Get Mystery Box with random crypto!

የምላስ ጣጣ ┄┄┉┉✽‌»‌ »‌✽‌┉┉┄┄ | እስላማዊ ትምህርቶች የሚለቀቅበት ቻናልነው(ኢንሻ አሏህ)@@@@/////………Eslamic Knowledge

የምላስ ጣጣ
┄┄┉┉✽‌»‌ »‌✽‌┉┉┄┄

#ክፍል_አንድ

★★#መግቢያ★★

#የምላስ_ጉዳይ_አሳሳቢ_ነው።

መልእክተኛው፦"ብልቱንና ምላሱን ለጠበቀልኝ ሰው በጀነት ዋስትና እሰጠዋለሁ።" ማለታቸው ይህነኑ ያመለክታል። የብልትንስ ጣጣ በጾምና በጋብቻ መከላከል ይቻላል። የምላስ ጉዳይ ግን በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ይከተለናል።

ከምላስ ጋር የተያያዙ ማህበራዊ በሽታዎች ተስፋፍተዋል። ሰዎች እንደ ቀላል ይዋሻሉ፤ ምንም ሳይመስላቸው ያማሉ፤ነገር ያሳብቃሉ፤ ቃልኪዳናቸውን ያፈርሳሉ፤ምስጢር ያባክናሉ።ክብደቱ ሳይሰማቸው በማይመለከታቸው ጉዳይ ውስጥ ይዘፈቃሉ፤ያፌዛሉ.....።የዚህ ኡማ ቀደምት አባላት (ሰለፉነ ሳሊሂን)"የምላስን ጣጣ" ከምንም በላይ ይፈሩ እንደነበር ከታሪካቸው እንረዳለን።

ለየትኛውም ማህበራዊ በሽታ መስፋፋት አንዱ ምክንያት የግንዛቤ ጉድለት እንደሆነ ይታመናል። እናም ችግሮችን ለመቅረፍ ስለጉዳዩ ሰዎች እንዲያውቁ ማድረግ ትልቁን ድርሻ ይይዛል።ጉዳዩ አሳሳቢ በመሆኑ እኛ ደግመን ደጋግመን ልንማማር ይገባል።

ምላስ ከሰው ልጅ የአካል ክፍሎች ውስጥ እጅግ አደገኛውና አመፀኛው ነው። በራሱ በሰው ላይ በመማፅ አቻ አይገኝለትም። በመጠን አናሳ ቢሆንም ሊያስከትለው የሚችለው ጥፋት ግን እጅግ ግዙፍና አስከፊ ነው።

በርሱ አማካኝነት የሰዎች ማንነት ይለያል። ደረጃቸውም ይወሰናል።

በርሱ ሰበብ አንዱ ወደላይ ፣ወደ ሰማየ ሰማያት ከፍ ሲል የሌላው የዝቅጠት ወለል ይነካል።

የሰው ልጅ በእርሱ አማካይነት የውስጥ ሀሳቡን ለሌሎች ይገልፃል። የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ሲሉ እውነቱን ተናግረዋል።

المرأ بأصغره بقلبه ولسانه
"የአንድ ሰው ማንነትና ደረጃ በሁለት ትንንሽ የአካል ክፍሎቹ ይለያል(ይወሰናል)።በቀልቡና በምላሱ

ከሰው ልጅ የአካል ክፍሎች ውስጥ ምላስን ይበልጥ አመፀኛና አደገኛ ካደረጉት ምክንያቶች ውስጥ የተወሰኑትን በሚቀጥለው ክፍል እናያለን ኢንሻአላህ!!

❀ኢንሻአላህ
❀ #ክፍል 2
❀ ይቀጥላል...

#ሸር

@husnel_khuluk