያለን ሰዎች ፈተና ይህ ነው። ዝሙትና መከራው ስለዚህ በዛሬዋ ንቃተ ህሊናን ሚሰጥ ማዕድ እንመገባለን ከአበው ምክርና ተግጻጽ።
ዲያብሎስ ሁሌም አንድን(አንዲትን) ወጣት በዝሙት ክፍኛ በመዋጋት ያደክመውና አልፎ አልፎ ይጥለዋል። በዚህ ጊዜ ወደ ንስሃ አባቶች አምርቶ ንስሃ በመግባት ይህን ኃጢአት
ሊያስፈጽሙት ከሚችሉት ምክንያቶች ሁሉ #በማንበብ ፥ ቃለ እግዚአብሔርን አብዝቶ በመስማት እራሱን በትጋት መጠበቅ ይጀምራል። በተመሳሳይ ጊዜ ከእንባ ጋራ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር በመጮህ ያድነው ዘንድ ይማጸናል። በዚህ ጊዜ የዝሙት አባት የሆነው ዲያብሎስ እንደምን ሊፈትነው ይችላል? ይህን መመለስ ታላቅ ግብዓት አድርጎ ስልቱን ሚቀይረውን ዲያብሎስን ግን አያስተውልም። የቀደመውን የዝሙት ፈተና ፍጹም ለጊዜው ይተወውና በሌኛው የከፋ ኃጢአትም ሊጥለው ያዘጋጀዋል ለእርሱ የአንደኛው ፍጻሜ ለሁለተኛው ኃጢአት ጅማሬ ይሆንለታል!! #ለማይነቃ ክርስቲያን።
@helansane
ከዚህ በኃላ ሚሰራው ስራ ለአመታት ያክል ወጣቱን በዝሙት እንዳይወድቅና እንዲወድቅም ምክንያት ሚሆኑትን ነገሮች ከሥሩ በማጥፋት ስለ ዝሙት #ማሰብ እንኳ እስኪያቆም ድረስ እርግፍ አድርጎ ይተወዋል በሌላኛው #በኩራት ኃጢአት ሊጥለው ስራውን ይጀምራል። አብልጦ ቅዱሳን መጽሐፍትን እንዲያነብ መልካም ስራዎችን በህይወቱ እንዲያበዛ ይራዳዋል የበለጠ ጨምሮ ጨምሮ ጸሎቱን ሁሉ እንዲያደርግ ያበረታዋል።(ካብኩህ ካብኩህና ቁልቁል አፈረጥኩህ) እያለ ላንተ ሚዘፍንልህን ግጥም ያዘጋጃል እርሱ ደራሲው የክፋት አባት ዲያብሎስ
@helansane
ወጣቱ በአዲሱ የስልት መንገድ መፈተኑን ሲጀምር ሰዎችን ተናጋሪ በመሆን ይጀምራል። እንዴት በነብያት ጾም ጊዜ አትጾምም እናትና አባትህ ቤተሰቦችህ አይጾሙም፥ አንተስ ለምንድነው ማጾመው? አንተ ለምንድነው ንስሃ ማትገባው? አንተ ለምንድነው ቁርባን ማትቀበለው? እያለ ሌሎችን ክፉኛ እንዲኮንንና እንዲገጽጽ ዲያብሎስ ያማክረዋል። ዘለፋው አይሎ ሌሎችን ከእግዚአብሔር በመራቃቸው ሊሰድባቸውና ሊጠላቸው ይጀምራል። ልቡ በፍጹም #ኩራት ይደፈናል #በጽድቅ ስም ሊሳደብ፥ በቁጣ ሊናገር፥ ፍጹም አላዋቂነቱን ሊያሳይ ይነሣል። በሉቃ ወንጌል(18፥11) እንዳለው ፈሪሳዊ "#እግዚአብሔር ሆይ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ #ቀማኞችና #ዓመፀኞች #አመንዝሮችም ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንኩ አመሰግንሃለሁ"" በማለት ይህም ወጣት በእግዚአብሔር ፊት ሊጸልይ ይጀምራል። ስለዚህ ቀደም ብሎህ የዘፈን ግጥሙን የወጣቱን አካሄድና ፍጥነት አይቶ በቶሎ ዜማውን የቀመረው ዲያብሎስ እንዲህ ይላል ብትጠይቀው ፈገግ እያለ ከዝሙት ስለ ተገላገለው ወጣት ""በዝሙት ኃጢአት ውስጥም ሆነ በኩራት ኃጢአት ውስጥ ሞት አለ። የሁለቱም ደመውዝ ሞት ነው።""እያለ ቅላጼውን ይጨምራል በክርፋታም ድምጹ #ካብኩህ ካብኩህና ቁልቁል አፈረጥኩ!!!!!!!!!!! እያለ ይቀጥላል
@helansane

#ውድ የሄላንሳን ቤተሰቦቼ የኃጢአት ፈተናዎቻችን ከእኛ ቢርቁ #እንጠንቀቅ!!! በከፋው ኃጢአት ሊጥለን ፍጹም የማይተወን ጠላት አለንና #እንንቃ #በኩራት ታጅረን ሌሎችን ከምንናገር ይልቅ በኃጢአት ውስጥ ሆነን በደለኝነታችንን እያመንን ከአምላክ ፊት ለምህረት መቆም ይሻላልና እድፋችን(ኃጢአታችን) በዝቶ የሌሎችን አንዲት እድፍ ለመፋቅ አንሩጥ።
#ሼር በማድረግ እንማማር
#የሰላም አባት የሰላም አለቃ ልዑል #እግዚአብሔር ለሀገራችን ሰላምና ምህረትን ይላክልን ቅድስት ቤተክርስቲያንን ይጠብቅልን ለሁላችንም የንስሃ እድሜ ያድለን። አሜን