Get Mystery Box with random crypto!

ወቅታዊ ማስታወሻ ለሙስሊሞች ክፍል 2 ውድ ሙስሊም ወንድም | እስላማዊ ትምህርቶች የሚለቀቅበት ቻናልነው(ኢንሻ አሏህ)@@@@/////………Eslamic Knowledge

ወቅታዊ ማስታወሻ ለሙስሊሞች
ክፍል 2


ውድ ሙስሊም ወንድም ና እህቶች
ይህን ወቅታዊ ማስታወሻዬን ጥቂት ጊዜያችሁን ሰውታቹ እንድታነቡት አደራ አደራ እላለሁ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ አና በጣም አዛኝ በሆነው

በባለፈው ክፍል ስለ አረፋ ቀን ትሩፋቶች በበቂ ሁኔታ ለማየት ሞክረናል
ዛሬም ከባለፈው በቀጠለ መልኩ ባጭሩ የምንገልጽ ይሆናል

ዱዓ

በላጬ ዱዓ ማለት የዓረፋ ቀን የሚደረግ ዱዓ ነው። ረሱል ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም

አላህን የምንፈልገውን ነገር እንዲለግሰን
ከምንፈራው ነገር እንዲጠብቀን
ዱዓችንን እንደሚቀበለን እርግጠኛ ሆነን በመተናነስ ወደ እሱ መጣራት ማልቀስ መዋደቅ አለብን

ወንጀላችንን ሙሉ በሙሉ እንዲምርልን ወደ እሱ በመመለስ ማህርታን ከእሱ ብቻ መጠየቅ አለብን

በዛሬው እለት ማን ከሳሪ እንደሆነ ያውቃሉን?!

ዐብዱላህ ኢብኑ ሙባረክ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ ፦
"ዐረፋ ቀን ማምሻውን ወደ ሱፍያን ሰውሪይ ረሂመሁላህ መጣሁ። እርሱም በጉልበቱ ተንበርክኮ አይኖቹ እያነቡ አገኘሁት። ወደኔ ዞር ብሎ ተመለከተ። እኔም ፦"ዛሬ ቀን ለክስረት የተዳረገ ማን እንደሆነ ታውቃለህን?" አልኩት።
እርሱም ፦" እርሱ ያ ጌታው አይምረኝም ብሎ የተጠራጠረ ነው።" በማለት መለሰልኝ።"

ኢብኑ ረጀብ ሐንበሊይ /ለጧኢፉ አልመዓሪፍ

የታላቁ ዓሊም ሱፍያን ሰውሪይ ንግግር ምንኛ አማረ
ስለሆነም ሁላችንም በዱዓ መበርታት ግድ ይለናል

የዓረፋ ቀን የሚውለው ዕለተ ጁመዓ ሀምሌ 1 የዐረፋ ቀን ሲሆን በዓሉ ደግሞ ቅዳሜ ይሆናል ። የሚፆመው ጁመዓ ነው ማለት ነው።
ጁመዓ እና ዓረፋ ሁለቱም የራሳቸው የሆነ ትሩፋት አላቸው ከነዚህም ትሩፋቶች መካከል በዋነኝነት 2ቱም ዱዓ ተቀባይነት ሚያገኝባቸው ቀናቶች መሆናቸው ነው

ስለ ዓረፋ ቀን ዱዓ ነብያችንﷺ እንዲህ ይላሉ፦
"خير الدعاء دعاء يوم عرفة"
"ከዱዓ ሁሉ በላጩ ዱዓ ማለት የዓረፋ ቀን ዱዓ ነው"

ስለ ጁሙዓ ቀን ዱዓ ነብያችንﷺ እንዲህ ይላሉ፦
"فيه ساعة لا يوافقها عبد مسلم، وهو قائم يصلي، يسأل الله شيئًا إلا أعطاه إياه"
"በጁሙዓ ቀን ውስጥ የሆነች ሰዓት አለች በዚች ሰዓት አንድም ሙስሊም የሆነ ባሪያ ቆሞ እየሰገደ ለአላህ ምንም ነገር አይጠይቅም አላህ ያንን ነገር ቢሰጠው እንጂ

አላህ ﷻ የዚህን ቀን ትሩፋቶች ከሚያገኙ እና ወንጀላቸው ከሚማርላቸው ሰዎች እንዲያደርገን እለምነዋለሁ በመልካም ዱዓቹ አትርሱኝ

ይህን አንገብጋቢ ማስታወሻ ለምታውቁትም ለማታውቁትም ሙስሊም ለሆነ አካል እንድታሰራጬ እና የመልካም ስራ ተቋዳሽ እንድትሆኑ እጠይቃለሁ በሉ እንግዲህ ሼር ሼር ሼር
ክፍል አንድን በዚህ ያገኙታል https://t.me/tolehaahmed/143

ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ
طلحة أحمد